የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስፈፃሚውን በተገቢው መንገድ አይቆጣጠርም፤ ተጠያቂ አያደርግም እየተባለ በህዝብ ዘንድ በተደጋጋሚ ይወቀሳል። አባላቱም በህገ መንግሥቱ በተቀመጠው መሰረት ለህዝብ፣ ለህሊናቸውና ለህገ መንግሥቱ ጠበቃ ከመሆን ይልቅ የፓርቲያቸው ጠበቃ ናቸው። በዚህም በአገሪቱ ዴሞክራሲ እንዳይኖር፣ ሙስና እንዲንሰራፋ፣ የህግ የበላይነት እንዳይከበር ምክንያት ሆነዋል ሲሉ የተለያዩ ምሁራን በተደጋጋሚ የሚገልጹት ጉዳይ ነው።

በቅርቡ በአገሪቱ የተፈጠረውን ለውጥ ተከትሎ ግን ምክር ቤቱ «አፉ መፈታት ጀምሯል።» እየተባለ ተጠያቂነቱ መጨመሩን፣ በነፃነትም መወሰን መጀመሩን ይገለፃል። በህጉ መሰረት ኃላፊነታቸውን የማይወጡ አስፈፃሚዎችን ለመጠየቅም መጀመሩን የሚያነሱ አሉ። በአጠቃላይ ባለፉት ስድስት ወራት በምክር ቤቱ ጥሩ እንቅስቃሴ መጀመሩን የሚያመላክቱ ሁኔታዎች አሉ። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥም ከወጡት አከራካሪ ህጎችንም ጨምሮ መርምሮ እንዲጸድቁ አድርጓል፡፡ ከምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች መካከል አንዱ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ነው። ከቋሚ ኮሚቴው ሊቀመንበር ከአቶ ተስፋዬ ዳባ ጋር ስለ ምክር ቤቱና የቋሚ ኮሚቴው ተጠሪ ተቋማት አፈጻጸም በተመለከተ ቃለ ምልልስ አድርገንላቸው እንደሚከተለው አቅርበናል። መልካም ንባብ።

አዲስ ዘመን፡– የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀደም ሲል ከነበረው አሰራር ያሻሻለው ነገር አለ?

አቶ ተስፋዬ፡– ምክር ቤቱ ቀደም ሲል ከነበረው አሰራር ትልቅ ለውጥ አድርጓል። በመጀመሪያ ደረጃ አደረጃጀቱን አስተካክሏል። ቋሚ ኮሚቴዎችን ከሃያ ወደ አስር ዝቅ አድርጓል። በዚህም ተለጥጠው የነበሩ ሥራዎችን በመሰ ብሰብ አባላቱን በማብዛት ሥራዎች ለመቆጣጠር ችሏል፤ በጥራት እንዲሠሩም አድርጓል።

ሁለተኛው ለውጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የቋሚ ኮሚቴዎች ሊቀመናብርትና ሚኒስትሮች የሥራ ውል ስምምነት ተፈራ ርመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ ትኩረት ሰጥተው አስፈፃሚዎች ፓርላማው የሚሰጣቸውን አስተያየቶች በትክክል መቀበልና መፈጸም እንዳለባቸው የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል። ይህም ለሥራችን ልዩ መደላድል ፈጥሯል።

ምክር ቤቱ ከዚህ ቀደም በተለየ ክትትልና ቁጥጥር አድርጓል፡፡ በውጤት ላይ የተመሰረተ የግምገማ ሥርዓት ተከትሏል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የመመዘኛ መስፈርት አውጥ ቷል። ያወጣውን የመመዘኛ መስፈርት ለሁሉም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች በመላክ ግብረ መልስ ተሰጥቶ፤ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች እንደ ሚመዘኑ ተግባብተናል። በተግባባነው መሰረትም በምዘናው ከ50 በመቶ በታች የሚያመጡ ዝቅተኛ፤ ከ50 እስከ 70 በመቶ መካከለኛ፤ ከ70 እስከ 90 በመቶ ከፍተኛ እና ከ90 በላይ በጣም ከፍተኛ ተብለው እንደሚፈረጁ ተግባብተናል። ይህ አቅጣጫም የተለየ አቅጣጫ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ለውጡን የሚያግዙ ህጎችና ስምምነቶችም በምክር ቤቱ መውጣታቸውም የተለየና ያልነበረ ሥራ ነው። የፓርላማውን ጽሕፈት ቤት ለማጠናከር የተሠራው ሥራም የዘንድሮውን የፓርላማ እንቅስቃሴ ልዩ ያደር ገዋል።

አዲስ ዘመን፡– ምክር ቤቱ አስፈፃሚውን የመጠየቅም፣ በአባላቱ መካከል የመከራከርና የመቃወም ሁኔታ እየተሻሻለ ነው። ይህንንም ምክርቤቱ ጥርስ እያወጣ ነው የሚሉ አሉ፡፡ እንዲህ ማለት ይቻላል?

አቶ ተስፋዬ፡– ቀደም ሲልም በምክር ቤቱ ክርክሮች ይካሄዱ ነበር። ነገር ግን፤ በድምጽ የመቃወም ሁኔታ አልነበረም። ይህም የፓርላማው የፓርቲ ዲሲፕሊን አጠቃቀም ግልጽ ስላልነበረ ነው። መናገር ቢቻልም አባላቱ ተቃውሞ ሲያደርጉ በአሰራር ይገመገሙ ነበር። በዚህም የተነሳ ቢያምኑበትም ባያምኑበት ከአስፈጻሚው ቀርበው የሚወጡ አዋጆችን በሙሉ ይደግፉ ነበር።

ይህን ሁኔታ በመገምገም የምክር ቤት አባላት በህገ መንግሥቱ ተጠሪነታቸው ለህገ መንግሥቱ፣ ለህሊናቸውና ለመረጣቸው ህዝብ ነው። ፓርቲውን ወክለው እስከተመረጡ ድረስም የፓርቲ ዲስፕሊን አለ። ይሁን እንጂ፤ ፓርቲው የሚፈልጋቸውን ወሳኝ አጀንዳዎች በፖሊሲ ጉዳይ ላይ ምንም አይነት ድርድር ባይኖርም፤ ከዚህ መልስ ባሉት ጉዳዮች አባላቱ ያመኑበትን አቋም መያዝ እንደሚችሉ ከመግባባት ተደርሷል። ለዚህ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያቀርቡትን ጭምር ሁሉም አባላት የማይቀበሉት።

ፓርላማው ፓርላማ የሚሆነው የሀሳብ ብዝሃነት ሲኖር ነው። ክርክር ተደርጎ ከዚያ አባላቱ ያመኑበትን አቋም በነፃነት ሲይዙ ነው ጠንካራ ፓርላማ የሚኖርን፤ በዚህ ስድስት ወር በምሳሌ የሚነሳውና የሦስት ቋሚ ኮሚቴዎች ሹመት ውድቅ የመደረጉ ጉዳይ በምክር ቤቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከናወነና ቀድሞ የማይታሰብ ነበር። የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አዋጅ ሲወጣም የተደረገው ተቃውሞና ክርክርም ሌላው ምሳሌ ነው። ይህ በጣም ጤናማና ፓርላማውን ፓርላማ ያደረገ ነው። ህዝብ ምስክርነት እየሰጠ ያለው ለዚህ ነው። እስካሁን የት ነበር ሊባል ይችላል፤ አዎን! እስካሁን ድረስ የፓርቲ ዲስፕሊን ፓርላማውን ጠርንፎ ይዞት ነበር።

አዲስ ዘመን፡– የአስፈፃሚ ሥራ ተመዝኖ ደረጃ የወጣ ከሆነ የተቋማቱን አፈፃፀም በደረጃቸው ሊገልጹልኝ ይችላሉበጠቅላይ ሚኒስትርጽሕፈት ቤት እንደተደረገው ግምገማ ምክር ቤቱስ ግምገማ አድርጓል?

አቶ ተስፋዬ፡– በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተደረገው የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ምክር ቤቱ ያደረገው ሳይሆን አስፈፃሚው ያደረገው ግምገማ ነው። ምክር ቤቱ ባስቀመጠው መስፈርት መሰረት አስፈፃሚውን መዝኖ ይፋ የሚያደርገው በዓመቱ መጨረሻ ላይ ነው። በግማሽ ዓመቱ ምክር ቤትና ቋሚ ኮሚቴዎች ክትትልና ቁጥጥር እያደረጉ ነው። በዚህም መሰረት የዘንድሮው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች አፈጻጸም ካለፉት ዓመታት በጣም የተሻለ ነው።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

ለምሳሌ፤ በእኛ ቋሚ ኮሚቴ ስር ያሉት የውጭ ጉዳይ፣ የሰላምና የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን አፈጻጸም ገም ግመናል፡፡ ጥሩ አፈፃፀም ነው ያላቸው፤ በተለይም የመከላከያ ሚኒስቴር እያደረገ ያለው ማሻሻያ በጣም ጥሩ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ከኤርትራ ጋር የተደረገውን የሰላም ሂደት ማሳካቱ፣ በውጭ አገር ያሉ ዜጎችን መብት ለማስከበር የሄደበት ርቀትና ከተለያዩ ተቋማት ጋር ባደረጋቸው የብድር ስምምነቶች ውጤታማ ነበር። የሰላም ሚኒስቴርም አዲስ ቢሆንም በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ነው። ከዚህም በላይ በመስክ ምልከታ ከዚህ በፊት ተቋማቱም ሆኑ ኃላፊዎች በአካል ታይተው የማይታወቁ እንደ የፋይናንስ ደህንነትና መረጃ ማዕከል፣ የብሄራዊ መረጃ ደህንነት ኤጀንሲ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ውስጥ በአካል ተገኝተን የመስክ ምልከታ አድርገናል። በምልክታውም ተቋማቱ ውጤታማ ሥራ እያከናወኑና ማሻሻያ እያደረጉ መሆኑን ተረድተናል።

አዲስ ዘመን፡– ቀደም ሲል ፓርላማው ሥራዎች እንዲሻሻሉ አስተያየት ቢሰጥም አስፈፃሚው አያስተካክልም ነበር። ለዚህ እንደማሳያ የዋናኦዲተርን የኦዲት ሪፖርት ማንሳት ይቻላል። አሁን ላይ አስፈፃሚው ምክር ቤቱ የሚሰጠውን አስተያየት በተጨ ባጭ እያስተካከለ ነው?

አቶ ተስፋዬ፤፡– አሁን ላይ ቀድሞው ችግር በተጨባጭ እየተሻሻለ ነው። እንደማሳያ የዋና ኦዲተርን የኦዲት ግኝት ብንመለከት እየተደረገ ያለው ማስተካከያ አበረታች ነው። ምክር ቤቱ ችግሩን ለመፍታት በራሱ ኮሚቴ አዋቅሮ ለማስተካከልም ጥረት እያደረገ ነው። የማያስተካክሉ አስፈፃሚ ተቋማትንም ተጠያቂ ለማድረግ ዝግጁ ነው። አስፈፃሚውን ተጠያቂ ከማድረግ በፊት ግን እንዲያስተካክሉ እየተሠራ ነው። በርካታ ተቋማትም እያስተካከሉ ነው።

ለምሳሌ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ብንወስድ ከንጉሡ ጊዜ ጀምሮ ያልተወራረዱ የኦዲት ግኝቶች ነበሩበት። በዚህም መሰረዝ ያለበት እንዲሰረዝ፤ መስተካከል ያለበት እንዲስተካከል ተደርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተለያዩ ተቋማት መከፈል ያለበትን ገንዘብ እንዲከፍል መመሪያ አስተላልፈዋል። ለኦዲት ግኝት ምክንያት የሚሆነውና ካለው ህግ ጋር የማይሄደው የውጭ ግዥም እንዲጣጣም በማስፈቀድ መመሪያ ወጥቷል። በመከላከያ ሚኒስቴርም ኦዲት እንዳይደረጉ ይከለከሉ የነበሩ ሂሳቦች የአገርን ጸጥታ ችግር ላይ የማይጥሉትን በመለየት ኦዲት እንዲደረግ በአዋጁ ማሻሻያ ወጥቷል።

የዜጎችን መብት በማስከበር ረገድም እንዲስ ተካከሉ የተሰጡ አስተያየቶችም አፈፃፀምም  መልካም ነው። የሚሰጡ አስተያየቶችን እንዲያ ስተካክሉ ወይም የማያስተካከሉበትን ምክንያት እንዲያቀርቡ ስምምነት ስለተደረገ ምላሽ የመስጠቱ አሰራር በጣም ተሻሽሏል።

አዲስ ዘመን፡– ምላሽ የማይሰጡ አስፈፃ ሚዎችን ተጠያቂ ለማድረግ ምክር ቤቱ ምን ያህል ዝግጁ ነው?

አቶ ተስፋዬ፡– እስካሁን የምንሰጠውን ግብረ መልስ የመመለስ ችግር የለም። ከአስፈጻሚዎች ጋር ያለን ግንኙነትም ተጠናክሯል። ነገር ግን፤ ቋሚ ኮሚቴዎች፣ ምክር ቤቱና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ምላሽ የማይሰጡ አስፈጻሚዎችን ተጠያቂ ለማድረግ ዝግጁ ነን። በዓመቱ መጀመሪያ ላይ አስፈፃሚውና የፓርላማ ኃላፊዎች ስምምነት ተፈራርመዋል። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርላማው «እከሌ የተባለ ሚኒስቴር ወይም ኃላፊ በተገቢው አልፈጸመም፤ አንሳው» ካላቸው እንደሚያነሱትና እንደማይደራደሩ በፊታቸው አስታውቀዋል። እርሳቸው ራሳቸው ከህዝብ በላይ አለመሆናቸውንም ተናግረዋል። በመሆኑም፤ ምክር ቤቱ በአግባቡ ያልፈጸሙትን ተጠያቂ ለማድረግ ምንም የሚያስቸግረው ነገር የለም።

አዲስ ዘመን፡– እርስዎ በሚመሩት ቋሚ ኮሚቴ ስር ያሉ ተቋማት አብዛኞቹ ማሻሻያ አድርገዋል። ማሻሻያ በማድርጋቸው ምን ውጤትአመጡ?

አቶ ተስፋዬ፡– እኔ የምመራው ቋሚ ኮሚቴ ሦስት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችና 16 ተጠሪ ተቋማት ያለው ነው። አብዛኞቹ ማሻሻያ እያደረጉ ነው። ጥሩ ውጤት ያመጡም አሉ።

በመጀመሪያ ማሻሻያ ያደረገው መከላከያ ሚኒስቴር ነው። ሚኒስቴሩ ያሉበትን ጉድለቶች በማየት አዋጁን በማሻሻል ጭምር እንደገና ተደራጅቷል። ተቋሙ ራሱን ሲያሻሻል ካሉበት ጉድለቶች ማሻሻያ በማድረግ ነው የጀመረው፤ በግምገማውም በኢትዮጵያ ህዝብ አመኔታን ማግኘቱ አንዱ የተነሳ ጉዳይ ነው። ይህን ለመፈጸም መከላከያ ያደረገው «ኢትዮጵያን መምሰል» የመጀመሪያው ማሻሻያ ነው። ሁሉንም ብሔር ብሔረሰቦች ከላይ እስከታች በማካተት የብሔር ተዋጽኦን መሰረት በማድረግ ተደራጅቷል። በተለይም ችግሩ በአመራር ደረጃ ስለነበረ በዚህ ላይ ከፍተኛ ሥራ ተሠርቷል። በተለይ፤ የታዳጊ ክልሎችን ተወካዮች በማሳተፍ ሙሉ እርካታ ስላልነበረ እርካታ ለመፍጠርም እየሠራ ነው።

ሁለተኛው በመከላከያ የተደረገው ማስተካካያ የሰራዊቱ አባላት ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኛነት ነጻ የማድረጉ ጉዳይ ሲሆን፤ እስካሁን አባል የሆኑ/ የነበሩ ሰዎች ሥራቸውን ወይም የፖለቲካ ድርጅት አባልነታቸውን እንዲመርጡ ተደርጓል። በዚህም

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

ከመቼውም ጊዜ በላይ የመከላከያ ሠራዊቱና ተቋሙ ጥብቅናቸው ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እንዲሆን ተደርጓል።

በንብረት አያያዝና አጠቃቀም ረገድም፤ የሙስናን በር የሚዘጋ የአሰራር ማሻሻያ ተደርጓል። ከዚህ በፊት ሲደበቁ የነበሩ አንዳንድ የተቋሙ ሥራዎች ለኦዲት ግልጽ ተደርገዋል። ከሠራዊት መብትና ግዴታም ጋር ተያያዞ የተደረጉ ማሻሻያዎች አሉ። የሠራዊቱን መብት ለማስጠበቅም ቅሬታ ያለው ሠራዊት እስከ ጠቅላይ አዛዥ ሄዶ ቅሬታውን የሚያቀርብበት ሥርዓት ተዘርግቷል። በአባላቱ ደመወዝ ይገዛ የነበረው ወታደራዊ ልብስም በመንግሥት ሙሉ ወጪ እንዲቀርብ ተደርጓል። ከዚህ በተጨማሪ በመከላከያ ውስጥ የባህር ላይ ጥቃትንና የሳይበር ጦርነትን ለመከላከል የሚችሉ የሠራዊት ክፍሎች ማቋቋም ተወስኖ እየተሠራ ነው። በአጠቃላይ በመከላከያም ሆነ በሌሎቹ ተቋማት መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እየተሠራ ነው። በሁሉም ተቋማት እስካሁን የተሠራው ሥራ በህዝብ ዘንድ ድጋፍ እያገኘ ነው።

አዲስ ዘመን፡– በመከላከያም ሆነ በጸጥታ ተቋማት ውስጥ የፖለቲካ አባል የነበሩ ሰዎች ምን ሆኑ?

አቶ ተስፋዬ፡– ሁለት አማራጭ ተሰጥቷቸዋል። አንደኛው፤ የፖለቲካ አባልነታቸውን ትተው በተቋማቱ መቀጠል፤ ሁለተኛው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተቋሙን ለቅቀው በመውጣት በፖለቲካ አባልነታቸው መቀጠል ነው። አብዛኞቹ አባላት የፖለቲካ ድርጅት አባልነታቸውን ትተው በመከላከያና በደህንነት ተቋማት ውስጥ ሥራቸውን ቀጥለዋል። በዚህም መሰረት፤ የብሔራዊ መረጃ ደህንነት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸውን ትተው ነው በኃላፊነታቸው የቀጠሉት፤ በአጠቃላይ የተቋማቱ ሠራተኞች ወገንተኝነታቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ እንዲሆን ተደርጓል። ይህ የደህንነት ተቋማትንም ሆነ የመከላከያ ሠራዊቱን ከፖለቲካ ነፃ የማድረግ ሥራ በሚገባ ተከናውኗል። በአሁኑ ጊዜ የድርጅት መዋጮ የሚያዋጣም ሆነ ስብሰባ የሚያደርግ የሠራዊት አባል/አካል የለም። በኢህአዴግ ምክር ቤትም ሆነ በሌሎች ድርጅቶች በሥራ አስፈፃሚነትም ሆነ በሌላ ደረጃ በፖለቲካ የሚሳተፍ ሠራተኛም ሆነ ኃላፊ የለም።

እነዚህ ተቋማት ባደረጓቸው ማሻሻያዎች በህዝብ ዘንድ አመኔታ አሳድረዋል። በተቃዋሚዎችም በተለያየ መልኩ ይታዩ የነበሩ በመሆናቸው አሁን በግልጽ እንዲጎበኟቸው ጭምር ተደርጓል። ህዝብ ስለተቋሙ ያለውን መረጃ ለተቋሙ በመስጠት አብሮ ለመሥራት እየተንቀሳቀሱ ነው።

በአገሪቱ ውስጥ ህገ ወጥ የገንዘብና የጦር መሳሪያ ዝውውርና ሌሎች ወንጀለኞችን በማጋለጥ የብሔራዊ መረጃ ደህንነት የአንበሳውን ድርሻ እየወሰደ ነው። ወንጀሉ ሲጋለጥ መጨረሻ ላይ የያዙት አካላት ስም ተጠቅሶ ቢገለጽም በሪፖርታቸው እንዳረጋገጥነው ግን በዚህ ዙሪያ ኤጀንሲው ኃላፊነቱን በከፍተኛ ደረጃ እየተወጣ ነው። የተቋሙን ሥራ የበለጠ ለማሻሻል አዋጅ አዘጋጅተው አጠናቅቀዋል። ይህን በማጽደቀም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደርጋሉ።

አዲስ ዘመን፡– የተቋማቱ ሠራተኞች ከፖለቲካ አባልነት ውጪ መሆናቸው ያበረከተው አስተዋጽዖ አለ?

አቶ ተስፋዬ፡– በጣም አበርክቷል። ከፖለቲካ ነፃ መሆናቸው ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መተማመን ፈጥሯል። ህብረተሰቡም በተቋማቱ እምነት መጣል ጀምሯል። ገዥውን ፓርቲ ሁሉም ህዝብ ይደግፈዋል ማለት አይደለም። እነርሱ ነፃ በመሆናቸው ሁሉንም አካል በእኩል ዓይን ያያሉ ማለት ነው። በዚህም ከዚህ በፊት የማይቻሉ የነበሩ መረጃዎች ከህዝብ እየተገኙ ነው። ተቋማቱ ከፖለቲካ ነፃ መሆናቸው ጥብቅናቸው ለህዝብ መሆኑ ይበልጥ ያጎላዋል፤ በህዝብም አመኔታ አግኝተዋል።

አዲስ ዘመን፡– በስድስት ወር ምን ያህል አዋጆቹን አጸደቃችሁ?

አቶ ተስፋዬ፡– በእኛ ቋሚ ኮሚቴ ያለፉ 13 አዋጆች ጸድቀዋል። ምክር ቤቱ በአጠቃላይ 22 አዋጆች በግማሽ ዓመቱ አጽድቋል። ከጸደቁት አዋጆች ከግማሽ በላይ በእኛ ቋሚ ኮሚቴ ያለፉ ናቸው ማለት ነው።

አዲስ ዘመን፡– አዋጁን በማውጣት ሂደት የአባላት ተሳትፎ ምን ይመስልላልምክር ቤቱን በሚመጥን ደረጃ ነው?

አቶ ተስፋዬ፡– ህጎቹን በማውጣት ሂደት ጥሩ ሥራ ተሠርቷል። በሂደቱ ረቂቆቹን ከሚያመነጩ አካላት ጋር ጥልቅ ውይይት አድርገናል። ባለድርሻ አካላትም እንዲወያዩበት ተደርጓል። የምክር ቤቱ የህግ ባለሙያዎችም አስተያየት ሰጥተዋል። ፓርላማውና ቋሚ ኮሚቴዎችም በሂደቱ በደንብ ተወያይተው ነው የጸደቁት፤ አብዛኞች አዋጆች በስምምንት የጸደቁ ናቸው። በአጠቃላይ የምናወጣቸው አዋጆች ጥራታቸው እየጨመረ ነው።

አዲስ ዘመን፡– ባለፉት ስድስት ወራት ካወጣችኋቸው ህጎች «የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ኮሚሽን አዋጅ በምክር ቤቱም ክርክሩ ከፍ ያለነበር። ህገ መንግሥቱን ጥሷል» የሚሉ አካላት አሉ። በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድነው?

አቶ ተስፋዬ፡– የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ኮሚሽን እና የእርቅና ሰላም አዋጆች በባህሪያቸው የኮሚሽኑ አባላት የውሳኔ ሀሳብ እንዲያቀርቡ ታስቦ የተቀረጹ አዋጆች ናቸው። እነዚህ አዋጆች ከአስፈፃሚው በጎ ሀሳብ ወደ ምክር ቤቱ የመጡ እንጂ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚው በደንብ ሊያቋቁማቸው የሚችሏቸው ነበሩ። ነገር ግን ሥራ አስፈፃሚው በህገ መንግሥቱ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ጸጥታን የማስጠብቅ ኃላፊነት ስላለበትና ችግሩ በርካታ አካባቢዎችን የሚዳስስ በመሆኑ በአስፈፃሚው ከሚወሰን የሁሉም ብሔር ብሔረሰብ ተወካዮች እንዲያጸድቁት በሚል በጎ ሀሳብ ነው ወደምክር ቤቱ የተመራው፤ ምክር ቤቱም በተሰጠው ሥልጣን መሰረትም አዋጁን አጽድቆታል።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

አዋጁ ለምክር ቤቱ ተመርቶ በመጀመሪያ ንባብ ሲቀርብ ከፌዴሬሽንና ከክልሎች ሥልጣን ኃላፊነት ጋር ይጋጫል የሚል ሀሳብ ተነስቷል። ይህን ለማስተካከልም በመጀመሪያ የተደረገው ይጋጫል ወይስ አይጋጭም የሚለውን ለማየት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ባለሙያዎችና ኃላፊዎች፤ አዋጁን ካመነጨው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እና ከጠቅላይ አቃቤ ህግ ባለሙያዎች ጋር አንድ ቀን የፈጀ ውይይት አድርገናል።

በስብሰባውም ላይ በህገ መንግሥቱ ለፌዴሬሽን ከተሰጠው ሥልጣንና ተግባር፣ ከፌዴሬሽን ማቋቋሚያ አዋጅ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ጋር ይጋጫል ወይ የሚል ነበር። የሚጋጭ ከሆነ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚያስገባ በመሆኑ የተደረገው የኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባር ከመጀመሩ በፊት ለፌዴሬሽን ምክር ቤትና ለክልሎች በህገ መንግሥቱና በሌሎች ህጎችና አዋጆች የተሰጡ ሥልጣኖች እንደተጠበቁ ሆነው የሚከተሉት ሥልጣንና ኃላፊነት ተሰጥተውታል በማለት እንዲጀምር ተደርጓል። የተሰጠው ሥልጣንና ተግባራት ጥናት ማድረግ፣ ምክረ ሀሳብ መስጠት፣ ሪፖርት ማቅረብ እና ማማከር የመሳሰሉት ናቸው። ኮሚሽኑ ምንም አይነት የመወሰን ሥልጣን የለውም። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሥልጣንን አልነካም። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን ብዙ ህዝብ ከሚኖርበት አካባቢ ዘሩ እየተቆጠረ እየተፈናቀለ ነው። የማንነትና ክልል እንሁን የሚሉ ጥያቄዎች በዝተዋል። እኔ በዚህ ክልል መካለል የለብኝም የሚሉም አሉ። እነዚህ ጉዳዮች ለበርካታ ግጭቶች ምክንያት እየሆኑ ነው። አዋጁም የወጣው ይህን ለመፍታት ከቅን ሀሳብ በመነጨ ነው። የተጠናውን ጥናት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ካላመነበትና ካልተቀበለው የማይረባ ነው ብሎ መጣል እንደሚችል አስቀምጠናል። ይህ በምንም በምንም መስፈርት ከህገ መንግሥቱ ጋር አይጋጭም።

አዲስ ዘመን፡– በዚህ ደረጃ ከሆነ ምክር ቤቱ ውስጥ ለምን በዚያ ደረጃ ክርክር ተካሄደ?

አቶ ተስፋዬ፡– ዴሞክራሲያዊ ፓርላማ ማለት ይህ ነው። ምክር ቤቱ ከፓርቲ ዲሲፕሊን ወጥቶ አባላት ያመኑበትን ሀሳበ ሰንዝረው ተከራክረዋል። የፈለጉትን መደገፍና መቃወም ችለዋል። የራሳቸውን ህገ መንግሥታዊ የፓርላማ አባልነት መብት ነው የተጠቀሙት፤ የተገመገመ ሰውም የለም።

አዲስ ዘመን፡– የትግራይ ክልል ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ውሳኔ አሳልፏል። ስለተላለፈው ውሳኔ ያውቃሉለመሆኑ ያስተላለፈው ውሳኔውምንድነው?

አቶ ተስፋዬ፡– የተላለፈውን ውሳኔ አላውቅም። አንዳንድ ሚዲያዎች «በእኛ ክልል ተፈፃሚ አይሆንም» የሚል ውሳኔ አስተላለፉ የሚል አይቻለሁ። ሌሎች ደግሞ አዋጁ ህገ መንግሥቱን ይቃረናል በማለት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የህገ መንግሥት አጣሪ እንዲተላለፍ መወሰናቸውን ይገልፃሉ።

የክልሉ ምክር ቤት አንቀበለው ማለት አይችልም። የምንከተለው የፌዴራል ሥርዓት እንደመሆኑ የክልልና የፌዴራል መንግሥታት ሥልጣን የተከፋፈለና አንዱ የሌላውን ሥልጣን የማክበር ግዴታ አለበት። በፌዴራል መንግሥት የሚወጡ አዋጆች አንድን አካባቢ ይጎዳሉ ተብሎ አልቀበልም ማለት አይቻልም። ይህ የዴሞክራሲ ጉዳይ ነው። አንቀበልም ካሉ ኢ-ህገ መንግሥታዊ ይሆናል። ተቃውሞ ማሰማት መብት ነው ለአብላጫ ድምጽ መገዛት ግን ግዴታ ነው። የፌዴራል መንግሥት ያወጣውን አዋጅ የማስፈጸምና የማክበር ግዴታ አለባቸው።

ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ለመሄድ ግን እንኳን የክልሉ ትልቁ የስልጣን ባለቤት የሆነው ምክር ቤት ወስኖ ግለሰብም ሄዶ ህገ መንግስት መጣስ አለመጣሱን ለህገ መንግስታዊ ትርጓሜ ማሰጠት ህገ መንግስታዊ መብት ነው።

አዲስ ዘመን፡– የሁለቱ ኮሚሽኖች አባላት ከስብጥርና በተለያየ መልኩ የሚነሱና ለኮሚሽኖች መመረጣቸውንም የማያውቁ ግለሰቦች እንዳሉይገለፃል። ሹመቱን እንዴት አጸደቃችሁት?

አቶ ተስፋዬ፤ ስናጸድቅ ስብጥሩን በበጎ መልኩ ነው ያየነው። ሁሉም አባላት በመልካም ስማቸው የሚታወቁ ናቸው። የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው የፖለቲካ ሰዎችም አሉበት። ከተለያየ ሙያ የተውጣጡ ትላልቅ ምሁራን አሉበት። በዚህ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በጣም ነው ያደነቅነው። ከኮሚሽኑ ዓላማ አንፃር ማንም እንደፈለገ የሚያዛቸው አይደሉም። በተቻላቸው መጠን ሁሉም ለአገራቸው አስተዋጽዖ ያደረጉ ናቸው። የዚችን አገር ሰላምና መረጋጋት የሚፈልጉም ናቸው። በመጥፎ አርዓያነታቸውና በመጥፎ ሥነምግባራቸው የሚታሰቡ ሰዎች የሉበትም። አልተነገርንም የሚሉ ሰዎች ካሉ ሹመቱን የሰጣቸውን አካል ማናገር ያስፈልጋል። እኔ ግን አልሰማሁም። ዋናው በቅንነት ለአገራቸው የሚያበረክቱትን አስተዋጽዖ አይተን ነው ያጸደቅነው፤

አዲስ ዘመን የካቲት 9 ቀን 2011 – አጎናፍር ገዛኽኝ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *