ኩምሳ ድሪባ በጫካ ስሙ ‘ጓድ መሮ’ ምዕራብ ወለጋ ስለመኖሩ ጥርጣሬው ከፍተኛ መሆኑንን የሚጠቁሙ ክፍሎች  ድምጽ እየተሰማ ነው። መሮ የት እንደሆነ ቆርጠው በስም የማይናገሩ ክፍሎች እንደሚሉት ግን ከኢትዮጵያ አልወጣም። አለ ከሚባልበት ቦታ እርቆና ከለላ ተሰጥቶት እየኖረ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ መሮ የሚመራው ሃይል ከዳውድ ኢብሳ የዕዝ ሰንሰለት አፈንግጦ ከወጣ የቆየ መሆኑንን ጎልቶ እየተሰማ ነው።

“ብችዬን አስክቀር እዋጋለሁ” ሲል በተደጋጋሚ መረጃ በሚሰጥበት የቢቢሲ አማርኛ ዝግጅት ክፍል ላይ የተናገረው መሮ የሚመራው ሃይል አለበት በሚባልበት ስፍራ ቄለም ወለጋ አቅንተው የነበሩ ከሦስት ያላነሱ የአስታራቂ ኮሚቴ አባላት ታፍነው መወሰዳቸው የዚሁ ነጸብራቅ ሆኖ ተወስዷል። ይህ ቀደም ሲል ድርድሩ ከዳውድ ኢብሳ ጋር ሳይሆን ከሌሎች ጋር ሊሆን እንደሚገባ ሲወተውቱ የነበሩ ሲሰጡ የነበረውን አስተያየት አጉልቶታል።

ይህ ሃይል በኦነግ ሸኔ ስም ተሰይሞ ክተት ካለበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ ንብረትና ገንዘብ ተዘርፏል። ሰዎች ተገለዋል። ታፍነዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ተፈናቅለዋል። የመከላከያና የፖሊስ ሃይሎች ተገለዋል። ይህ ሁሉ ቢሆንም አቶ ዳውድ ኢብሳ በዝምታ የታለፉት ከላይ በተገለጸው ምክንያት እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። ይህ ባይሆን ኖሮ አቶ ዳውድ ” በቃ ፤ትጥቅ ፍቱና ግቡ” የሚል ትዕዛዝ ባሳለፉ ማግስት ነበሮች መጠናቀቅ እንደሚገባቸው የሚናገሩ ” ሰራዊቱ ካሁን በሁዋላ የአባገዳዎች ነው። የኦሮሞ ህዝብ ነው። ለናንተ አደራ አስረክባለሁ” የሚለው አነጋገራቸውም እሳቸው የእዝ ሰንሰለቱን ሙሉ በሙሉ እንደማይመሩት አመልካች ነው።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በውጭ ያለው የኦነግ ሸኔ አካል አገር ውስጥ በስውር ከሚሰሩ ሃሎች ጋር በመሆን ጦርነት የማስቀጠል ፍላጎት እንዳላቸው የሚናገሩ እንደሚሉት መሮ የነዚሁ አካላት ወገን ነው። በሌላ በኩል ሰላምን የሚፈልጉት ሃይሎች ጢርነቱን አይፈቅዱም። አቶ በቀለ ገርባ ለቪኦኤ እንዳሉት በኦነግ የሰራዊት ብዛት መተማምነ ባይኖርም፣ ድርጅቱ በሰጣቸው አሃዝ መሰረት ቁጥሩ ከፍተኛ ነው። እሳቸው በዝርዝር ባይናገሩም አሁን እጅ ሰጠ የሚባለው ሃይል ቁጥሩ ከሁለት መቶ ብዙም የዘለለ አይደለም። ይባስ ተብሎ አባ ገዳና ሃድ ሲንቂዎችን አፍኖ ወስዷል።

አቶ ጃዋር መሐመድን ጠቅሶ ቢቢሲ እንዳለው ‘እየደረሰብን ያለውን ስቃይ ሁሉ በሆዳችን ይዘን እየሄድን ነው። አሁን ግን የህይወት ጉዳይ ስለሆነ መናገር አለብን። አባ ገዳዎች፣ እናቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች ለሃገር ሰላም እና እርቅ ለማውረድ ነው የሚደክሙት እንጂ ምንም በደል አልፈጸሙም። በአስቸኳይ እንዲለቀቁን እንጠይቃለን” ሲል በፌድቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።

አቶ ጃዋርና አቶ ዳውድ ቀድሞውንም ፍቅር የሌላቸው፣ ዳውድ ኢብሳ አስመራ ” በትግል” ላይ በነበሩበት ወቅት ” ያለ አንዳች ጥቅም እድሜያቸውን የሚገፍ” በሚል በሚመራው ሚዲያ ሲዘነጥላቸው ነበር። ይህ ልዩነት ዛሬ ይኑር አይኑር ባይታወቅም “እየደረሰብን ያለውን ስቃይ ሁሉ በሆዳችን ይዘን እየሄድን ነው። አሁን ግን የህይወት ጉዳይ ስለሆነ መናገር አለብን” ማለቱ የዳውድ ኢብሳ ሸኔ ኦነግን መጨረሻ አሳሳቢ ያደርገዋል።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ይህ ብቻ አይደለም። አባገዳና አደ ስንቄዎችን፣ የኦሮሞ ሽማግሌዎች ሆነው በአንድነት ባስቀመጡት የስምምነት ካላንደር መሰረት በተቀመጠው ቀነ ገደብ ወደ ሰላማዊ ህይወት የማይመለስ ታጣቂና አመራሮችን አስመልክቶ አባገዳዎች ምን መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ከውዲሁ እየተጠበቀ ነው። የተጠየቀው ሁለት ቀን ቢጨመር እንኳን የሚጠናቀቀው ቅዳሜ በመሆኑ፣ ከቀነ ገደቡ በሁዋላ ትጥቅ ፈቶ በሰላም ወደ ካምፕ የማይገባ የሰራዊት አካል በሙሉ ከኦሮሞ ህዝብ በይፋ እውቅና እንዲነፈገውና በሽፍታነት እንዲፈረጅ የሚያደርግ ውግዘት ይተላለፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ አግባብ ያላቸው ገልጸዋል።

ስለታፈኑት የእርቅ ኮሚቴ አባላት ቢቢሲ የሚከተለውን ብሏል።

የእርቅ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት የኮሚቴው አባላት የሆኑ ሁለት አባ ገዳዎች እና አንዲት ሴት በቄለም ወለጋ አንፊሎ ተብሎ ከሚጠራ ስፍራ ታፍነው እንደተወሰዱ ተናግረዋል።

አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ”ለማግባባት ወጣ እንዳሉ ነው ታፍነው የተወሰዱት፤ ክፉ ነገር እንደማይገጥማቸው እርግጠኛ ነኝ። ይህንም ችግር በቅርቡ እንፈታዋለን” ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

• “ከ[እኛ] የተለየን ጦር 5 በመቶ እንኳ አይሆንም” መሮ የኦነግ ጦር አዛዥ

”ብዙ ፈተናዎች እንደሚኖሩን እየወቅን ነው እርቅ ወደማውረዱ የገባነው። እርቅ ለማምጣት ነው እየሰራን ያለነው። ሰላምም ይሰፍናል። የሚያጋጥሙን ችግሮች ወደ ኋላ አያሰቀሩንም” ሲሉም ጥረታቸውን በዚህ ምክንያት እንደማያቋርጡም ተናግረዋል።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አነጋግረነው የነበረው የኮሚቴው ፀሃፊ ጀዋር መሃመድም የእርቅ ኮሚቴ አባላት ችግር እየገጠማቸው እንደሆነ ተናግሯል።

”የገጠመ ችግር አለ። በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ ከኮሚቴው አባላት ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ለህዝቡ መግለጫ እንሰጣለን” ሲል ጀዋር ገልጿል።

ጀዋር ሃሙስ ምሽት ላይ በፌስቡክ ገጹ ላይ ታፍነው ተወስደዋል ያላቸውን አራት ሰዎች ከስም ዝርዝራቸው ጋር አውጥቷል። ታፍነዋል ተወስደዋል የተባሉት ሰዎች የት እንዳሉ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው ተናግሯል።

• በምዕራብ ኦሮሚያ በታጠቁ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 41 መድረሱ ተገለፀ

በተመሳሳይ መልኩ በምዕራብ ወለጋ መነ ሲቡ ወረዳ የቴክኒክ አባላቱ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ከነዋሪዎች ሰምተናል። ተፈጸሟል ስለተባለው ድብደባ ግን ከቴክኒክ ኮሚቴው አባላት ማረጋገጥ አልተቻለም።

እርቅ ኮሚቴ አባላቱን ማን አፈናቸው?

የቴክኒክ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት አባ ገዳ በየነ ሰንበቶም ሆኑ የኮሚቴው ፀሃፊ ጀዋር መሃመድ የእርቅ ኮሚቴውን አባላት ያፈነው ኃይል ይህ ነው በማለት በስም ከመጥቀስ ተቆጥበዋል።

ጀዋር የአባላቱን መታፈን ይፍ ባደረገበት ጽሁፍ ”እየደረሰብን ያለውን ስቃይ ሁሉ በሆዳችን ይዘን እየሄድን ነው። አሁን ግን የህይወት ጉዳይ ስለሆነ መናገር አለብን። አባ ገዳዎች፣ እናቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች ለሃገር ሰላም እና እርቅ ለማውረድ ነው የሚደክሙት እንጂ ምንም በደል አልፈጸሙም። በአስቸኳይ እንዲለቀቁን እንጠይቃለን” ሲል በፌድቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *