30 ዓመት እንደሚሆነው የሚነገርለት ልጁ ሃምዛ ቢን ላደን፣ ከሁለት ዓመት በፊት በአሜሪካ መንግስት ሽብርተኛ ተብሎ ተፈርጇል። መረጃው እንደሚያትተው ቢን ላደን የተገደሉት ልጃቸው ሃምዛን እየሞሸሩ በነበረበት ወቅት ነው –  BBC Amharic

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እንዳስታወቀው፣ እንደ አውሮፓውያኑ በ2011 ኦሳማ ቢን ላደን ከተገደለ በኋላ ልጁ ሃምዛ ቢን ላደን የአልቃይዳ ቁልፍ ሰው ሆኗል። በዚህ ዓመት የአባቱን ገዳዮች ለመበቀል በምስልና በድምጽ የተቀረጸ መልዕክት ለተከታዮቹ አስተላልፏል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

• የቢንላደን የቀድሞ ጠባቂ በጀርመን

መስከረም 11፣ 2001 አሜሪካ፣ ኒው ዮርክ ውስጥ የአውሮፕላን ግጭት በመፍጠር ወደ 3000 የሚጠጉ ሰዎች በመግደል ተጠያቂ የሆነው ቢን ላደን፣ ከአደጋው ከአስር ዓመት በኋላ በ2011 ፓኪስታን ውስጥ በአሜሪካ ልዩ ሃይል መገደሉ ይታወሳል።

30 ዓመት እንደሚሆነው የሚነገርለት ልጁ ሃምዛ ቢን ላደን፣ ከሁለት ዓመት በፊት በአሜሪካ መንግስት ሽብርተኛ ተብሎ ተፈርጇል። መረጃው እንደሚያትተው ቢን ላደን የተገደሉት ልጃቸው ሃምዛን እየሞሸሩ በነበረበት ወቅት ነው። ቢን ላደን ልጁ ሀምዛ እንዲተካው የመጀመሪያ ምርው ነበር።  ሃምዛ በአፍጋኒስታንና በፓኪሰታን ድንበር አካባቢ ወይም ደግሞ ወደ ኢራን ተሻገሮ ሊሆን ይችላል ተብሏል።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

የት ቦታ እንዳለ በትክክል ባይታወቅም ደቡብ ማዕከላዊ እስያ ውስጥ ይገኛል ተብሏል። ስለዚህም አሜሪካ ያለበትን ትክክለኛ ቦታ ለሚናገር ሰው 1 ሚሊዮን ዶላር እሰጣለሁ ብላለች።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *