በአዲስ አበባ ከ1ሺህ በላይ ህገ ወጥ አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጄንሲዎች እገዳ እንደተጣለባቸው የከተማ አስተዳደሩ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው ህጋዊ አሰራርን ተከትለዉ የሚሰሩ የአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች 315 መሆናቸውን ቢሮው አመልክቷል፡፡

ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸዉ ማስታወቂያ በመለጠፍና ህጋዊ በማስመሰል ሲንቀሰቃሱ የነበሩ በከ1ሺህ ስድስት ኤጄንሲዎች ላይ በጥናት በመለየት እርምጃ እንደተወሰደ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ ተናግረዋል፡፡

ቢሮ ባደረገው የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች ህገወጥ ኤጄንሲዎችን የማሸግ ስራ እየተከናወነ መሆኑም አመልክቷል፡፡

አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጄንሲዎች ተቀጣሪውን ከቀጣሪዉ ጋር በሚያገናኙበት ወቅት የአገልግሎት ክፍያን ወይም ኮሚሽን መቀበል ያለባቸዉ በህጉ መሰረት ከቀጣሪዉ ሆኖ እያለ ከተቀጣሪ የሚወሰዱት ክፍያ ግን ህገ ወጥ ድርጊት መሆኑን ቢሮው ገልጿል፡፡

ተቀጣሪዎችም ከኤጄንሲዎች ክፍያ በሚጠየቁበት ወቅት ለህግ አስከባሪ አካላትና ለቢሮው በመጠቆም እርምጃ እንዲወሰድበት ማስደረግ እንደሚችሉም ተጠቁሟል፡፡

የአገር ውስጥ ስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ህጋዊ በሆነ መንገድ መስራታቸው በርካታ የሰራ እድል ይፈጥራሉ ያለው ቢሮው፣ በአንፃሩ ግን ህጋዊ ፈቃድና አሰራር ሳይከተሉ የሚሰሩ ኤጀንሲዎች በመኖራቸው ተቀጣሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡

ቢሮው የሰራተኞችን የስራ ላይ ደህንነት ለማስጠበቅ እንዲቻል ያሉትን ባለሙያዎች በመመደብ ቁጥጥር ማድረጉን እንደሚቀጥልም ኣስተውቋል፡፡

AA EPRDF official

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *