አቶ ገዱ አንዳርጋቸዉበቅድሚያ በጋንግሪን የጎጥ በሸታ የታመመዉን የአማራ ክልል ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ በቶሎ እንድትታደጉት ጥሪየን እያስተላለፍኩ በሽታው ወደ ከተሞች እንዳይዛመትና ለበሽታው መጥናት መንስዔ የሆኑትን ጉዳዮች ከዚህ በታች በዝርዝር እገልጻለሁ፡፡

ቢሮው ቀደም ሲል በበላይነት በምትመራው ገነት ገ/እግዚአብሔር ገ/እየሱስ በምትባል የወያኔ ተላላኪ የተጠነሰሰ በሽታ እንደሆነ ቢታወቅም ዛሬም የበሽታው ቁስል በየዕለቱ እየመረቀዘ ወደ ጋንግሪን በመቀየሩ በሽታው ወደሌሎች ተቋማት ሳይዛመት እንዲወገድ በሚል ነው ጦማሬን ያነሳሁት፡፡

የተቋሙን የጋንግሪን ጎጥ በሽታ ለማከም የክልሉ መንግስትና አዴፓ በዕቅፉ ያዘላቸውን ዘልዛላ ኃላፊዎችን አስናቀ ይርጉን እና ሷሊህ አቡ በአስቸኳይ ከም/ቢሮ ኃላፊነት ማንሳት ይኖርበታል፡፡ የክልሉ የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ተግባር እንዴት ወደቀ? ምላሹ በተቋሙ የተፈጠረው ስርዓት አልበኝነትና ጋጥ ወጥነት እንደሆነ ማንም የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡

የክልሉ ከተሞች ዕጣ ፈንታ ከላይ በተገለጹት ኃላፊዎች እጅ በመውደቁ በከተሞች እየተስተዋለ ያለው ችግር የክልሉ መልካም አስተዳደር ችግር እየሆነ ከመጣ ውሎ አድሯል፡፡

የዚህ ሁሉ በሽታ መነሻ በተቋሙ ውስጥ በም/ቢሮ ኃላፊነት የተመደቡ ደካማ አመራሮች (አስናቀ ይርጉና ሷህሊ አቡ) እና ከዓመት በፊት በተካሄደው የሰው ኃይል ሕገ ወጥ ስምሪት እንደሆነ በግልጽ ማሳየት ይቻላል፡፡ በአዲሱ የስራ ምዘና ደረጃ አወሳሰን ጥናት (JEG) በሚል ሰበብ ከሠራተኛ ድልድል መመሪያ ውጭ የትምህርት ዝግጅትና አገልግሎት የሌላቸውን በስመ የምስራቅ ጎጃም ዞን በተለይ የሁለት እጁ እነሴ የሞጣ ተወላጅ የሆኑት ሠራተኞች በየሥራ ክፍሉ በዳይሬክተትነት /የሥራ አመራር ከሚቴ/ በማይመጥናቸዉ የሥራ መደብ በኃላፊነት በመመደባቸውና በማሰራታቸው ነዉ፡፡ ይህ ሲባል አዲሱን የስራ ምዘና ደረጃ አወሳሰን ጥናት መሰፈርት የሚያሟሉ ቢሆን ኑሮ እንኳ ከአንድ ወረዳ አይደለም ከአንድ ቤተሰብ ቢመረጡ ቅሬታ የለንም፡፡ ነገር ግን  ግለሰቦችን በአዲሱ የስራ ምዘና ደረጃ አወሳሰን ጥናት በደልዳይ ኮሚቴነት በመመደብ መስፈርቱን ሳያሟሉ የድልድል ምደባ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ሙሉ መረጃዉን ጀባ ልበላችሁ፡-

  1. የጽዳት ውበትና አረንጓዴ ልማትና ፕላን አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት

በዚህ የሥራ ክፍል ከአዲሱ የስራ ምዘና ደረጃ አወሳሰን ጥናት በፊት ተመድቦ ይሰራ የነበረዉ የሞጣዉ ተወላጅ አወቀ ሙኔ ይባላል፡፡ ይህ ግለሰብ ወደቢሮው ከመምጣቱ በፊት የሞጣ ከተማ አስተዳደር የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት በሥራ አስኪያጅነት ተመድቦ ሕዝቡን ሲያገለግል ሳይሆን በሕዝቡ ሲገለገልና በከፍተኛ ሙስና ላይ በመዘፈቁ የክልሉ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በከተማው ባካሄደው የከተሞች መድረክ የሕዝብ ውይይት ተገምግሞ መድረኩ ሳይጠናቀቅ ወደ ባህር ዳር ከተማ እንዲመጣ ተደርጎ በቀድሞው የቢሮው ኃላፊ በነበረችው ገነት ገ/እግዚአብሔርና በአስናቀ ይርጉ ተባባሪነት ያለምንም የሰው ኃይል ስምሪት በቀጥታ የሥራ ክፍሉን እንዲመራ ምደባ ተድርጓል፡፡

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

በዚህ አሰራራቸው ጉዳዩ ክልል ድረስ በመድረሱ በአንድ ወቅት የቀድሞው ብአዴን የአሁኑ አዴፓ ባካሄደው የድርጅት ጉባዔ በቀድሞው የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳዳሪ የነበሩና በአሁኑ የአዴፓ ማዕከላዊ ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ ምግባሩ ከበደ ሀሳቡ ተነስቶ ገነት ገ/እግዚአብሔር እንተገመመገመችና በአዲሱ የስራ ምዘና ደረጃ አወሳሰን ጥናት መሠረት ዘርፉ በፕላነር እንዲመራ በማስገደዱ ግለሰቡ ተነስቶ ነበር፡፡

ማንም እንደሚያውቀውና ጥናቱ እንደሚያመለክተው የሥራ ክፍሉ በፕላነር መመራት እንዳለበት በግልጽ በማስቀመጡ ወ/ሮ አስቴር ዘመነ የተባለች የመጀመሪያ ዲግሪዋም ሆነ ሁለተኛ ዲግሪዋ ፕላነር የሆነ በመላ ሃገሪቱ በፕላር ዲገሪና ማስተርስ ካለቸዉ በጣት ከሚቆጠሩት ሴቶች መካከል አንዷ የሆነችሁ ተወክላ እንድትሰራ ተመደበች፡፡ ምደባውን ተቀብላ እየመራች ባለበት ሁኔታ አገልግሎቷ ስለሞላ የደረጃ ዕድገት እንዲወጣለት በመጠየቅ ላይ እንዳለች ቀደም ሲል የፕላነር የትምህርት ዝግጅት ዘርፉ የማይፍልገዉንና አያሰፈልግም ተብሎ እንዲለቅ የተደረገዉን  አወቀ ሙኔ ተወክሎ ስራዉን በግብር ይዉጣ እንዲመራዉ እየተደረገ ነዉ፡፡ ይህ ዘርፍ በዉክልና ትምህርት ዝግጅቱ በማይፈለገዉ ዘርፍ የክልሉ ከተሞች ዕጣ ፈንታ አደጋ ላይ እየወደቀ ስለሆነ እባካችሁ አንድ በሉን፡፡

  1. የሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

ይህ የሥራ ክፍል በክልሉ ያሉ የከተማ ነክ ጉዳዮችን ለመተግበር ህጎችን በማዉጣትና በአፈጻጸም የሚታዩ ጉድለቶችን እየተከታተለ ሕጋዊ የማድረግና አላሰሩ ያሉ ሕጎችን በመከለስ ከህግ አንጻር ኃላፊዎችን በቅርበት የሚያማክር ዘርፍ ነዉ፡፡ ነገር ግን ክፍሉን በዉክልና እንዲመራ የተመደበዉ በቢሮው የአዲሱ የስራ ምዘና ደረጃ አወሳሰን ጥናት ድልድል በኮሚቴነት ተመድቦ የነበረና የትምህርት ዝግጅቱ በሕግ እንኳን ዲፕሎማ በሕጋዊ መንገድ  ሳያሲዝ በጋጠ ወጥነትና ለኃላፊ የመላላክ ሥራ በመስራት የተሠማራው የሞጣዉ ተወላጅ ሰለሞን መሰለ በምደባ ቦታውን እንዲይዘው ተደርጓል፡፡ ከግል ፋይሉ የተገኘው ማስረጃ በደብረ ማርቆስ ከተማ በ1980ቹ መጨረሻ ዋሸራ ኮሌጅ ተብሎ ከሚጠራውና በትምህርት ሚኒስቴር ቅድመ ዕውቅና ሳያገኝ ዳብዛው ከጠፋው ኮሌጅ አገኘሁት ከሚለው የትምህርት ማስረጃ ውጭ ምንም ዓይነት የትምህርት ዝግጅት የሌለው ግለሰብ ነው፡፡ በዚህ ሸፍጡ በቢፒአር ጥናት ከነበረበት ምስራቅ ጎጃም ዞን ተወክሎ ከቢሮው ጥናት ሲያካሂድ ቆይቶ ዲግሪ አለኝ ብሎ ቀደም ሲል ተቋሙን ሲመሩ የነበሩትንና ሀኡን በአምባሰደርነት የተሸሙትን አምባሰደር ያለው አባተን በማጭበርበር መመደቡ ይታወቃል፡፡

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

ግለሰቡ ዲግሪ እተማርኩ ነው በቅርቡ አጠናቅቃለሁ በሚል ለገነት ገ/እግዚአብሔር  በማውራት፡፡ ካስወራም ከ10 አመት በላይ ሆኖታል፡፡ነገር ግን ያቀርበዉ ዋሸራ የግል ኮለጅ ከሚባል ተቋም ዲፕሎማ ሰጠናዋል የሚል ነዉ፡፡ በዲፕሎማዉም አንተማመንበትም፡፡ ከሰዉ ኃይል የሰራ ሂደቶች ጋር ሰለሚግባብ ሸፋፍነዉለት እንጅ ዲፕሎማዉም በወጉ የሚያሟላ አይደለም፡፡ ነገር ግን በቢሮ ወስጥ በህግ ዲግሪና ማስተርስ ያላቸዉ ሠራተኞች እያሉና በቋሚነት መመደብ እየተቻለ የሞጣ ተወላጅ ስላልሆኑ ብቻ ተከልክለዉ ምንም በማይሟላዉ በሞጣዉ ተወላጅ  ሰለሞን መሰለ የስራ ክፍሉ እንዲመራ ተደርጓል፡፡ ስራዉም እየተሰራ ሳይሆን ሰራዉ እተሞተና አየተሟሟተ ይገኛል፡፡

  1. የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዳይሬክቶሬት

የሥራ ክፍሉን በብቃት ስተመራ የነበረችዉን መሃንዲስ ወ/ሮ ፍሬህይወት በሪሁን መደቡን አሟልታ ደረጃ እድገት ሲወጣላት ሌሎች መስፈርቱን የሚያሟሉት እርሷ ስትደክምበት የቆየች ስለሆነች አንወዳደርም በሚል የሚመዘገብ ሲጠፋ ከሞጣ ሰው ተፈልጎ ባምላኩ የተባለ ግለሰብ ከምስራቅ ጎጃም ዞን ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን መምሪያ መጥቶ እንዲመዘገብና በአስናቀ ይርጉ ፈተና እንዲወጣ ተደርጎ ከአመራር በሚሰጠዉ ነጥብ የሥራ ክፍሉን ከአምስት ዓመታት በላይ በውክልና ስትመራ የነበረችው ባለሙያ እያለች ለሞጣዉ ተወላጅ አብልጫ ነጥብ ተሰጥቶት እንዲመደብ ሲደርግ ክስ ተመስርቶበት የደረጃ ዕድገቱ ሲታገድ ሞራሉ ተነካ በሚል የምስራቅ ጎጃም ዞን ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን መምሪያ መምሪያ ኃላፊ ሆኖ እንዲመደብ ተሯጠዉ ካስመደቡት በኋላ ወ/ሮ ፍሬህይወት በሪሁን የተባለችው ባለሙያ በአዲሱ የስራ ምዘና ደረጃ አወሳሰን ጥናት ድልድል ያለማንም ተወዳዳሪ በብቸኝነት የሥራ ክፍሉን በዳይሬክተርነት እየመራች ያለች ቢሆንም በደካማውና በሞጠኛዉ አለቃዋ አስናቀ ይርጉ  ደካማ አመራር ዘርፉን ማሳደግ እንዳልተቻለና የሕንጻ አዋጁን መተግበር እንተሳናት እንዲሁም የሞጦችን ትዕዛዝ እንድትፈጽም ስለምትገደድ ሰራዉ አደጋ ላይ ነዉ፡፡

  1. የከተሞች መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

በአዲሱ የስራ ምዘና ደረጃ አወሳሰን ጥናት ድልድል በዚህ ዳይሬክቶሬት በትምህርት ዝግጅትም ሆነ በስራ ልምድ በግልጽ የተቀመጠዉ መስፈርት የሚያሟሉና ለበርካታ ዓመታት ሥራውን ሲመሩ የነበሩት ባለሙያዎች በተለያየ ምክንያት ከውድድር በማስወጣት ተፈላጊውንና ዝቅተኛ የትምህርት ዝግጅት የማያሟላ፣ በቢሮው ቆይታ የተመደበበትን ሙያ ከመፈጸም ይልቅ በኮሚቴ ሥራ ከኃላፊዎች እግር ሥር የማይወጣው ደከማውና በቆየባቸው ቢሮች በድክመት የተባረረ የሞጣዉ ተወላጅ አይናለም በለጠ እንዲመደብ ተደረጓል፡፡ በዚህ ምደባ ቢሮዉ ብቻ ሳይሆን በለሌሎች ተቋማት ትዝብት ላይ ተቋሙ ወድቋል፡፡

  1. ግዥ፣ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

በዚህ ዳይሬክቶሬት በተደረገ ምደባ እመቤት የምትባል የአስናቀ ይርጉ ተላላኪ በከፊል ምስራቅ ጎጃም ዞን የሆነች ዳይሬክቶሬቱን እንድትመራ ለአለቆቿ ከደንብና ከመመሪያ ውጭ ግዥና ክፍያ እየፈጸመች ያለች ደካማ ሠራተኛ መሆኗ ይታወቃል፡፡

ለዚህ ሁሉ የተቋሙ ብልሽትና አደጋ ላይ መውደቅ ዋና ተጠያቂዎች የቢሮዉ ም/ኃላፊዎች የሞጣዉ ተወላጅ አስናቀ ይርጉ እና በደካማ አመራሩ የሚታወቀው ም/ቢሮ ኃላፊ ሷሊህ አቡ ተጋሪነት ነዉ፡፡

የሻጥር አፈጻጸም ስልታቸዉም

1ኛ. በአዲሱ የስራ ምዘና ደረጃ አወሳሰን ጥናት ድልድል አብዛኛው የሞጣ ተወላጆችን በኮሚቴነት በመመደብ ሲሆን የኮሚቴዉ ሰበሳቢ በሞጣዉ ተወላጅ  አይናለም በለጠ በአባልነትም በሞጣዉ ተወላጅ ሰለሞን መሰለ እና ሌሎችም ተመድበዉ እንዲሰሩ ማደረግ

2ኛ. በዉክልና በተያዘዉ መደብ ላይ ቅጥርም ሆነ ደረጃ እድገት እንዳይወጣበት ማድረግና
3ኛ.ማኔጅመንት ስብሰባ ላይ ቢሮ ኃላፊዎችን ለማሰማን በቅድሚያ ሁለቱ ምክትል ኃላፊዎች ተመካከረዉና ተደራጅተዉ መግባት ነዉ፡፡

የሞጣ ተወላጅ ስንል ሞጣዎች ቅር እንዳትሰኙ ይልቁንም እንዲህ አይነት ወራዳ ስራ የሚሰሩትን ጠባቦች እንደሃገር እንዲያስቡና በሰማችሁ እየነገዱ ስለሆነ እነ አስናቀ ይርጉን ታግላችሁ አስተካክሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ተቋሙን የሚመሩት አቶ ፈንታ ደጀን የአስናቀ ይርጉና የሷህሊ አቡ ደካማ አመራር ለሚመሩት ተቋም አደጋና ለሚመረሯቸው ከተሞች የቅሬታ ምንጭ ስለሆነ ሴራቸውን በቅርበት ተከታትለው ያስተካክሉ አለበለዚያ ከኑግ ጋር የተገኘ ሲሊጥ….. እንዳይሆን፡፡

በተጨማሪም የተከበሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸዉና የአዴፓ ማዕከላዊ ጽ/ቤትም ለጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት የተቋሙን አደረጃጀትና የሰው ኃይል ስምሪቱ የሚስተካከልበት መንገድ እንትፈልጉልንና አስናቀ ይርጉንና  ሷሊህ አቡ በአስቸኳይ ከም/ቢሮ ኃላፊነት እንድታነሱልኝ በሠራተኛው ስም ከአደራ ጭምር አቤቱታየን አቀርባለሁ፡፡
ከሰላምታ ጋር

Satenaw

Share and Enjoy !

Shares

2 Comments

  1. የቀረበዉ ሃሳብ በሙሉ ዉሸት ይሆናል ብየ ባልከራከርም አገላለጹ ግን የአንድን አካባቢ ስም እየጠሩ ማህበረሰቡን በጅምላ ፈርጆ መልካም እሴቱን ለማንቋሸሽ የሄድከበት መንገድ የዛጎል ኒዉስን የሚመጥን አይደለም፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ ከምከታተላቸዉ ድህረ ገጽ ጋዜጣዎች መካከል ቀዳሚዋ ናት፡፡ የምታቅርቡት ሃሳብ ጠቃሚዎች ናቸዉ፡፡ ነገር ግን ሰሞኑን የአማራ ክልል ስራና ከተማ ልማት ቢሮ የሚሰራዉን ችግር ኮነን ብላችሁ በጋዜጣዋ የወጣዉ ጽሁፍ ጸረ-ህዝብ ነዉ፡፡ በአሁኑ ወቀት የመንግስት አሰራር ተቋማትን በፖለቲካ ድርጅቶችና በተሿሚዎች የሚመሩበት ስርዓት ነዉ ያለ ፡ ክልሉን የሚመራዉ ድርጅት ብአዴን እና ከየትም ለቃቅሞ የሚያመጣቸዉ ድኩማን አመራሮቹ በሚፈጥሩት ችግር መሪዎች የተወለዱበት አካባቢ ስም እየተጠራ በአካባቢዉ የሚኖረዉ ማህበረሰብ የችግር ፈጣሪዎችን ሃጺያት እንዲሸከም ታልጋ የሚለጠፍበት ፣ በወል የሚንቋሸሽበት የመንጋ ፍርድ ተቀባይነት የለዉም ፡፡ ጸሃፊዉ ግልጽ የስብዕና ብሰለት ማነስ ታይበታል፡፡ እንዲዉም በእኔ እምነት ጽሁፉን ያቀረበዉ ሰዉ ችግሩን ፈጠሩ ብሎ ከሚከሳቸዉ ሰዎች በምንም አይለይ፡፡እሱም ያዉ ነዉ፡፡ ስለዚህ ዛጎል ኒዉስ መሰረቴ ህዝብ ነዉ ብለህ ከተነሳህ ከእንዲህ አይነቱ አጻጻፍ እንድትቆጠቡ እመክራለሁ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *