እስከመቼ ሕዝብ በአገሩ ላይ ባይታዋር ይሆናል?

ከሐረር የሚሰማው ያስደነግጣል።ጊዜው ፈቅዱዋል የሚሉ ለዜጎች በሰላም መኖር እንቅፋት ሆነዋል።ይህንን የሚያስቆም የአካባቢ ሆነ የክልል አስተዳደ የለም።ጠቅላይ ሚንስትሩ ደግሞ እንኳን ሐረር ከቤተ መንግስቱ ሩቅ ያልሆነውን የለገጣፎን መፈናቀል አልሰማሁም ብለዋል።የሐረርን ጩኸት ይሰማ?እዛም የዲሞግራፊ ፖለቲካዊ ይሆን? ሕዝብ ከመፈናቀሉ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት የባለስልጣኑን ተከለ ሰውነት ለመገንባት የምትራወጡ እና ሕዝብ ተበደለ ሲባል ለውጡ እንዳይቀለበስ በሚል አጀንዳ ፍለጋ ከምትደክሙ የሐረር ሕዝብ ጩኸትና ፊቱ የተጋረጠበት ችግር ይፈታ።ከሰሙዋችሁ ንገሩዋቸው ።

ተከታዩን የሐረር ሕዝብ ጩኸት ያንብቡ ያሰራጩት

.- ሐረር

ከእሁድ ምሽት ጀምሮ የሀረር ህዝብ በተለይ የቀበሌ 16 ህዝብ ውጪ እያደረ ነው፡፡ አስቡት እስቲ ለዘመናት የኖረበት፤ ልጆቹን ያፈራበት መኖሪያ ቤቱ እንዳይፈርስ ልጆቹን፣ ሚስቱን ትቶ ለሊቱን ሙሉ ውጪ በዝናብና በውርጭ እየተቀጠቀጠ ቤቱ እንዳይፈርስበት ሲጠብቅ፡፡ ቤት የቀሩትን የህፃናቱን፤ የእናቱን እና የሚስቱን ፍርሀትና ጭንቀት አስቡት እስቲ!

.

ይኸው ለሁለት ተከታታይ ለሊቶች የቀበሌ 16 አባቶች፣ ጎልማሶችና ወጣቶች ቤታቸውን በጋራ ለመጠበቅ ውጪ እያደሩ ነው፡፡ ህጋዊ መሆናቸውን የሚያሳይ ካርታ ይዘው ‘አቤት’ ቢሉም የሚሠማቸው አልተገኘም፡፡ ትላንት ለሊት እንዳውም እነዛ አጉራ ዘለል አፍራሾች ጋር ተፋጠው ነበር ያደሩት፡፡

.

እውን መንግስት ከዚህ በላይ ምን እስኪፈጠር ነው የሚጠብቀው? ተጨባጬና ዘላቂው መፍትሔስ መለስተኛ ክሊኒክ በሚሠራ በጀት አፅም ማዞር ነው?! (FYI አፅሟ ሀረር የገባች ቀን ነው ማፍረሡ የተጀመረው፡፡)

.

የዚህች ሀገር መሪስ በዚህ ሠዓት አጎራባች ሀገራት አጣዳፊ በሆነ ጦርነት ውስጥ እስካልሆኑ ድረስ ፖለቲከኞች First Things First እንደሚሉት መሪውም የጎረቤት ሀገሮች ነገር ላይ ከማተኮር ይልቅ መጀመሪያ ይህ ሠውን በገዛ ሀገሩ ላይ ባይተዋርና ባዳ አድርጎ ከባድ ቂምን ለሚያስቋጥረው ከቦታ ቦታ እንደወረርሽ እየተከሠተ ላለው አፀያፊ ችግር የማያዳግም መፍትሔ ማበጀቱ አይቀድምም?! ቆይ ምን እስኪፈጠር ነው የሚጠበቀው?! እስከመቼስ???

.

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ ፈጣሪ ከናንተ ጋር ይሁን! መፀሀፉም እንደሚለው “ንብረታችሁንና ቅጥራችሁን ነቅታችሁ ጠብቁ፡፡ የሠውም አትንኩ!”

#ፍርድያውቃልንጉሴ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *