በኖርዌይ የስደተኝነት ጥያቄ አቅርባችሁ ጉዳያችሁ ተይቶ የጠበቃችሁትን ሰይሆን አሉታዊ ምላሽ ተስጥቶኣችሁ ጉዳዬ በፍትሓዊ መልኩ አልታየም፣ ወይንም የስደተኝነት ጉዳይ አፈጻጻም ብዙ ግዜ ከመፍጀቱና እዚህ አገር ብዙ ከመቆየቴ የተነሳ ወደ ፊት ኑሮዬን ወደ ኢትዮጵያ ተመልሼ ለመቀጠል እቸገራለሁ ወይንም ለህይወቴ ስለሚሰጋ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አልችልም በሚሉ ምክንያቶች ከኖርዌይ መንግስት ጋር በጭቅጭቅ ያለችሁ ወገኖቻችን ሰሞኑን የኖርዌይ መንግስት መልስ ያለገኙ ስደት ጠያቂ ኢትዮጵያዊያንን አስገድዶ ለመመልስ የሚቻል ስምምነት ተፈራርመዋል የሚል ወሬ በዜና አውታሮች ስሰራጭ ሰንብቷል።

ኢትዮጵያናየኖርዌይ መንግስት መልስ ያለገኙ ስደት ጠያቂ ኢትዮጵያዊያንን አስገድዶ ለመመለስ የሚቻል ስምምነት ከዚህ በፊት ተፈራርመው ነበር (2012)። ስምምነቱንና ያስገኘዉን ውጤት በተመለከተም ብዙ ጥናቶች ተከሂዶ ስደት ጠያቂ ኢትዮጵያዊያንን አስገድዶ መመለስ ውስብስብና አስቸጋሪ እንደሆነ ታይቷል።
በመሰረቱ ሀገራችን ኢትዮጲያ በአህጉራዊውም ሆነ አለም አቀፈ የስደተኞች ችግር ለማቃለል እየሰሩ ካሉና ቀዳሚ ሚና ከሚጫወቱ ሀግሮች አንዷ ናት። በቅርቡም የሀገሪቱን የስደተኞች ህግ በማሻሻል በሀገሪኛዉ እይታ አከራከሪ ቢሆንም ለብዙ ሀገሮች ሚሳሌ የሚሆን ውሳኔ ወስዳለች።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ነገር ግን ሀገራችን ኢትዮጲያ ከፈረመቻቸዉ አህጉራዊውም ሆነ አለም አቀፈዊ የስደተኞች ውሎች አንጻር ፣በውጪ ሀገሮች የስደት ጥያቄ አቅርበው ጥያቄያቸው አዎንታዊ ምላሽ ያለገኛ ዜጎችዋን የመቀበል ግዴታ አለባት።
በአንጻሩም ደግሞ የሀገራችን ህገመንግስት የዜግነት መብቶችና ሌሎች ሰብዓዊናዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚያካትት በመሆኑ መንኛዉም ሰው ያለፈቃዱናኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ተገዶ እንድመጣ የኢትዮጲያ መንግስት ይደግፋል ብዬ አላምንም።

በኖርዌይና በአውሮፓ መንግስታት በኩል ከስደት ተማላሾችን ቁጥር በማብዛት የስደትኝነትን ችግር እንፈታለን በሚል የተሳሳተ እሳቤ በስልጣን ለይ ያሉ እንዳንድ ስደተኛ የሚቃወሙ ፓርቲዎች የተቻለቸዉን እያደረጉ ነው። ምንም እንኳን የእያንዳንዱ ስደት ጠያቂ ጉዳይ የግለሰብ መሆኑን ብታወቅም በስልጣን ለይ ያለውና በተለይም የፍትሕ ሚንስተርን የሚያስተዳድረው ፓርቲ ኢትዮጵያዊያንን በድፍኑ ለመመለስ ፍላጎት አለው።
• ስለሆነም በምትሰሙት ወሬዎች ሰትሸበሩ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደው የአቋም ለውጥ ካለ ለማጣራት ብትሞክሩ፣
• ባልተሰበና ድንገተኛ በሆነ የመያዝና በግዳጅ ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ ሁኔታ ልገጥም ስለሚችል ሁል ግዜ በየትኛዉም ቦታና ሁኔታ መብታችሁን የመወቅ፣ እርዳታ የሚታገኙበትን ቦታዎች መወቅ፣ ቢያንስ በሀሳብ ዝግጁ ሆኖ መጠበቅ ይመከራል። (https://www.nhri.no/veiledn…/rettshjelpstiltak-og-frivillige /)
• ይህን ለማለት የፈልግኩት እንድትረበሹ፣ ስጋት እንድገባችሁ ሰይሆን ቅደመ ዝግጅትና ዕውቀት እንዲኖራችሁ ነው።
• ከዚህ በፊት ተቋቁማው የነበሩትን መህበሮችንና ግንኙነቶችን ማጠናክር ያስፈልጋል። አንዱ ሰው በችግር ከወደቀ ቶሎ መረጃ በመለዋወጥ መረዳዳት።
• በመጨረሻም ስደት መጠየቅ እንደነዉር እየታየ ብዙ የእዕምሮ ሽክም፣ ምስጢርና ብቻነት ውስጥ ያለችሁ ህልማችሁ ሰይሆን መከራ የገጠማችሁ ሁሉ በያላችሁበት ተስፋ እንዳትቆርጡ ራሰችሁን ከሚገባው በላይ እንዳታስጨንቁ እያልኩ
• ከዚህ ተመልሶ ኑሮ የመገንባት የቤተሰብና የእኮኖሚ አቅም ያለችሁም የስደት ተመላሾች ድጋፍ ወሰዳችሁ እንድተመለሱ እመክራለሁ። መመለስ አልችልም ጉዳዬ ፍትሓዊ እልባት አለገኘም የምትሉም በትዕግስትና በተጋጋዝ እንድትጋፈጡ እመክራለሁ።
እኔ በበኩሌ እየተከታተልኩ የጉዳዩን አሳሳቢነት ለሌሎች ለማሰወቅ እየሞክርኩ ነው። ለሚመለክተው አካል ዳብዳቤም ጽፌአለሁ። ዳብዳቤው ተገቢው ቦታ መድረሱን ግን እርግጠኛ አይደለሁም። መረጃ በማቀበል ለማገዝ ብዬ ነው ይህን የጻፍኩት።
እንተሳሳብ። እንረዳዳ።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

ለማ ደስታ
ለኖርዌይና ለአውሮፓ ቤተክርስቲያናት የስደትና የፍልሰት ጉዳዮች አማካሪ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *