በግጭቱም 5 ታራሚዎች ከመሞታቸውም በላይ በውል ቁጥራቸው ያልታወቁ ታራሚዎች ተጎድተው ሕክምና ተደርጎላቸው እየተመለሱ ነው፡፡ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ በተደረገው ፍተሻም 20 ሞባይል ስልኮች፣ ቢላዋ፣ ጩቤ፣ ገጀራ፣ አካፋና ዶማ እንዲሁም ለማቀጣጠያነት የሚያገለግል ‹ላይተር›፣ አሲድና ሀሺሽ ተገኝተዋል፡

ትናንት በግምት ከቀኑ 7-8፡00 ባለው ጊዜ በባሕር ዳር ማረሚያ ቤት ግጭት መቀስቀሱና የ4 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ቀደም ብለን ዘግበን ነበር፡፡ ዘግይቶ በደረሰን መረጃ ደግሞ በግጭቱ የሟቾች ቁጥር 5 ደርሷል፤ የሟቾች አስከሬንም ለቤተሰቦቻቸው ተሰጥቷል፡፡ በሌላ በኩል አንድ የፖሊስ አባል እስካሁን አልተገኘም፡፡ የተንቀሳቃሽ ስልኩ ማረሚያ ቤቱ ውስጥ መገኘቱንና የፖሊስ አባሉ ግን እስካሁን ያለበት ሁኔታና ቦታ አለመታወቁ በማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ኮማንደር ውብሸት መኮንን ተገልጿል፡፡

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ለግጭቱ መነሻ የሆነው የማረሚያ ቤቱን የፍተሻ ሥርዓት አለመዘመን በመጠቀም ያልተፈቀዱ ቁሳቁሶች መግባታቸውን ጥቆማ ደርሶ ለመፈተሽ በመሞከሩ ነው፡፡ በጥቆማው መሠረት 6 ፖሊሶች ለፍተሻ ሲገቡ በታራሚዎች ለማፈን ሙከራ ተደረጎባቸዋል፤ ጉዳትም ደርሶባቸዋል፡፡

ግጭቱ እንደተጀመረ አካባቢ የተወሰኑ ታራሚዎች ፖሊሶችን ለማገዝ ቢሞክሩም በሂደት ግን     ወደለየለት ግጭት ተገብቶ ከፍተኛ የድንጋይ ውርወራ መቀጠሉን ነው ኮማንደሩ ለአብመድ የገለጹት፡፡

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

በግጭቱም 5 ታራሚዎች ከመሞታቸውም በላይ በውል ቁጥራቸው ያልታወቁ ታራሚዎች ተጎድተው ሕክምና ተደርጎላቸው እየተመለሱ ነው፡፡ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ በተደረገው ፍተሻም 20 ሞባይል ስልኮች፣ ቢላዋ፣ ጩቤ፣ ገጀራ፣ አካፋና ዶማ እንዲሁም ለማቀጣጠያነት የሚያገለግል ‹ላይተር›፣ አሲድና ሀሺሽ ተገኝተዋል፡፡

በግጭቱ እየተጎዱ ያሉት ንጹኃን መሆናቸውን ያስታወቀው መምሪያው የግጭቱን ጠንሳሾች ገና መለዬት አለመቻሉን አስታውቋል፡፡

የታራሚዎች ቤተሰቦች ስጋት እንዳይገባቸው የሟቾችን አስከሬን በፍጥነት ለቤተሰብ ማስረከቡንም መምሪያው አስታውቋል፡፡

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

ዘጋቢ፡- አለምነህ አዛናው – (አብመድ)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *