“እስከ ሰኔ አዲስ ነገር ይታያል” ሲሉ ይጀምራሉ። አክለውም ” ሰኔ መጨረሻ የኦሮሚያ የትግል ሜዳ ተዋንያኖች ይለያሉ። ሩጫው በዚህ የትግል ሜዳ ውስጥ የሚሳተፉትን ወገኖች አንጥሮ ለማውጣት ነው። ከአንድ ወገን የጨዋታው ስልት አንጋፋ የኦሮሞ የትግል ሰዎችን ከፉክክሩና ከመሪነቱ አምድ ላይ ማስወገድ ነው”

አባ ቃሉ በኦሮሞ ትግል ዙሪያ ያውቁታል። ከዛጎል ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት ኦዴፓ ኦነግ ሸኔ ሲቀር ከሌሎቹ የኦነግ ደርጅቶች ጋር ለመዋሃድ ከግማሽ መንገድ በላይ ከሄደ በሁዋላ በሰነድ አስደግፎ ስምምነቱን አላማጽደቁ በኦነግ ድርጅቶች ዘንድ ቅሬታ አስነስቷል። ለመቀላቀል ሂደት ላይ ካሉት የኦነግ ድርጅቶች ኦዴፓ አንዳንድ የድርጅቱ ከፈተኛ አመራሮች ቢሾምም ውህደቱን በፊርማ አለማጸደቁ  በጎን ዳውድ የሚመሩት ሸኔ ኦነግ ቀደም ሲል የተለያቸውን ድርጅቶች መልሶ እንዲቀላቀል ለማድረግ ጥረትም እንዲጀመረ አድርጓል።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

አባ ነጋና ጀነራል ከማል ገልቾ የሚመሩት የኦነግ ድርጅቶች ከዳውድ ኢብሳ ጋር ተመልሰው አብረው ለመስራት የሚችሉበት እድል እጅግ ያነሰ መሆኑንን እንደሚያምኑ ያወሱት አባ ቃሉ፣ ቄሮን ፓርቲ አድርጎ ወደ ፊት የመምጣቱ ጉዳይ እስከ ሰኔ ቀውን ይሆናል ብለዋል።

ይህንኑ ሃሳብ በኦሮሞ ሚዲያ ኔት ዎርክ የውይይት መድረክ ቄሮን ፓርቲ የማድረግ ሃሳብ እየቀረበ መሆኑ፣ በቅርቡ ከቪኦኤ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረገው ጃዋር መሐመድ ፣ አሁን ህግ ባለበትና በነጻነት መንቀሳቀስ በሚቻልበት ሁኔታ በህብዕ መስራት ስለማይቻል ቄሮን ድርጅት የማደረግ ሃሳብ እንዳለ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

አባ ቃሉ ሃሳቡ አዲስ አይደለም ካሉ በሁዋል፣ ቄሮ ወደ ፓርቲ እንዲሸጋገር የሚደረገው አንጋፋ የኦሮሞ ታጋዮችን ከመሪነት መንበር የማስወገድ እቅድ ያነገበ መሆኑንን ያሰምሩበታል። ይሁን እንጂ ቄሮን የሚመሩትና ቄሮ ያለው የተለያዩ አደረጃጀቶችን የሚመሩዋቸው አካላት እንዴት ተስማምተው ወደ አንድ ይመጣሉ የሚለው ቀጣዩ ፈተና ነው።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

የኦሮሞ ትግል በሸዋ ተወላጆች ተጠንሥሶ በሂደት በአንድ አካባቢ ሰዎች መጠለፉ ውጤት እንዳያመጣ አድርጎታል የሚል ሃሳብ መኖሩን ያወሱት ኦቦ ቃሉ፣ ቄሮን አስመልክቶ የተሳሳተ ግንዛቤ መኖሩንም ይናገራሉ።

ኦዲፒን ጨምሮ ከሁሉም የኦሮሞ ድርጅቶች ጀርባ የቄሮ አደረጃጀት መኖሩን ያመለከቱት ኦቦ ቃሉ ከሁሉም በላይ ትልቅ ሃይል ያለው የአባ ነጋ ቡድን መሆኑን አበክረው ይናገራሉ። የዚህም ምክንያቱ የሚዲያ ሽፋን ማጣት ነው።

ቄሮ ወደ ፓርቲንት መዛወሩ የሚደገፍ ቢሆንም ኦዴፓ በቅርቡ ውህደቱን ይፋ በማድረግ ይህንን የቄሮ ሃይል ይጠቀልለዋል የሚል እምነት እንዳላቸው ኦቦ ቃሉ አስታወቀዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

እሳቸው ይህንን ቢሉም እስከ ሰኔ ድረስ ቄሮ ፓርቲ ሆኖ በኦሮሚያ እንደ ሰደድ እሳት ይቀጣጠላል የሚል እምነት ያላቸው ብዙ ናቸው። እንዚህ አካልት እንደሚሉት ቄሮን ፓርቲ የሚያደርጉት ክፍሎች አሁንም የመካከለኛው ኦሮሚያ ተወላጆች አለመሆናቸው ጎምጉምታ እያስነሳ ነው። ቄሮን ፓርቲ ለማድረግ የሚሰራው ስራ በእነ ጸጋዬ አራርሳ የሚመራ መሆኑም ተጠቁሟል።በኢትዮጵያ ለውጥ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ የቀደሙት አንጋፋ ታጋዮች እድሜ ከመፍጀት የዘለለ ሚና እንዳልንበራቸው በተደጋጋሚ ሲተች እንደነበር የሚያስታውሱ ክፍሎች ሃሳቡ እውን ሲሆን ውዝግቡ ከባድ እንደሚሆን ከወዲሁ ይጠቁማሉ።

ጃዋር ይህንኑ አስቀድሞ በመግንዘብ ይመስላል ከፊሎቹ ወደ በጎ አድራጎትና የማህበራዊ አገልግሎት ሰጪነት እንደሚዛወሩ ለቪኦኤ ጥቆማ ሰጥቷል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *