) የለውጡን የአንድ ዓመት ጉዞ በተመለከተ ሀገር አቀፍ ሕዝባዊ ውይይት በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የመንግስት አመራሮች፣ ፖለቲከኞች፣ ምሁራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡ ለውጡ ተስፋዎችን እና በአንጻሩ ከፍተኛ ስጋቶችን ይዞ መምጣቱ በውይይቱ ተነስቷል፡፡ ለውጡ ይዟቸው ከመጡት ተስፋዎች መካከል የሕዝቡ የፖለቲካ ንቃት መዳበር፣ የመናገር፣ የመጻፍ እና የመገናኛ ብዙኃን ነጻነት፣ በእስር ላይ የነበሩ ዜጎች መፈታት እና በውጭ የሚገኙ ተፎካካሪ ኃይሎች ወደ ሀገራቸው መግባት ተጠቅሰዋል፡፡

ይሁንና መጠነ ሰፊ ስጋቶች ከለውጡ ጋር አብረው መምጣታቸውም በመድረኩ በስፋት ተነግሯል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግሮችን በባህላዊ እና ማህበራዊ አሴቶቹ አልፏል፤ አሁን ግን የስነ ምግባር አሴቶች አየተሸረሸሩ ለአደገኛ ችግር ተጋልጧል ተብሏል፡፡

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

አመራሩ በተለይ ለውጡን እየመራ ያለው አካል በሕዝቡ ዘንድ እየተሸረሸረ የመጣውን ተአማኒነቱን ማደስ ይጠበቅበታል፤ ከህዝቡ ጋርም ለመግባባት በተጨባጭ የሚታዩ ተግባራትን መስራት ይኖርበታል ነው የተባለው፡፡

የመረጃ እጥረት መኖሩ እና በብርሀን ፍጥነት ነገሮች እየተከናወኑ መሆናቸው የለውጡን ሂደት ለመገመት እና እንዲህ ነው ለማለት አስቸጋሪ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ለሀገራችን እውነቱን ተናግሮ ከመሸበት የሚያድር አመራር በአሁኑ ጊዜ ያስፈልገናል፤ ካልሆነ ሕዝብና መንግስትን ዋጋ እንደሚያስከፍልም ነው ያሳሰቡት፡፡

በሀገራችን ሁለት ሀይሎች ይስተዋላሉ፤ ‹‹ ጽንፈኛ እና ምክንያታዊ፡፡ ጽንፈኛውን በድርድር ወይም በውይይት ወደ ምክንያታዊነት መውሰድ ካልተቻለ ለውጡ ይኮላሻል፡፡ የአመራር ብቃትም የሚለካው በዚህ ነው›› የሚል ማብራሪያም ከተወያዮቹ ቀርቧል፡፡

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በሕዝቡ በተለይ በወጣቱ ዘንድ በሀሳብ የበላይነት አለማመን፣ ስሜታዊነት፣ ችኩልነት፣ በሀሰት መረጃ መታለል እና መረበሽ በችግርነት ቀርበዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከየትኛውም ጊዜ በላይ ሀገራዊ አንድነት፣ መግባባት እና እርቅ የሚያስፈልጋት ጊዜ ላይ መሆኗም ተነግሯል፡፡

ልዩነቶችን ማቻቻል እና በሰከነ መንገድ መወያየት ከችግር ለመውጣት ዋነኛ መፍትሄዎች መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡ በአንዴ ሊመለሱ የማይችሉ ጥያቄዎችን አብዝቶ መጠየቅም ለለውጡ ሌላው ስጋት ሆኖ ነው የቀረበው፡፡

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

በለውጥ መሪዎች ላይ እየተሸረሸረ የመጣውን እምነት ለመመለስ ተጨባጭ ስራዎች መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል የውይይቱ ተሳታፊዎች። የማይፈጸሙ ወይም ለመፈጸም የሚያስቸግሩ ነገሮችን ለሕዝቡ ቃል አለመግባት እና አወዛጋቢ ጉዳዮችንም ወደ ኋላ ማዘግየት ተገቢ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የመንግስት አካላት የሚሰጡት ያልተገባ፣ እርስ በርሱ የሚጋጭ መግለጫ እና የሚይዙት አቋም ሕዝቡን ከማወናበድ አልፎ ለለውጡ ስጋት ነውም ተብሏል፡፡ የለውጡን ኃይሎች ሕዝቡ በምን መልኩ መደገፍ እንዳለበት በግልጽ መቀመጥ አንዳለበትም በተሳታፊዎች ተነስቷል፡፡

ዘጋቢ፦ ቢኒያም መስፍን ባሕር ዳር፡ መጋቢት 25/2011ዓ.ም (አብመድ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *