የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣቸዉ ሲል ራሱን« የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት»ብሎ የሰየመዉ አካል ጠየቀ። ይህ አካል በዛሬዉ ዕለት በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከተዉ ከተማዋ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ አስተዳደር የላትም ብሏል።

የከተማዋን ህዝብ ጥያቄ እንዲመለስ ከመስራት ዉጭ የስልጣንም ይሁን በቀጣዩ ምርጫ የመወዳደር ፍላጎት እንደሌለዉም ገልጿል። ሆኖም ግን የአዲስ አበባ ህዝብን ጥያቄዎች ለመመለስ የሚሰራ የፖለቲካ ፓርቲ ካለ ሊደግፍ እንደሚችል አስታዉቋል። በአሁኑ ወቅት ግን ምንም አይነት የፖለቲካ ፓርቲ ከኋላው ሆኖ ድጋፍ እየሰጠው እንዳልሆነም አመልክቷል፡፡

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

«ባለአደራ ምክር ቤቱ» በቅርቡ አካሂዶት በነበረዉ ስብሰባ ከተስብሳቢው ዉክልና ማግኘቱን ገልጾ በሂደት እስከ እያንዳንዱ ቀበሌ ድረስ በሚዘረጋ መዋቅር እንደሚወከል አመልክቷል።

መግለጫው አያይዞም በአዲስ አበባ ከተማ መታወቂያ በጅምላ መሰጠቱን የሚያሳይ መረጃ እንዳለዉ ጠቅሶ ድርጊቱን ተቃዉሟል። መንግስት በጉዳዩ ላይ በቅርቡ የሰጠዉ መግለጫም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀደመ አቋም ጋር የሚጣረስ ነው ሲል ተችቷል፡፡

ባለአደራ ምክር ቤቱ ባለፈው በአቋም መግለጫ ያስቀመጣቸው ጥያቄዎች በአፋጣኝ እንዲመለሱ ፡ ኢህአዴግ «በአዲስ አበባ ላይ ልዩ ጥቅም ያለው አካል አለ» በሚለው አቋሙ ጸንቶ የሚቀጥል ከሆነ በቀጣዩ ምርጫ በከተማዋ ሊሸነፍ እንደሚችል ሊያውቀው ይገባልም ብሏል መግለጫው፡፡ዘገባዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን የሶሎሞን ሙጨ ነዉ።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

Source – DW

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *