በኢትዮጵያ የተለያዩ የግል ኮሌጆች በአንድ ወርና ሁለት ወር ውስጥ በማስትሬት ዲግሪ የሚያስመርቁ እንደተገኙ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው መድረክ ላይ በትምህርት ጥራት ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ እንደተገለፀው በሃገሪቱ ካሉት 174 ያክል የግል የትምህርት ተቋማት 46 ካምፓሶች ላይ ከፍተኛ ችግር ተገኝቷል።

ህጋዊ ሰነድ አሟልተው አየሰሩ ያሉትም 46 ብቻ እንደሆኑ ነው በመድረኩ የተገለፀው።

በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ብቻ በሚገኙ የግል የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻም ያለ እውቅና ፍቃድ ተማሪ መዝግበው የሚያስተምሩ፣ የርቀት ትምህርት ፍቃድ ወስደው መደበኛ ትምህርት የሚያስተምሩ፣ ሳያሳውቁ የካምፓስ ህንፃ የሚቀይሩ፣ ኮሌጅ የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸው ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ብለው የሚያስተምሩ አንደ ስቴሽነሪ አይነት መለስተኛ የንግድ ፍቃድ ወስደው ኮሌጅ ብለው የሚያስተምሩ እንደተገኙ ነው በመድረኩ ላይ የተገለፀው።

በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ካሉ በ174 ከፍተኛ የግል ትምህርት ተቋማት 43ቱ ብቻ ህጋዊ ሰነድ አሟልተው እንደሚሰሩ ተገልጿል፡፡

በፎርጅድ የንግድ ፈቃድ ተቋም ከፍተው በክልሎች ትምህርት የሚያስተምሩ እንዳሉም ተደርሶበታል፡፡

በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሰረት መንግስት ከዚህ በኋላ ዩኒቨርስቲ የመገንባት እቅድ ስለማይኖረው የግል ባለሃብቱ ያሉበትን ችግሮች በማስተካከል ወደ ህጋዊነት እንዲመጣ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የግሉ ባለሃብቶች ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማሪም ገልፀዋል።

ሪፖርተር፡- ቤተልሄም ጥጋቡ EBC

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *