(በድሉ ዋቅጅራ)

ቴዲ የዛሬን እንጃ እንጂ፣ ኢትዮጵያ በነበርክበት ጊዜ ምክር የምትሰማ ልበ ብሩህ ልጅ ነበርክ፡፡ እንደ ታላቅ ወንድምም፣ እንደ መምድምጠኸኝ ታውቃለህ፡፡ ዛሬም ምክሬን ትሰማለህ ብዬ እገምታለሁ፡፡

ቴዲ፣ እውLlነት ኢትዮጵያን ትወድ እንደሆነ፣ በርእዮት የራዲዮ ፕሮግራም የምታስተላልፈውን አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ እባክህ ተወው፡፡ ቴዲ፣ እዚህ አዲስ አበባ እያለህ በኤፍ.ኤም 97.1 ላይ ፕሮግራም ስትሰራ ትኩረትህ ከፖለቲካ የራቀ፣ አበባና ቢራቢሮ መሰል ጉዳዩች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ በፕሮግራምህ ከእኔም ጋር ስለግጥምና ፊደል አውርተን እናውቃለን፡፡ ውጭም ከሄድክ በኋላ፣ ለውጡ ተቀጣጥሎ ህወሀት ከቤተመንግስት መውጣቱ እርግጠኛ እስኪሆን ድረስ፣ እንደ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ያሉ፣ ምንም ባይሰሩ እንኳን እድሜያቸው ብቻ ሊያስከብራቸው የሚችሉ ሰዎችን እንጂ፣ መሪዎችን አትዘረጥጥም ነበር፡፡ ቲም ለማ ለውጡን ሀ ብሎ ሲጀምር ግን የዘወትር አርእስትህ ለማና አብይ ሆነዋል፡፡

መቼም የማህበረሰባችንን እና የሀገራችንን ውለታ ላንተ መንገር አይገባም፡፡ አቅፎ ደግፎ አሳድጎ ለዚህ አብቅቶሀልና ታውቀዋለህ፡፡ ይሁን እንጂ በ go fund me የገንዘብ መዋጮ ስትጠይቅ ስሰማ፣ የእናትህን ጡት ለመንከስ ምን ያህል ለመሄድ እንደተዘጋጀህ አስቤ ከልቤ አዘንኩ፡፡

ቴዲ፣ በእርግጥ ጥሩ አማርኛ ትችላለህ፤ አማርኛህ የትግራይ ሰው አማርኛ አይመስልም፡፡ ለዚህ አላማህ ብዙ ገንዘብ ልትሰበስብም ትችላለህ፤ ነገር ግን ለውጡን በተመለከተ ምንም ማድረግ አትችልም፡፡ ምክንያቱን ይህ ለውጥ፣ ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከቋንቋ ችሎታና ከገንዘብ በላይ – የህልውና ጉዳይ ነው፡፡

አየህ ቴዲ፣ በ1966 ለውጡ ከሽፎ የደርግ አንባገነን መንግስት 17 አመት ገዛን፡፡ የ1983ም ለውጡ ከሽፎ የህወሀት አንባገነንና ከፋፋይ መንግስት ለ27 አመት ገዛን፡፡ ዛሬ ይህ ለውጥ ቢከሽፍ ሁሉንም አንድ አድርጎ የሚገዛ አንባገነን መንግስት እንኳን አናገኝም፤ የእኛም የሀገራችንም ህልውና ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል፡፡ ይህን እናውቃለንና ከለውጡ መሪዎች ጋር እየተወያየንም ሆነ እየታገልናቸው፣ ፍቃደኛ እስከሆኑና እስከሰሙ ድረስ ሲሳሳቱ እያረምናቸው፣ ይህን ለውጥ ከግብ አድርሰን፣ ለልጆቻችን መልካም ሀገር እናቆያለን፡፡ እና እባክህ ቴዲ ስለማይታየው የልብህ መሻት ማለትም ስለብሄር፣ ስልጣንና ገንዘብ ሳይሆን፣ ለይስሙላ በአፍህ ስለምታሽሞነሙናት ሀገርህ – ስለኢትዮጵያ አስብ፡፡

እንደሁልጊዜው ምክሬን ትሰማለህ ብዬ እገምታለሁ፡፡ ታላቅ ወንድምህና መምህርህ በድሉ ዋቅጅራ፡፡

www.facebook.com/372989976100177/posts/2256609801071509

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *