በአዲስ አበባ ሶስት ክፍለ ከተሞችና በቡራዩ ከተማ በህገ ወጥ መንግድ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ 11 ጌት ዌይ የቴሌኮም ማሽን፣ 14 ቲፕሊንግ ማሽን፣11 ፍላሾችና በርካታ ሲም ካርዶች በቁጥጥ ስር ዋሉ።

ህገ ወጥ የቴሌኮም መሳሪያዎቹ በቁጥጥ ስር የዋሉትም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ፣አቃቤ ህግ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጄንሲ፣የኦሮሚያ ፖሊስና ኢትዮ ቴሌኮም ባካሄዱት የቅንጅት ስራ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ የፋይናንስ ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት መንግስታዊ ያልሆኑ የፋይንስ ተቋማት ዲቪዥን ሃላፊ ኢንስፔክተር ሳሙኤል ሰለሞን ለፋና ብሮድጀካስቲንግ ተናግረዋል

ህገ ወጥ መሳሪያዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉትም በኮልፌ ቀራኒዮ፣ በልደታና በላፍቶ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ እንዲሁም በቡራዩ ከተማ መሆኑ ነው የተገለፀው።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

እነዚህን መሳሪያዎች የቴሌኮም መፍቃድ ሳይኖራቸው በህገ ወጥ መንገድ ከውጭ በማስገባት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ አራት ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኢንስፔክተር ሳሙኤል ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው እየተመረመረ መሆኑን የጠቀሱት ኢንስፔክተሩ በቀጣይም ተመሳሳይ የኦፕሬሽን ስራዎች በሌሎች ቦታዎች የሚከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በቁጥጥ ስር የዋሉት ህገ ወጥ የቴሌኮም መሳሪያዎች የዋጋ ግምት እየተጣራ መሆኑን ኢንስፔክተር ሳሙኤል ገልፀዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በታሪክ አዱ

FBC

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *