የኦዲፒ የምስረታ በዓል በቀጣይ የህዝቡን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለሚደረገው ትግል ራሳችንን የምናዘጋጅበት ነው – አቶ ለማ መገርሳ

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) የ29ኛ ዓመት የምስረታ በዓል

ማጠቃለያ ስነ ስርዓት በአዲስ አበባ በሚሌኒየም አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የማጠቃለያ በዓሉ ላይም የኦዲፒ ምክትል ሊቀመንበርና ኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን እንዲሁም ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

አቶ ለማ መገርሳ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልእከት፥ የዛሬዋ ቀን በኦሮሞ ህዝብ ትግል ውስጥ ልዩ ቀን ነች፤ ዛሬ የምናከብረው የኦዲፒን 29ኛ የምስረታ በዓልና 1ኛ ዓመት የድል ቀንን ነው ብለዋል።

ቀኑ ከዚህ በፊት ካከበርናቸው 28 ዓመታት ይለያል ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ፥ ምክንያቱም የዛሬዋ ቀን ከፍተኛ መሰዋእትነት በመክፈል ከመጣ ድል በኋላ የሚከበር በመሆኑ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) የህዝቡን ትግል በመቀላቀልና ራሱን በማደስ ለዛሬዋ የድል ቀን የደረሰ ፓርቲ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ከፊታችን ቀጣይ ትግል ይጠብቀናል ያሉት አቶ ለማ፥ የዛሬውን የምስረታ በዓልን ከማክበር በዘለለ ህዝቡን በልማት እና በኢኮኖሚ ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ ለሚደረገው ቀጣይ ትግል ራሳችንን የምናዘጋጅበት ነው ብለዋል።

ኦዲፒ ዛሬም ልክ እንደትናንቱ የሀዝቡን ጥቅም በማስቀደም እንደሚታገል በመጥቀስ፥ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎችም በቀጣይ በሚደረገው ትግል የህዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ ራሳቸውን ማዘጋጀት እንደለባቸውም ምልእከት አስተላልፈዋል።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

ኦዲፒ ለዛሬ ድል የበቃው ከህዝቡ ጋር በመሆን ነው ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ለማ መገርሳ፥ በቀጣይ ህዝቡ ከፓርቲው ጎን እንዲቆምና ድጋፍ እንዲያደረግለትም ጥሪ አቅርበዋል። አክለውም፥ ዛሬ እዚህ የደረስነው በአንድነታችን ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ወደ ፊትም የኦሮሞ ህዝብ ችግሮችን በአጭር ጊዜ ለመቅረፍ እና የሚያጋጥሙትን እንቅፋቶች ለማለፍ ያለን ብቸኛ አማራጭ አንድነታችንን ማጠናከር ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ለወጣቶች ባስተላለፉት መልእክት፥ እናንተ በከፈላችሁት መሰዋእትነት ዛሬ ላይ ደርሰናል፤ ወደ ፊትም በመደማመጥና በመተጋገዝ አሁን እንደ ሀገር የመጣውን ለውጥ ለማስቀጠል በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ ልዩነታችንን ወደ ጎን በመተው በመወያየትና በጋራ በመታገል መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በቀጣይ ጊዜያትም ልዩነታችንን በማጥበብ ለህዝቡ ጥቅም በጋራ እንስራ ሲሉም ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።

በአጠቃላይ ለኦሮሞ ህዝብ ባስተላለፉት መልእክትም፥ ሁሉም ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በእኩልነት የሚኖርባትን አዲሲቷን ኢትዮጵያ የመገንባት ሀላፊነት በኦሮሞ ላይ የተጣለ ነው፤ የኦሮሞ ህዝብ ከዚህ በፊት ሀገሪቱን ከወራሪ ለመጠበቅ ከፍተኛ መስዋዕትነት እንደከፈለ ሁሉ አሁንም ሀገሪቱን አንድ በማድረግ ታሪክ መስራት ይጠበቅበታል ሲሉም ተናግረዋል።

በፖለቲካ የተገኘው ድል ቀጣይነት የሚኖረው በኢኮኖሚው ዘርፍም ሲደገም ነው ያሉት ረእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ፥ ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ሰላም ነው ብለዋል።

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

ስለዚህም ኦዲፒ በቀጣይም የክልሉን ሰላም በማስጠበቅ በፖለቲካ ዘርፍ የተገኘውን ድል በኢኮኖሚውም ለመድገም በቁጥረኝነት እንደሚሰራ ነው ያስታወቁት።

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) በቀጣይ ጊዜያትም ለሀገሪቱ ሰላምና አንድነት ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ያሉት የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ፥ የሀገሪቱ ብሄሮችና ብሄረሰቦችም በዚህ ላይ እምነት ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል።

አቶ ለማ፥ በርካታ ኢትዮጵያውያን በዓሉ የእኛም በዓል ነው በማለት ከእኛ ጋር ለማክበር በመካከላችን ይገኛሉ በማለት ምስጋናቸውንም አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልእክት፥ ኦዲፒ ለኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን መላውን የሀገራችን ሕዝቦች በአንድነት፣ በሰላም እና በፍቅር በልጆቻቸው መስዋዕትነት የመጣውን ለውጥ እና ታሪካዊ ጉዞ በከፍተኛ ሃገራዊ ስሜትና ኃላፊነት እየመራ ይገኛል ብለዋል።

በዚህ ታሪካዊ የለውጥ ሂደት እያንዳንዳችን የጉዞው አንዱ አካል እንጂ አንዳችን የአንዳችን ተሳፋሪዎች አይደለንም።

እንደ አዲስ አበባ አስተዳደርም በዚህ ታሪካዊ ሂደት መዲናዋን እንደስሟ አዲስና ሀገራዊ ፣ አህጉራዊና አለማቀፋዊ ሚናዋን እንድትወጣና በደረጃዋ ልክ እንድትቀመጥ በሁሉም ትብብር በሰፊው እየሰራን እንቀጥላለን ሲሉም ተናግረዋል።

እስካሁን ባደረግነው እንቅስቃሴም ከላይ እስከታች ያለው አመራርና መላው ህዝብ እየሰጠ ላለው ድጋፍና ተሳትፎ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስም ምስጋና አቅርበዋል።

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶችን በመወከል የሶዴፓ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ባስተላለፉት ምልእክት፥ ያለፈው አንድ ዓመት የለውጥ ጉዞ በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ውስጥ ማንም ሊክደው የማይችለው ድል መመዝገቡን አንስተዋል።

በሀገር ደረጃ የተቀሰቀሰው የለውጥ ማእበል እና በኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪነት የመጣው ለውጥ አጋር ድርጅቶችን ከሁሉም በላይ ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑንም ገልፀዋል።

በተለይም በለውጡ የአጋር ድርጅቶች የሚመሯቸው ክልሎች ህዝቦችም ተጠቃሚ መሆናቸውን ነው የሶዴፓ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ሙስጠፌ ያስታወቁት።

በቀጣይ ለሚደረገው ሀገራዊ ለውጥም አጋር ድርጅቶች ከኦዲፒ ጎን መሆናቸውንም ነው አቶ ሙስጠፌ ያረጋገጡት።

የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶችን በመወከል የሶዴፓ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ባስተላለፉት ምልእክት፥ ያለፈው አንድ ዓመት የለውጥ ጉዞ በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ውስጥ ማንም ሊክደው የማይችለው ድል መመዝገቡን አንስተዋል።

በሀገር ደረጃ የተቀሰቀሰው የለውጥ ማእበል እና በኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪነት የመጣው ለውጥ አጋር ድርጅቶችን ከሁሉም በላይ ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑንም ገልፀዋል።

በተለይም በለውጡ የአጋር ድርጅቶች የሚመሯቸው ክልሎች ህዝቦችም ተጠቃሚ መሆናቸውን ነው የሶዴፓ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ሙስጠፌ ያስታወቁት።

በቀጣይ ለሚደረገው ሀገራዊ ለውጥም አጋር ድርጅቶች ከኦዲፒ ጎን መሆናቸውንም ነው አቶ ሙስጠፌ ያረጋገጡት።

በሙለታ መንገሻ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *