የሰብል ምርታማነት በሚፈለገው ልክ ባለማደጉ 26 በመቶው የክልሉ ሕዝብ ከድህነት ወለል በታች እንደሚገኝ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ።

አማራ ክልል ሰብል ሊመረትበት የሚችል 4 ነጥብ 95 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ባለቤት ነው፡፡ ከሀገሪቱ አጠቃላይ የሚታረስ መሬት ደግሞ 35 በመቶ ድርሻ ይይዛል፡፡ ከአጠቃላይ ምርትም 32 ነጥብ 8 በመቶውን ይሸፍናል፡፡ ይሁንና ክልሉ ካለው ሰፊ የመሬት እና የመስኖ ውሃ ሀብት አንጻር ምርታማነቱ በሚፈለገው ልክ አላደገም፡፡

ይህን አስመልክቶ የአማራ ክልል የመኸር ምርት ንቅናቄ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ አየተካሄደ ነው፡፡

በግብርናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ጥንካሬዎች እና ድክመቶች በውይይቱ ቀርበዋል፡፡ የክልሉን ምርታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ የመፍትሄ ሀሳቦች እና ምርታማነት በሚፈለገው ልክ ያላደገባቸው ምክንያቶችም ተገልጸዋል፡፡

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

የሰብል ምርትን በ 2001/2002 ከነበረው 56 ሚሊዮን ኩንታል በ 2010/11 102 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል ማድረስ ተችሏል በውይይቱ እንደተገለፀው፡፡ ይሁን እንጅ በ”ትራንስፎርሜሽን” ዘመኑ የታቀደውን 156 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ማሳካት አልተቻለም፡፡

በዚህም ምክንያት በምግብ ዋስትና ራስን ለመቻል የሚደረገው ጥረት በሚፈለገው ልክ አለመሳካቱ ተገምግሟል፡፡ በመሆኑም 26 በመቶው የክልሉ ሕዝብ ከድህነት ወለል በታች ይገኛል፡፡ የስራ እድል ለመፍጠር፣ ገበያውን ለማረጋጋት እና የስነ ምግብ ጤና ዘርፍን ለማሻሻል ምርታማነት ጉልህ ድርሻ ቢኖረውም በተለያዩ ምክንያቶች በሚፈለገው መጠን አለማደጉ በውይይቱ ተገልጿል፡፡

የማዳበሪያ እና የምርጥ ዘር አቅርቦት በወቅቱ እና በሚፈለገው መጠን አለመድረስ ለምርት መጠን የዜጎችን ሕይዎት በሚቀይር ደረጃ አለማደግ ከምክንያቶች ውስጥ እንደሚጠቀሱ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ሰለሞን አሰፋ ተናግረዋል፡፡ በክልሉ በያዝነው የምርት ዘመን 5 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ የሚያስፈልግ ቢሆንም 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብቻ መቅረቡን ዶር. ሰለሞን ገልጸዋል፡፡ ይህ የሆነውም በዓለም አቀፍ ገበያ የዋጋ ጭማሪ በመከሰቱ እና በማጓጓዣ ችግር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

የማዳበሪያ ስርጭቱ በወቅቱ አለመድረሱ በ2011/12 የምርት ዘመን የታቀደውን 120 ሚሊየን ኩንታል ሰብል ለማምረት እንቅፋት ሊሆን እንደሚችልም ስጋታቸውን ተናግረዋል፡፡ የግብዓት አቅርቦቱን ለማሟላት ቢሮው ጥረቱን መቀጠሉንም ነው የተናገሩት።

በአንጻሩ ክልሉ ምርጥ ዘር አስቀድሞ በማከማቸቱ በቂ አቅርቦት መኖሩ ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል አርሶ አደሮች፣ ባለሙያዎችና አመራሮች በቴክኖሎጂ እና በተሻሻሉ አሰራሮች ታግዘው በስፋት አለመስራታቸው በግብርናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ዐበይት ችግሮች መሆናቸውንም ዶክተር ሰለሞን ተናግረዋል፡፡

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

የሰብል ምርታማነትን በክልሉም ሆነ በሀገር ደረጃ ለማሳደግ በሳይንሳዊ መንገድ ታግዞ መስራት እንደሚገባ በውይይቱ ተመላክቷል፡፡ የማሳ መረጣ፣ ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ በአግባቡ መጠቀም፣ በወቅቱ መዝራት፣ የተፈጥሮ ማዳበሪያ (ኮምፖስት) መጠቀም፣ አሲዳማ መሬትን ማከም፣ ትርፍ ውሃን ከማሳ ማስወጣት እና ሰብልን በወቅቱ መሰብሰብ በመፍትሄነት ከቀረቡት ምክረ ሀሳቦች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ጤፍ፣ በቆሎ፣ ማሽላ እና ስንዴን የመሳሰሉ ጉልህ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ሰብሎችን በስፋት ማምረት ለምርታማነት አድገቱ ተገቢ መሆኑም በውይይቱ ተመላክቷል፡፡

Amhara mass media

ዘጋቢ፦ ቢኒያም መስፍን

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *