የሀገር መከላከያ ሰራዊት ግጭት ተከስቶ በነበረባቸው በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች  በመግባት የመቆጣጠር እና የማረጋጋት ስራ በማከናወን ላይ መሆኑን ገለፀ። በግጭቶቹ ጀርባ ማን ነው ያለው የሚለው ተጣርቶ እርምጃ እስከሚወሰድ ድረስ ህብረተሰቡ ተረጋግቶ መደበኛ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን እንዲያከናውን ጠይቀዋል። ግጭቶቹ ባሉባቸው አካባቢዎች  በሁለቱም ወገን ያሉ አመራሮች ከጉዳዩ እጃቸውን እንዲያስወጡም አሳስበ

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የምክትል ኢታማዡር ሹም ፅህፈት ቤት ሀላፊ ኮለኔል ተስፋዬ አያሌው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትእንደተናገሩት፥ የክልሉ መንግሰት ባቀረበው ጥሪ መሰረት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢዎቹ ገብቶ የማረጋጋት ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል።

አሁን ላይም አካባቢዎቹ እየተረጋጉ ቢሆንም በመንገድ ዳርቻዎች ላይ አልፎ አልፎ የተኩስ ልውውጥ እንዳለ ነው ያመለከቱት።

ከተሞች ወደ መረጋጋት ቢገቡም የተኩስ ልውውጡ የሚሰማውም በገጠራማ አካባቢዎች መሆኑን ጠቁመዋል።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

አካባቢዎቹ ሰፊ እንደመሆናቸውም በብቃት ለመቆጣጠር ተጨማሪ ሀይል ወደ ስፍራዎቹ አሁንም እየገባ መሆኑን የጠቆሙት ሃላፊው፥ በሁሉም ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች እየገባ የማረጋጋት እና የመቆጣጠረ ስራ ያከናውናል ብለዋል።

የግጭቱ መንስኤን ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የማጣራት ስራ እንደሚከናወን እና ያንን መሰረት በማድረግ አርምጃ እንደሚወሰድ አመልክተዋል።

ተዘግተው ያሉ የደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ደብረ ሲናና እና ደብረ በርሃን መንገዶችንም የማስከፈት ስራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

ኮለኔል ተስፋዬ በሁለቱም በኩል ታጥቆ ያለ ህዝብ የሚኖርበት አካካባቢ መሆኑን ነው የገለፁት።

በግጭቶቹ ጀርባ ማን ነው ያለው የሚለው ተጣርቶ እርምጃ እስከሚወሰድ ድረስ ህብረተሰቡ ተረጋግቶ መደበኛ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን እንዲያከናውን ጠይቀዋል።

ግጭቶቹ ባሉባቸው አካባቢዎች  በሁለቱም ወገን ያሉ አመራሮች ከጉዳዩ እጃቸውን እንዲያስወጡም አሳስበዋል። by  (ኤፍ.ቢ.ሲ)

Photo – file (ኤፍ.ቢ.ሲ)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *