ያለደረሰኝ ግብይት ሲፈጽሙ የነበሩ ሶስት ከፍተኛ ግብር ከፋይ ድርጅቶች እጅ ከፍንጅ መያዙን የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለስልጣን አስታወቀ። ባለስልጣኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ድርጅቶቹ የ95 ሺህ ብር ግብይትን ያለደረሰኝ ሲፈጽሙ በተደረገ ዘመቻ መያዛቸውን ገልጿል።

አቡበከር ይማም፣ አሽቃር ውድማጣስ እና አብዲሳ ከበደ በሚል የንግድ ስም የተመዘገቡት ድርጅቶቹ በግንባታ ግብዓት ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ናቸው ተብሏል። የባለስልጣኑ የህግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት ንጉሴ እንዳስታወቁት የድርጅቶቹ እንቅስቃሴ ለ15 ቀናት ክትትል ሲደረግበት ቆይቷል።

በዚህ አመት ብቻ 700 የዘመቻ ስራዎች መሰራቱን የጠቀሱት አቶ ታምራት፥ የአሁኑ ድርጅቶቹ አመታዊ ገቢያቸው ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሆኑ ከፍተኛ ግብር ከፋይ መሆናቸው እና በግብር ስርዓቱ ውስጥ ከፍተኛ ጫናን የሚያሳርፉ በመሆናቸው እንደሚለይ ተናግረዋል።

ባለስልጣኑ በከተማዋ የሚደረገውን ያለደረሰኝ የሚፈጸም ግብይት ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር አጠናክሮ እቀጥላለሁም ብሏል።

FBC

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *