Related image

በመፈቅለ መንግስት እ.አ.አ ከ1989 ወደ ስልጣን የመጡት አልበሽር በገቡበት መልኩ ተሸኝተዋል። በሽር የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች በመርዳት፣ በማስታጠቅ፣ ከለላ በመስጠት የሚታወቁ ናቸው። ከሁሉም በላይ ግን በዳርፉር ምስኪኖች ላይ የፈጸሙት ጭፍጨፋ ሁሌም ይዘክራቸዋል።

መንግስት ገልብጠው በጠመንጃ ሱዳንን ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት አልበሽር ከስልጣን እንደሚወርዱ በገሃድ መነገር ከጀመረ ቢሰነባብትም ዛሬ በገሃድ ወታደሮቻቸው አሰናብተዋቸዋል። በተቃውሞ የከረሙት ዜጎች ደስታቸውን ሲገልጹና እልል ሲሉ የሚያሳዩ ምስሎችና ቪዲዮዎች ከካርቱም እየወጡ ነው።

በየስፍራው ” ታላቁ መሪ” የሚል ዓይነት መፈክር ተጽፎበት የተለጠፈው ምስሎቻቸውና ባነሮች በሰዓታት ወደ ቆሻሻነት ተለውጠዋል። ጦር ሃይሎ ቁልፍ ስፍራዎችንና የመገናኛ አውታሮችን ከተረከበ በሁዋላ ለሁለት ዓመታት የሚፈጅ የሽግግር መንግስት አውጇል። ህገ መንግስቱም ውድቅ መደረጉን አብስሯል። ከሁለት ዓመት በሁዋላም መንግስት በምርጫ እንደሚቋቋም ይፋ አድርጓል። እናም አልደፈር ባዩ በሽር ማረፊያ ቤት ተዛውረዋል።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

የመከላከያ ሚኒስትሩ አህመድ አዋድ ቢን አውፍ በሱዳን የቴሌቪዥን ጣቢያ  የሱዳን ጦር ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽርን ከስልጣን በማውረድ ስልጣን መቆጣጠሩን በማስታወቅ ሀገሪቱን ለሁለት ዓመታት የሚያስተዳድር ወታደራዊ የሽግግር መንግስት መመስረቱን አብስረዋል። የሽግግር መንግስቱንም የመከላካያ ሚኒስትሩ እንደሚመሩት ተመልክቷል። አገሪቱ እስክትረጋጋ ለሶስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል።

ጀነራሉ በመግለጫቸው የአገሪቱ ህገመንግስት ከስራ ውጭ መሆኑን፣  የሀገሪቱ ድንበሮች መዘጋታቸውንና ለ24 ሰዓታት የአየር ክልሏ ከእንቅስቃሴ ውጭ መሆኑን ገልጸዋል።  አልበሽርም በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተናግረዋል።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

የዳቦ ዋጋ ውጋ ናረ በሚል ሰበብ የተቀጣጠለው ተቃውሞ በመጨረሻ ጦር ሃይሉን አካቶ አልበሽርን በልቷቸዋል። ሰላሳ ዓመታት በሱዳን ሕዥብ፡ጫንቃ ላይ የተፈናጠጡት አልበሽር ቀጣይ እጣቸው ምን እንደሆን ከወዲሁ በይፋ የተገለጸ ጉዳይ ባይኖርም፣ የቀድሞው የዓለም ኧቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ያልተዘጋ ፋይል እንኳን ደህና መጡ እንደሚላቸው ይጠበቃል።

በተለይም ለህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ግንባር እጅግ የቀረቡ ስትራቴጂክ ወዳጅ የሆኑት አልበሽር ላይመለሱ መወገዳቸው፣ ኤርትራ ላይ ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ መነሳትና የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የምስራቅ አፍሪቃ ፖለቲካ ላይ ወሳኝ ሚና እንዲጫወቱ ዳግም እድል ማግኘታቸው፣ ዶክተር አብይ በቀጠናው የያዙት አዲስ ሃሳብ ጋር በትቅሉ ሲታይ ቀላል የምይባል የአሰላለፍ ለውጥ እንደሚታይ ከወዲሁ እየተነገረ ነው።  በአገር ቤት ያለውም የማፈንገጥ ፖለቲካ ሊላዘብ እንደሚችል ግምት እየተሰጠ ነው።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

አዲሱ የሱዳን አስተዳደር ከኤርትራና ከኢትዮጵያ ጋር ሳይውል ሳያድር ግንባር እንደሚገጥም የሚገልጹ ክፍሎች በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል በአልበሽር ወቅት የነበረው ያልጠራ ግንኙነት መስመር እንደሚይዝ፣ ከክልልና ከመንደር መሪዎች ጋር የሚደረግ የጓሮ ምክክር እንደሚቆም በድፍረት ይናገራሉ። የደቡብ ሱዳን ችግር እንደሚቃለል ያመለክቱት ክፍሎች በሱዳን የተደረገው ለውጥ ዝም ብሎ ከውስጥ ስለተፈለገ ብቻ የመታ አለመሆኑንንም ያሰምሩበታል።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *