ደቡብ አፍሪካ በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ አደጋ ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስድስት የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተሮችን ልትልክ ነው።

በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተነሳውን ቃጠሎ ለመቆጣጠር ደቡብ አፍሪካ ስድስት የእሳት ማጠፊያ ሄሊኮፕተር ልትልክ መሆኑን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል። በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ በተለያዩ የፓርኩ ክፍሎች ላይ የእሳት ቃጠሎ መድረሱ ይታወቃል።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

የእሳት ቃጠሎው በቁጥጥር ስር ከዋለ ከሳምንት በኋላም ያለፈው ሰኞ ድጋሚ መቀስቀሱን ተከትሎ የአካባቢው ማህበረሰብ እሳቱን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ይገኛል።

በተደረገው ርብርብም አምባው ላይ የተነሳውን እሳት መቆጣጠር የተቻለ ቢሆንም የተነሳው እሳት ግን ወደ ፓርኩ ገደላማ አካባቢ እየተስፋፋ በመሆኑ ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ሆኗል።

እስካሁን በደረሰው ቃጠሎ ምንም አይነት በዱር እንስሳት ላይ የደረሰ አደጋ የለም ያሉት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ፥ በቀጣይ ቃጠሎውን ለመቆጣጠር ከደቡብ አፍሪካ ስድስት ሄሊኮፕተሮችን ለማምጣት መስማማታቸውን ገልጸዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በተጨማሪም ፈረንሳይ ድጋፍ ለማድረግ መስማማቷን የገለጹ ሲሆን፥ኬኒያም በሀገራቸው ፓርክ ላይ በተነሳ እሳት ምክንያት ባፋጣኝ መላክ አለመቻሏን ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ ከቀጣይ ማክሰኞ ጀምሮ የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር መላክ እንደምትችል ማስታወቋን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል ።

FBC

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *