(ከታምራት ይገዙ) – የዛሬውን ጹሁፌን እንዲህ በማለት ተንደርድሬ  ልጀምር:: አቶ ኤርምያስ ለገሰ ሰላምና እርቅ ለአንተና ለአንተ ይሆን ዘንድ የዘወትር ምኞቴ ነው ምክንያቱም በራሱ ላይ ሰላም ፍቅር የሌለው ግለሰብና ከራሱ  ጋር የሚጣላ አሊያም የተጣላ ሰው ለአገራችንም ሆነ ለዛ ለሚሰቃይ ህዝባችን የሚያስብ ሆኖ አይገኝም አሊያም  ይህም ያልፋል ለሚባለው የብህሎች አባባል ቦታ የሚሰጥ አይሆንምና ነው:: ከራሱ ጋር የተጣላ ሰው የሚናገረው ሁሉ እንደ ሬት የመረረ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የሚነገርበት አስተያየት እንኳን ምን ጠሩ ቢሆን የእርሱ ዦሮ አድምጦ አዕምሮው የሚተረጉመው ግን ሬት ሬት አርጎለት ስለሆነ ለማንም ሰው ጤና አይሰጥም ስለሆነም አቶ ኤርምያስ ለማንም ይቅርታ ከመጠየቅህ በፊት መጀመሪያ ከራስህ ጋር እርቅ ማድረግ አለብህ ይህንን እርቅ ከራስህ ጋር ከአደረክ ያን ግዜ የምትናገረውን ሁሉ የሚያዳምጡህ  ማር ማር እያላቸው  አጣጥመው ያድምጡሃል እነርሱም የሚሉሁ ሁሉ ማር ማር አያለህ አጣጥመህ ታዳምጠዋለህ ማለት ነው እንግዲህ ምርጫው የአንተና የአንተ ብቻ የአቶ ኤርምያስ ለገሰ ነው  እሬት ይሁን አሊያም ማር

እንደ እውነቱ ከሆነ በተለያየ ግዜ አቶ ኤርምያስ ላለፈው አንድ ዓመት በዕለታዊ ቢሚባለው ፕሮግራም ላይ  ለሚያነሳቸውና ለሚሰጣቸው ትንታኔዎች ምክናታዊ የሆኑ ሙግቶች ላቀርብለት እያሰብኩ አይ ይቅር ያደገውና ያሳደገው ሟቹ መለስ ዘናዊና የኢሃዴግ መራሹ ሕወሀት ነው በማለት አልፈው ነበር :: ሆኖም ግን ሰሞኑን ኢሳት ላይ በዕለታዊ ቢሚባለው ፕሮግራም ላይ እራስን ጻዲቅ አርጎ ሌሎችን ሃጢያየኛ የማድረጉን አካሄድ መልእክት አድምጬ ለማለፍ ህሊናዬ አልፈቀደምና ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት አብሮ ይፈተፍታል” የሚባለውን የአቦው ምሳላዊ አነጋገር ላስታውስህና ልሞግትህ ፈቀድኩ::

የተቃውሞም ሆነ የድጋፍ ሀሳብ የማቅረብ ሁሉም እኩል መብት እንዳለውም እረዳለሁ ግን ይህንን መብታችንን  በተለይ አገራችን በአሁኑ ሰዓት ያለችብትን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት በጥንቃቄ ለበጎ እና ለገንቢ ነገር ብናውለው ጥሩ ይመስለኛል :: ተቃውሟችንም ምክኒያታዊ እና ብስለት ሲላበሰ ነው ለወጤት የሚበቃው:: በተለይ እንዳንተ ያለ በኢሃዴግ መራሹ ሕወሃት ውስጥ ጥርሱን ነቅሎ ላደገና እስከ ሚንስትር  ደረጃ የደረሰ ትላንት በህዝባችን ላይ ለተፈጸመው ግፍና መከራ አሻራውን ጥሎ ላለፈ  የአሁኑ አክቲቪስና ጋዜጠኞ በዛም አነሰ ተከታዮች ያፈራ እያየ መራመድ እና እያስተዋለ መተንፈስ ይጠበቅበታል የሚል እምነት አለኝ::

በርግጥ ቅዱስ መጽሀፍ ከፍሬአቸው ታውቋችኋላችሁ እንደሚለው የአንተ አድራጎት  ከምር ለአገራችንና ለህዝባችን ሰላም ፈላጊ አለመሆንህን አንደበትህ ያሳብቅበሃል ይህን ለምን እንደ ማትለኝ እርግጠኛ ነኝ ምክንያቱም በሚንስተርነት ዘመንህም ሆነ አሁን ጋዜጠኛና አክቲቨስት ከሆንክም ቦሃላ እንደ ተጠያቄ ሰው አይደለም ንገሮችን የምታያቸው በምሳሌ ልሞግትህ::

ዶ/ር አብይ ስልጣን በያዙበት ሰሞን አቶ ኤርምያስ ትንታኔ ሲያደርጉ የዶ/ር አብይ መመረጥ ትግሉን እንደተፈለገው መጠን ሊያፈጥነው አይችልም በሳቸው ፋንታ ዶ/ር ደብረ ጺዮን ቢመረጡ ይሻል ነበር የሚል እድምታ ታሰማ ነበር:: በኔ እይታ ይህ አባባል “መሸጥ የለመደ እናቱን ያስማማል” እንደሚባለው አቶ ኤርሚያስ ለገሰ የዶ/ር ደብረ ጺዮንን መመረጥ የፈለከው በአገራችን ውስጥ ህዝብ ከህዝብ ጋር ደም ሲፋሰስ አንተ ግን በነጻዊቷ አገር ቁጭ ብለህ ስለሚፈሰው ደም ዳጎስ ያለ መጽሃፍ ጽፈህ ዳጎስ ያለ ሀብት ለማከማቸት ነው የሚል እምነት ነው ያለኝ:: በሌላ በኩል ይህ ዓይነት አካሄድህ ደሞ ከቡርቃ ዝምታ ደራሲ ከጋዜጠኛ ተስፋዪ ገብረአብ ጋር አንድ ያደርጋችዋል ለነገሩ ሁለታችሁም በሸር ያሳደጋችሁ ሊቀ ሴጣኑ መለስ አይደል

April 6/2018 ወይንም መጋቢት መጨረሻ 2010 ላይ ደሞ በዕለታዊ ፕሮግራም ላይ በ25ኛው ደቂቃ ላይ እንዲህ በለህ ነበር “ስለ ማዕከላዊ መዘጋት አንስተህ አተታ ስታቀርብ እነዚ ሰዎች በ27 ዓመታት ውስጥ ቶርቸር ፈጽመናል ብለው ያምናሉ ወይ? ከዶ/ር አብይ ጨምሮ? ትላለህ:: እንደ እውነቱ ከሆነ ጠ/ሚ ዶ/ር ዕብይ ለዚህ ዓይነቱ ጥፋት መሰለኝ ይቅርታ የጠየቀው ይህንን ይቅርታ የማትቀበል ከሆነ አቶ ኤርምያስ እንደ እውነቱ ከሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠ/ሚ ዶ/ር ዕብይን ስህተት ከማወቁ በፊት አንተን ኤርሚያስ ለገሰን በአዲስ አበባን ወጣቶች ላይ በሰራኽው አስከፊ ስራ በውል ያውቅሃል ብል ማጋነን አይደለም:: ህወሀት ኢትዮጵያውያን ላይ ለፈጸመው አረመናዊ ጭካኔ ሁሉ የእጅህ አሸራ ያለበት በመሆኑ የኢሕኣዴን አመራሮችን በማውግውዝ የአንት ሓጢያት ሊሺረው አይችልም ባይ ነኝ:: ለምን እራስህን እንደ ጲላጦስ ከደሙ ንጹህ ነኝ  ትላለህ?

ሌላው ደሞ በ28ኛው ደቂቃ ላይ እንዲህ በለህ ነበር ሙዜም ውስጥ የነማን ታሪክ የነማን ምስል ነው የሚቀመጠው የሚለውም መታሰብ አለበት ለምሳሌ ብለህ ከአጠገቤ ብነሳ በማለት በአጠግብህ ያሉ ሰዎችን ስም በመጥራት አስቀምጠሃል::  በተጨማሪ ለ27ዓመት ውስጥ የተፈጸመውን ቶርቸር በቭዲዮ ተቀርጾ በምስል ተደግፎ ይቀርባል ወይ ብለህ ጥያቄ ታቀርባለህ::  እውነት እውነት እልሃለው አቶ ኤርምያስ በሙዜም ውስጥ የተገራፊዎቹ ስምና ምስል ብቻ ሳይሆን የአስገራፊዎቹ ሚንስትሮችና የገራፊዎቹ ምስል ጭምር መቀመጥ አለበት ታዲያ የነ አቶ መለሰ; የነ አቶ በረከት እና የሌሎቹ ግፍ ፈጻሚዎች ፎቶ (ምስል) ሲለጠፍ የእርሶ የአቶ ኤርምያስ አይኖርም ብለው ያስባሉ ምክንያቱም የአቶ በረከት ካለ እርሶም አሉ ማለት ነው ምክንያቱም ምን ግዜም ቢሆን አገራዊ እርቅ መጥቶ በዳይም ተበዳይም ይቅር እግዚአብሔር ካልተባባለ በስተቀር በአቶ በረከት ውስጥ እርሶ ይኖራሉ  በእርሶ በአቶ ኤርሚያስ ውስጥ አቶ በረከት አሉ :: ለእንደዚህ ዓይነት

አቶ ኤርምያስ ህወሀት/ኢሃዴግን ከድተው ስለወጣህና የህወሀት/ኢሃዴግ በለስልጣኖች የፈጸሙትን ወንጀል ዳጎስ ባሉ ሁለት መጻህፎ ለንባብ ስላበቁ(እርሶም ዳጎስ ያለ ዶላር ያገኙ ይመስለኛል ለፈገግታ) እንደ ጲላጦስ ከደሙ ንጹህ ነኝ ብለው ከሆነ ተሳስተዋል ቢያንስ የአቶ በረከት ሃጢያት ሲነሳ የእርሶም የሚነሳ ይመስለኛል ለምን ብትሉኝ እርሳቸው ሃጢያት እንዲሰራ ከሚሉኮቸው ሰዎች ውስጥ እንደውም በጣም የቅርብና ምክትላቸውም የነበሩ ስለነበረ::  በእርሳቸው ውስጥ እርሶ አሉ በእርሶ ውስጥ እርሳቸው አሉ ብል ማጋነን አይሆንብኝም::

አቶ ኤርሚያስ ከአገር ከመውጣቶት በፊት በሚሊዮን በሚቆጠሩ ወጣት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን  ውስጥ ወያኔያዊ አስተሳሰብ ፍለላጎትና እምነት እንዲሰረጽ  የሰሩ ሞሆነትን እርሶ ይረሱ ይሆናል እንጂ ታሪክና ትውልድ አይረሳውም::፣ እሱም ብቻም ሳይሆን ከመምሩ ዲቀ መዝሙሩ እንደ ሚባለው ትን ታንግ የሆኑ የህወሀትን ካድሬዎችን አሰልጥነው  ያሰማሩ ፣ ከሁሉ የሚከፋው ደሞ ወጣቱ ትውልድ ለትግል እንዳይነሳሳ ስነ ልቦናውን የሰለቡና ያሰለቡ ኖት :: በታሪክ ብልታቸው የተሰለቡ ጅግኖች ነበሩን ልቡ የተሰለበ ጅግና ግን የለንም ይህም የሚያሳየው የእርሶና የአለቃዎት የአቶ በረከት መመሪያ በወጣቱ ብልት ላይ ጠርሙስ ማንጠልጠል ብቻ ሳይሆን ትልቁ ስራችሁ ስነ ልቦናውን መስለብ ነበር:: ኢህኣዴግ ለተፈጸመው ሁሉ አሻራቸውን በተወሰነ ደረጃ ትተው ካለፉ ሰዎች ውስጥ እርሶ አንዱ ኖት ብል  ከእውነት የራኩኝ አይመስለኝም::

አቶ ኤርምያስ አንድ ጥያቄ ልጠይቆት ከመለሱልኝ ጥያቄዪም እየተካሄደ በላው የአገራችን የሽግግር ለውጥ አሉታዊ ላይ በአቶ በቀለ ጋርባ; በአቶ ጁዋር መሃመድ; በአቶ ተስፋዪ ገብራብ እና በእርሶ(በአቶ ኤርምያስ ለገሰ) እንዲሁም በዶ/ር ጸጋዪ አራርሳ  መሃከል ያለው ልዩነትን ምንድን ነው? ለኔ ግራ ቢገባኝ “ቀልቀሎ ስልቻ ስልቻ ቀልቀሎ” ብዪ ማለፉን ነው የመረጥኩት::

አቶ ኤርሚያስ ይቺ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ስንት የመከራ ወንዞችን ተሻግራለች መሰሎት ገና ስንት ትሻገራለች እውነት ነው የምሎት አቶ ኤርሚያስ ይህቺ አገራችን ስንት የግፍ ተራራዎችን አቋርጣለች እንዳይገርሞት ገና ስንት ታቋርጣለች አልዋሾትም አቶ ኤርሚያስ ኢትዮጵያችን ስንት የበደል ሰይፎችንና ጦሮችን አምክናለች መሰሎት ገና ስንት ታመክናለች እውነት እውነት ነው የምሎት ኢትዮጵያችን  ስንት አምባገ- ነኖችንና  በቁማቸው የሞቱ  እያለቀሰች ቀብራለች ገና ስንቱን በቁማቸው የሞቱትን ትቀብራለች ባጠቃላይ  ጭቆና ከኢትዮጵያውያን ደም ሙልጭ ብሎ ወጥቶ በነፃነት፣ በእኩልነት፣ በዳኝነት በጠራ ደም እስቲተካ ድረስ ኢትዮጵያ  ወደ እግዚአብሔር እጆችዋን ዘርግታ ትጸልያለች የሚል ተስፋ አለኝ::

በሌላ በኩል በኔ እምነት “ዛሬ አገራችንን  ክፉኛ የጐዳው የእኲይ ሰዎች ግብር ብቻ ሳይሆን፣ የጥሩ ሰዎች ዝምታ ጭምር ነው፡፡ ከየትኛውም የታሪክ ጊዜ ይልቅ፣ ክፉዎች በክፋታቸው ጥሩዎች ደግሞ በዝመታቸው በአገራችን በኢትዮጵያና በሕዝባችን ላይ አባሪ ተባባሪ ሆነዋል፡፡ ክፉዎች ክፋትን በኢትዮጵያ ላይ በገቢር ሲተገብሩ፣ ጥሩዎች በግብር አልቦነት እኲይ እንዳሻው እንዲናኝ ሙሉ ፈቃድ ወይንም ዕድል ሰጥተውታል (ፈረንጆቹ sin of omission and sin of commission ከሚሉት ሐሳብ ጋር ይዳበላል፡፡ የሚገርመው በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ አገር የምትኖሩ ኢትዮጵያዊ ሙህራኖች የት ነው ያላችሁት እውቀታችሁ እና የህይወት ተሞከሮችሁ በአሁኑ ሰዓት ለምትወዶት አገራችሁና ለምትወዱት ህዝባችሁ ካልዋለ የናንተ ተሞክሮና የናንተ እውቀት “የጋን ውስጥ መብራት ነው” ቢባል ስህተት ይሆን? በዚህ አጋጣሚ ምግባራቸውን በውል ሳያጤኑ ወይ እኲዩን ወይ ደግሞ ጽድቅን በማድረግ ላይ ያሉ አላዋቂዎችን አልዘነጋሁም፡፡

 

በመጨረሻም ኤርምያስ ለገሰ ተስፋዪ ገብረአብ

ጀዋር መሓመድ ጋሽ በቀለ ገርባ ምንና ምን ናቸው

ለሸርና ተንኮል የጆሮ ጉታቻ ያንገት ሃብል ናቸው በማለት ለዛሬው ልሰናበት::

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *