በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳዳር በፍኖተ ዳሞት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አንድ ነብር ተማሪዎች ወደሚማሩበት ክፍል ገብቶ በሶስት ተማሪዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን ኮሌጁ አስታወቀ ፡፡

የኮሌጁ ዲን አቶ ነብዩ መኮንን ዛሬ ሚያዚያ 4/2011 ዓመተ ምህረት ረፋድ ላይ ተማሪዎችና መምህራን ሰላማዊ የመማርና ማስተማር ስራቸውን ሲያከናውኑ ነበር ፡፡ ነገር ግን ከየት እንደመጣ ያልታወቀ ነብር ተማሪዎች ወደ ሚማሩበት ክፍል ውስጥ መስኮት ሰብሮ በመግባት በተለይ በአንድ ተማሪ ላይ በአንገቱ ፣ በራሱ ላይና በእጁ ላይ ጉዳት አድርሷል ፡፡ በሌሎች ሁለት ተማሪዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት ማድረሱን አቶ ነብዩ ተናግረዋል ፡፡

ሦስት ነብሮች በአካባቢው በተደጋጋሚ ይታዩ እንደነበር ከጥበቃ ሰራተኞች እና ከአካባቢው ነዋሪዎች መረጃ ይሰጣቸው እንደነበር የገለጹት አቶ ነብዩ ዛሬ ጥዋት ላይም ወደኮሌጁ ገብቶ እንደታየ ገልጸዋል ፡፡

ሁሉም ተጎጅዎች በፍኖተ ሰላም ሆስፒታል ህክምና ተደርጎላቸው ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን የገለጹት አቶ ነብዩ በቀጣይ የመማር ማስተማር ስራውን ሰላማዊ አድርጎ ለማስቀጠል ስጋት ስለፈጠረ የሚመለከተው አካል አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል ፡፡

ነብሩ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ ጥዋት በተማሪዎች ላይ ጉዳት ያደረሰው ነብር አሁንም ተማሪዎች ከሚማሩበት ክፍል ውስጥ ገብቶ መውጣት እንዳልቻለ የኮሌጁ ዲን ገልጸውልናል ፡፡

እርስዎ ቢሆኑ በዚህ ወቅት ምን ሊያደርጉ ይችላሉ ?

Finote Selam City Government Communication Affairs Office

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *