አዲስ አበባን አስመልክቶ ከተለያዩ ጽንፎች የሚነሱትን ሃሳቦች በማካተት ሁሉንም ወገን የሚያካትትና የሚያግባባ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚያስችል ውይይት በማካሄድ  መግባባት ላይ ለመድረስ እቅድ መያዙን ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ አገር ወዳድ ከፍተኛ የስራ ሃላፊ ለዛጎል ተናገሩ።

ጋዜጠኛ እስክንድ ነጋ የሚመራውን አካልና አቶ ጃዋር መሐመድንና ጉዳዩ የሚመለክታቸውን አካላት በማገናኘት ህዝብ ሊታዘበውና ሊፈርድ በሚችልበት መልኩ ውይይት ይካሄዳል። ውይይቱ እንዲካሄድ እየሰራ ያለውን አካል ለጊዜው ያላስታወቁት የዜናው ምንጭ፣ በውይይቱ መግባባት ላይ እንደሚደረስ እምነታቸውን ገልጸዋል።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

በአዲስ አበባ ጉዳይ ያለው ችግር በአብዛኛው ረጋ ብሎ ያለመወያየትና ጉዳዩን ከራሳቸው የውክልና ዓላማ አንጻር የሚያራግቡ አካላት ባልተገባ መልኩ እያጦዙት መሆኑንን የጠቆሙት የዛጎል ምንጭ፣ በፍጹም ቀናነት ጉዳዩን አጀንዳ ያደረጉ ወገኖች ችግሩን በውይይቱ እንደሚፈቱት እርግተኛ መሆናቸውንና ለሌሎችም አካላት አርዓያ እንደሚሆኑ አመልክተዋል።

እስክንድርና ጃዋር በጉዳዩ ላይ ስለመስማማታቸውና ውይይቱ መቼና እንዴት እንደሚደረግ ይፋ ያላደረጉት የዜናው አቀባይ፣ ውይይቱ በቅርቡ ሲካሄድ ከመግባባት ላይ እንደሚደረስ እምነታቸው እንደሆነ አመልክተዋል። ይህንን ሃላፊነት በመውሰድ ስራውን እየሰራ ላለው አገር ወዳድ ያላቸውን ክብርም ገልጸዋል።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

በካሚሴና አካባቢዋ ተነስቶ ከነበረው ችግር ጋር በተያያዘ በሚመራው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክ መግለጫ የሰጠው ጃዋር መሐመድ ከዚህ ጋር ይያያዝ አይያያዝ ባይታወቅም ” ግልስጽ ውይይት፣ በግልጽ መወያየት፣ ከስር አንስቶ በቀናነት በመወያየት መፍትሄ ልንፈልግ ይገባል። ተዋልደናል…” ሲል ባልተለመደ መልኩ የሰከነ መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *