በትናንትናው እለት ለዝግጅት ክፍላችን አንዲት ስፍራውን የጎበኝች ወዳጇ ያጫወተቻትን የገለጸች እህት እንዳለችው የጌዲኦ ጉዳይ እረፍት የሚሰጥ ጉዳይ አይደለም። ባልደረባዋ አካባቢውን አይታ ከተመለሰች በሁዋላ ለቀናት ታማለች። ያየችውን በውሉ ለመናገር የሚያስችል አቅምም የላትም። ባለቤቷም በሁኔታዋ ተጨንቋል።

የሰማችውን ያጫወተችን እንዳለችው ነገሮች ሁሉ ይከብዳሉ። ለመናገርና በእዛ ያለውን እውነታ ለማስረዳት ይቸግራል። ቀውሱ በቃላት የሚገለጽ አይደለም። ህጻናት፣ ሴቶች፣ አራሶች ፣ አዛውንቶች፣ ሁሉም ተፈርዶባቸዋል። ሰው እንደጨው በተዘራበት በዚያ ስፍራ የሚሆነው ሁሉ ሰው ለሆነ ምጥ ምጥ ያሰኛል። ህሊናን ስለሚረብሽ ሰው የሆነ ያን ካየ በሁዋላ ወደ ቀድሞው ማንነቱ ለመመለስ ይጨንቀዋል።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

ህጻናት የተጣለ አጥንት አንስተው እንደሚግጡ ከመስማት በላይ የሚያም ጉዳይ አይኖርም። እመጫት እርጥብ ህጻን ደረቷ ላይ ተጣብቆ እንደ አረም ሜዳ ላይ ወድቃ ማየት ለድርጊቱ ፈጻሚዎችና ለሴራው አካሎች መዝናኛቸው ነው። ሰው ከቄዬው ተባሮ በህይወት እያለ ሜዳ ላይ መጣሉ ለነዚህ ክፉ ጭራቆች ድላቸው ነው። ስለ ሁኔታው የተናገረችው እህት ሁሉም በየበኩሉ በአዲስ አበባ የተጀመረውንና በየአካባቢው የሚችለውን ያድርግ ባይ ናት። መንግስትም የተረከበው የመከራ ክምር ሰፊ ቢሆንም ክረምቱ ሳይብስ ለጌዲዮ ህዝብ አስቸኳይ አማራጭ ሊፈልግ ግድ ነው።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ይህቺ እህት እንዳለቸው መከራውና ክፉው በደጅ ነው። የባሰው በበራችን ፊት ለፊት ነው። አስቀድሞ ክፉውን መቀነስ እንደ ዜጋም፣ እንደ ሰውም ግዳጅ ነው።

ፎቶ ከስዩም ተሾመ ፌስ ቡክ የተወሰደ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *