ለውጡ ሱዳንን እንዳያምሳትና ወደ እርስ በእርስ ግጭት እንዳያመራት ስጋት አለ። በለውጡ ሲፈነጥዝ የነበረው ህዝብ ጦር ሰራዊቱ የሽግግር ስልጣን መያዙን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ተቃውሞ እየተሰማ ነው። ትግሉና ተቃውሞው በጠመንጃ ስልጣን የያዘ አካል እንደገና ስልጣን መያዝ የለበትም በሚል ነው ተቃውሞ የተነሳው። ተቃውሞውን ሲመሩ የነበሩት ወገኖች የሲቪል መንግስት ሊቋቋም እንደሚችል እያሳሰቡ ነው። ይህንኑ ከግንዛቤ የከተተ ይመስላል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መግለጫ አውጥቷል። ” ሱዳን ከተረጋጋች ትርፍ አለው፤ ከተናጋች አደጋው ክፉ ይሆናል ” ሲሉ አስተያየት የሰጡ አሉ።

የአዲሱ ፖለቲካ ጅማሮ !! “መንግስት የሱዳንን ሕዝብ ፍላጎት በውል ይረዳል፣ ያከብራል”

የሱዳን የሰላሳ ዓመት መሪ ከመንበራቸው ከተሰናበቱ በሁዋላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫው የሱዳንን ህዝብ ፍላጎት በውል እንደሚረዳና እንደሚያከብር አመልክቷል። ኢትዮጵያ የእህት አገር ሱዳንን የለውጥ አካሄድ በቅርብ እንደምትከታተልም አድርጋለች። ሱዳናውያን አሁን ያሉበትን አስቸጋሪ ሁኔታ በመልካም ሁኔታ እንደሚያልፉትም እምነት እንዳለም ተመልክቷል።

ኢትዮጵያ የሱዳንን ሉዓላዊነትና የፖለቲካ ነጻነት እጥብቃ እንደምታከበር የገለጸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ፣ የሱዳን የፖለቲካ ባለድርሻ አካላት አሁን ላለው የአገሪቱ ሁኔታ ሰላማዊ መፍትሄ እንደሚፈልጉ እምነት እንዳለው ገልጹዋል።

ጃዋር መሀመድ በፊስ ቡክ ገጹ እንዳለው ” ለውጡ ለህወሃት አስደንጋጭ ነው” ብሏል። በሌላ በኩል ዜናው ለሌሎች ኢትዮጵያዊያን መልክም ዜና ላይሆን እንደሚችል ስጋቱን ጠቁሟል። የህገወጥ መሳሪያ ዝውውር እንዳይበራከት  ኢትዮጵያ ጉዳዩን በጥንቃቄ ማየትና ድንበሯን አጥብቃ መቆጣጠር እንዳለባት መክሯል።

Jawar MohammedAl Bashir’s removal is a blow to TPLF. However it might not necessarily be a good news for the rest of Ethiopia because instability in Sudan will further increase flow of weapons. Tighter border control is necessary.

ጃዋር ካለው በተቃራኒ ለውጡ የዓለም አቀፍ ለውጥ አካል ተደርጎ እንደሚታይና በዶከተር አብይ የሚመራው የምስራቅ አፍሪቃ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቁርኝት አካል እንደሆነ አስተያየት እየተሰጠ ነው። ልክ በግብጽ እንደተደረገው የወታደሩ ወደ ስልጣን መምጣት የውጭ ሃይሎች እጅ እንዳለበት አመላካች ነው ተብሏል። በተቀመጠው የሶስት ወር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጊዜ ውስጥ በሱዳን ፖለቲካዊ መረጋጋት እንዲኖር ድጋፍ መስጠት አግባብ እንደሆነ የሚጠቁሙ አሉ።

Image result for sudan protest

በማህበራዊ ገጾች ለአልበሽር ያላቸውን ፍቅር የሚገልጹ ወገኖች በሱዳን አለመረጋጋት እንደሚነግስ እየገመቱ ነው። እነዚህን ክፍሎች የሚቃወሙ ደግሞ በፕሬዚዳንት ኢሳያስና በአልበሽር መካከል የነበረው ችግር ለመጨረሻ ጊዜ ያከትምለታል እያሉ ነው። አያይዘውም በአፍሪካ ህብረትም ሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ያለተቃውሞ መመልከታቸው የዚሁ አመላክች ተደርጎ እንደሚወሰድ ይናገራሉ።

ለጀርመን ሬዲዮ አስተያየት የሰጡት አቶ አበበ አይነቴ በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስልታዊ ጥናት ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ እና በተለይም የጂኦ ፖለቲካዊ ጉዳዮች አጥኚ  ለውጡን ተከትሎ ስጋት እንዳይከሰት ስጋት አላቸው።
«በጦር ኃይሉ መካከል መከፋፈል የሚኖር ከሆነ ተቃውሞው መጣም ሊቀጥል ይችላል። ተቀውሞው የሚቀጥል ከሆነ ደግሞ የበለጠ የወታደራዊ ኃይሉ ጉልበት እንዲያገኙ እና ወደ ኃይልSudan Proteste gegen Präsident Omar Al-Bashir in Khartoum (picture-alliance/AP Photo)

እርምጃ ሊገባ ይችላል። ወደ ኃይል እርምጃ የሚገባ ከሆነ ደግሞ የአገሪቱ ሰላም ይናጋል በዚህም የብዙ ሰዎች መፈናቀል እና መሰደድ ሊኖር ይችላል»
በአቶ አበበ አስተያየት የሱዳኑ ተቃውሞ ቀጥሎ አለመረጋጋትን ካስከተለ ደግሞ በቀጣናው ሀገራት ላይ ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀርም።
«ደቡብ ሱዳን አልተረጋጋችም። ኢትዮጵያም የውስጥ ፖለቲካ ችግር አለባት ኤርትራም እንደዚሁ የኤኮኖሚ የፖለቲካ ማህበራዊ ችግር ያለባት ሀገር ነች። የሶማሊያ ጉዳይ ሌላው ራስ ምታት ነው። እንግዲህ በቀጣናው ያሉ ሀገሮች በሙሉ አቅማቸው የተከፋፈለ እና የየሀገራቱ ኤኮኖሚ እየተዳከመ የውስጥ ፖለቲካውም ያለመረጋጋት ሁኔታ ስላለ አጠቃላይ ይሄ ተደምሮ በቀጣናው ሰላም እና ደህንነት ጉዳይ ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ሚና ማሰደሩ የማይቀር ይሆናል።»

———————————————————————————————————————————————————-

Statement from the Ministry of Foreign Affairs of the Federal Democratic Republic of Ethiopia
Ethiopia is closely following current developments in sisterly neigbouring country, the Sudan.

Ethiopia expresses its confidence that the Sudanese will surmount this difficult moment. Ethiopia fully respects the sovereignty and political independence of the Sudan and sincerely hopes that all Sudanese political stakeholders will find a peaceful solution to the problem.

Ethiopia fully understands and respects the wishes of the Sudanese people and stands by them.

አልበሽር ከሥልጣን እንደሚወርዱ ሲጠብቅ የነበረው  ህዝብ በዋና ከተማይቱ በካርቱም ጎዳናዎች ደስታውን ሲገልጽ ቢውልም ከመከላከያ ሚኒስትሩ መግለጫ በኋላ ግን ስሜቱ ተቀዛቅዟል። በተለይ ለአራት ወራት የዘለቀውን ተከታታይ ተቃውሞ ሲያስተባብር የነበረው የሱዳን ሙያተኞች ማህበር ወታደራዊውን መፈንቅለ መንግሥትSudan - Alaa Salah - Die Sudanesin führt Proteste gegen Präsident Omar al-Bashir an (Getty Images/AFP)

እንደማይደግፍ አስታውቋል። ማህበሩ የአል በሽር አስተዳደር በሲቪል የሽግግር መንግሥት እንዲተካ እንጂ ሥልጣኑን ወታደራዊ ምክር ቤት እንዲይዝ እንደማይፈልግ አስታውቋል። አል በሽርን ያነሳው ጦር ኃይሉ ሥልጣኑን መያዙ በሀገሪቱ ለ4 ወራት ሲካሄድ የቆየውን ተቃውሞውን ሊያባባስ ይችላል የሚል ስጋት አሳድሯል።

አሜሪካ የሱዳንን መንግሥት ሽብርን  ይደግፋሉ ከምትላቸው ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ካስገባች ወዲህ ሱዳን ለረዥም ዓመታት ተገላ ነበር። አል በሽርም በዳርፉር ተፈጽሟል በተባለ የጦር ወንጀል በዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች  ፍርድ ቤት  2009 እና 2010 የእስር ማዘዣ ተቆርጦባቸዋል። ዛሬ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላም በዚሁ ምክንያት ወደ ሄጉ ፍርድ ቤት  ሊወሰዱ ይችላሉ የሚሉ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። የወታደራዊው ምክር ቤት ሊቀመንበር አውፍ የ75ቱ አል በሽር ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸው እና በአስተማማኝ ስፍራ እንደሚገኙ ነው የተናገሩት።

 

 

 

 

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *