ዛጎል ዜና – ከሙስና ጋር በተያያዘ ሲጠበቅ የነበረው የፌደራል ጠቅላይ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ መግለጫ እጅግ አነጋጋሪ ሆኗል። አቶ ብርሃኑ ” ጥቃቱ ደርሶ ቢሆን የሚፈጠረውን በማስታወስ እንዳሉት አገርና ህዝብን ክፉኛ ሀዘን ላይ የሚጥል ድግስ ተደግሶ ነበር።

ጉዳዩ በምርመራ ላይ በመሆኑ ዝርዝር መግለጫ እንደማይሰጡ በማስቀደም አቶ ብርሃኑ እንዳሉት ለኢትዮጵያዊያን ተደግሶ ነበር። እናም ሕዝብ በብዛት አዘውትሮ በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች፣ በመስብሰቢያ አዳራሾችና ማእከሎች ላይ ጉዳት ለማድረስ ነበር የታቀደው።

ውጥኑ ዓለም አቀፍ ከሆኑ አሸባሪዎች ጋር በጥምረት የተቀነባበረና ምርመራውም ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው በመሆኑ ለጊዜው ማብራሪያ እንደማይሰጡ ያስታወቁት አቶ ብርሃኑ፣ ተጠርጣሪዎቹ ሲያዙ የተገኙ ማስረጃዎች የጥቃት ኢላማዎቻቸውን የሚያሳዩና እቅዳቸውን የሚያስረዱ ሆነው ተገኝተዋል።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

ለጥቃት የተመረጡ ቦታዎችን በፎቶ ምስል የያዙበት ማስረጃ፣ የተለያዩ የማንነት ሰነዶች፣ የውጭ አገር ፓስፖርቶችና የሽብር ጥቃቱን ለማከናወን የሚያስችል ዝግጅት ያቀናበሩበት እቅድና፣ እቅዱ እንዴት እንደሚተገበር የተነደፈው እቅድ ተጠርጣሪዎች እጅ ላይ ተገኝቷል።

ስለ ተጠርጣሪዎች ማንነትና አገር ምንም ፍንጭ ያልሰጡት አቃቤ ህጉ፣ በተመሳሳይ አሁራፊ የሴራ ፖለቲከኞች ከዚህ ድርጊት ጀርባ ስለመኖራቸውን ያሉት ነገር የለም። ምርመራው ሲጠናቀቅ ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን ግን አልሸሸጉም።

ቀደም ባሉት ወራቶች በሶማሌ ክልል የሽብር ጥቃት የመፈጸምና መነሻቸውን ከዛ ያደረጉ የሽብር መልዕክተኞች በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ጉዳት ለማድረስ ዝግጅት እንዳላቸው መረጃ እንዳለ የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዚዳን መናገራቸው ይታወሳል። በዚም ሳቢያ አስፈላጊው ጥንቃቄ ከፌደራል ጋር በተቀናጀ መልኩ እንደሚደረግ አስታውቀው ነበር።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

የዛሬው የአቃቤ ህግ ብርሃኑ መግለጫ ከዚህ ጋር ይያያዝ አይያያዝ የታወቀ ነገር የለም። የፌደራል የመረጃና የደህንነት ክፍሉ ይህንን የተቀነባበረ ድርጊት አስቀድሞ በማክሸፉ ምስጋና የቸሩት አቶ ብርሃኑ ህብረተሰቡንም አመስግነዋል። ህዝቡ አሁንም በተመሳሳይ ድጋፉን እንዲያደርግ ጠይቀዋል። ህዝቡ ባይጠየቅም ድጋፉን እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። ተጠርጣሪዎቹ በእጃቸው በተያዙ ሰነዶች መሰረት የሽብር ጥቃቱን ቢፈፀሙ የከፋ ጉዳት ሊያደርሱ ይችሉ እንደነበር ግን ደጋግመው አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ሃላፊነት ከመጡ ጊዜ አንስቶ ዘመናዊ የመረጃ ቢሮ ለማድረግ ስር ነቀል ለውጥ ማካሄዳቸው፣  በአጭር ጊዜ፣ በአነስተኛ ወጪ ተልዕኮውን የሚፈጽም የመከላከያ ሃይል እንዲገነባ ከፍተኛ የሪፎርም ስራ እንደተሰራ በተደጋጋሚ መናገራቸው የሚታወስ ነው። የቀደመውን የድህንነት መዋቅርና አሰላለፍ የቀየሩት ዶክተር አብይ አሜሪካና ፈረንሳይ ከፍተኛ ድጋፍ እንዳደረጉላቸው ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ አካላት ይናገራሉ። በመከላከያ ውስጥ የተካሄደውን ሪፎርም አስመልክቶ ማንም በቀላሉ ሊዘውረው የማይችል ለአገሩ ታማኝ የሆነ አመራርና ሰራዊት መዋቀሩን፣ ይህም ፈረንሳይና አሜሪካ በግናብር ቀደም ድጋፍ የሚያደርጉለትና በበጀትም ቢሆን ከፍተኛ እገዛ እየተደረገለት ያለ ተቋም ነው።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ከቀድሞው በተለየ በእኩል የብሄር ተዋእጾ የተገነባው የመከላከያ ሃይል ላለፉት ዘጠኝ ወራት እንዲዘመን መደረጉን ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸው አይዘነጋም።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *