ጠቅላይ አቃቤ ህጉ አቶ በርሃኑ ፀጋዬ በሰጡት መግለጫ እንደጠቆሙት፥ በሶስት የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ውስጥ ከተፈፀሙ የሙስና ወንጀሎች ጋር በተያያዘ የተቋማቱን የስራ ሀላፊዎች እና ባለሀብቶች ጨምሮ 59 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል።

አቶ ብርሃኑ በመንግስት ተቋማት እና ፕሮጀክቶች ላይ የተፈፀመ ከባድ ወንጀሎችን በተመለከተ ባለፉት 3 ወራት ምርመራ መደረጉን ተናግረዋል። በዚህ ምርመራም በወንጀሎቹ የደረሰውን ጉዳት እና ተጠርጣሪዎቹ ያደረሱትን ብክነት ተመርምሯል ነው ያሉት።

በብዛት ሙስና ይፈፀማል ተብሎ የሚታመነው በግዢ ሂደት በመሆኑ በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ተቋም ላይ ምርመራ ተካሂዷል ብለዋል።

ይህ ተቋም ላይ በተካሄደው የምርመራ ውጤት መሰረትም ከ400 ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዢ ጋር በተያያዘ በጥቅም በመመሳጠር ተጠርጣሪዎቹ በመንግስት ላይ በአጠቃላይ 23 ነጥብ 7 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል። ከዚህ ግዥ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎቹ የዳቦ እጥረት እንዲከሰት በማድረግ በህዝብ እና በመንግስት ላይ ተፅዕኖ ማድረሳቸው ተነግራል፡፡

ከኮምፒውተር ግዥ ጋር ተያይዞ የቴክኒክ ምርመራ ያለፉ አቅራቢ ድርጅቶ እያሉ ምርመራውን ካላለፉ ተቋማት ግዥ እንዲፈፀም ተደርጓልም ነው ያሉት፡:

በውሃ ስራዎች ኮንስትራክን ኮርፖሬሽን ውስጥ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች እርስ በርሳቸው በመመሳጠር ከ55 ሚሊየን ብር በላይ ያለ አግባብ በተፈፀመ የብረት ግዢ ውስጥ የተፈፀመ የሙስና ወንጀል መኖሩንም ገልጸዋል።

እንዲሁም የመድሃኒት ፈንድ ኤጀንሲም ከግዥ ስርዓቱ ውጭ የ79 ሚሊየን ብር ግዥ መፈጸሙን አቃቢ ህጉ አንስተዋል።

በአመራሮች ላይ እየተካሄደው ባለው ማጣራት ካላቸው ገቢ በላይ ንብረቶችን አፍርተው እንደተገኙ መረጋገጡንም ነው የተናገሩት። የባለሃብቶቹ ስም ዘርዘር ግን ይፋ አልተደረገም።

ፎርቹን እንዳለው ስልሳ አንድ ባለስልጣናት መታሰራቸውን በሚከተለው መልኩ ማለዳ ላይ አስቀድሞ አስነብቧል።

Fed Police Arrest 61 Government Officials

Federal Police have arrested Yigezu Daba, director general of the Public Procurement & Property Disposal Service and 60 other government officials on suspicion of corruption and economic sabotage.

Officials from the then Ministry of Finance, Economics & Cooperation, the Public Procurement & Property Disposal Service, the Food & Drug Administration Agency, the Pharmaceuticals Fund & Supply Agency and the Ethiopian Water Works Construction Enterprise were also arrested yesterday, April 11, 2019, by a police operation that began early in the morning. The Office of the Attorney General is expected to give a press conference late in the afternoon today.

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *