የእስራኤል የእሳት አደጋ መከላከል ባለሙያዎች ለአምስት ቀናት በፓርኩ ይቆያሉ፤ ባለሙያዎቹ ነገ ጠዋት አዲስ አበባ ይገባሉ።

እስራኤል ዓለማቀፍ ልምድ ያላቸውን የእሳት አደጋ መከላከል ባለሙያዎች ወደ ፓርኩ እንደምትልክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ገልጿል።

በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ላይ የተነሳውን ቃጠሎ የመቆጣጠር ስራ ለማገዝ የሚመጡት ከ7 እስከ 9 የሚሆኑ እስራኤላውያን ናቸው። አውሮፕላን ወይም ሄሊኮፕተር ግን ይዘው እንደማይመጡ ነው ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ባለሙያዎቹ ከነሙሉ የእሳት አደጋ መከላከያ መሳሪያና ሀኪሞቻቸው ነገ ጠዋት 12:00 ላይ አዲስ አበባ እንደሚገቡ የደንና ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ ተናግረዋል። ወዲያኑም ወደ ጎንደር እንደሚያቀኑ ታውቋል።

ለአምስት ቀናትም ፓርኩ እየተቃጠለ በሚገኝበት ቦታ ሆነው የመቆጣጠር ስራውን ያግዛሉ ነው ያሉት አቶ ኩመራ። ልምዳቸውን ተጠቅመውም የተሻለውን የመቆጣጠሪያ መንገድ ለመተግበር እንደሚያግዙ ይጠበቃል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

እንደ አቶ ኩመራ መረጃ ኬንያ በ “ማውንት ኬንያ ብሔራዊ ፓርክ” ላይ ቃጠሎ ተከስቶ እሳቱን በማጥፋት ላይ በመሆናቸው ሄሊኮፕተሮቿን ከፊታችን ማክሰኞ በፊት እንደማትልክ ታውቋል። ከደቡብ አፍሪካ ይመጣሉ ስለተባሉትም “ለመምጣት ዝግጁ ናቸው” ከሚል መረጃ የተለዬ ተጨባጭ ውጤት አለመኖሩን ነው የተናገሩት።

ከአካባቢው ነዋሪዎች ጥረት ውጪ ተጨባጭ ዘመናዊ የመከላከል ስራ እስካሁን አልተጀመረም። በፓርኩ ላይ የጀመረው እሳትም በአሳሳቢ ደረጃ መስፋፋቱን ቀጥሏል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ዘጋቢ፦ አስማማው በቀለ

Amhara media agency

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *