የአማራ ክልል አካባቢ ደንና ዱር አራዊት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክትር በላይነህ አየለ ለአማራ መገናኛ ብዙሃን  እሳቱን መቆጣጥር እንደሚል ከፓይለቱ  ማረጋገጫ ማግኘታቸውን አስታወቁ።

ከኬንያ የመጣችው ሄሊኮፕተር የመርጨት ስራ መጀመሯን፣ የውሃ አቅርቦትና አስፈላጊ ነገሮች መሟላታቸውን፣ ፓይለቶቹ እሳቱ ያለበትን ቦታ ካዩም በሁዋላ በአፋጣኝ እንደሚያጠፉት ማረጋገጫ መስጠታቸውን ነው ዶክተሩ የተናገሩት።

በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት፣ በውጭ ጉዳይ፣ አደጋ መከላከል በጋር መስራታቸውን ያስታወቁት ዋና ዳይሬክተሩ ” እሳቱን ለማጥፋት ቀን መቁረጥ ይቻላል” ከዘጋቢው ተጠይቀው ” ፓይለቱ ማስተማመኛ ሰጥቷል፤ እንደሚያጠፋው ነገሮናል፤ ቀን ግን መቁረጥ አይቻልም፤ ስራው ገና መጀመሩ ነው” ሲሉ መልሰዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

እሳቸውና የዞኑ አስተዳዳሪ ዘመቻውን እየመሩ መሆናቸውን ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል። ሄሊኮፕተሯ በአንድ ምልልስ ፩፫፻ ሊትር ወሃ እንደምትረጭ ያስታወቁ ሲሆን ነዶ የከሰመው ረመጥ ሰፊ ሽፋን መያዙን አመልክተዋል።

የስራኤል ባለሙያዎች ራሳቸውን ችለው መረጃ የመሰብሰብ ስራ እንደሚሰሩም ገልጸዋል። መርጃም እየሰበሰቡ ወደ ኤምባሲያቸው እንደሚልኩና በቀጣይ በሰበሰቡት መረጃ መሰረት መን መደረግ እንዳለበት ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከእስራኤል አቻቸው ጋር ከተወያዩ በሁዋላ ወደ ኢትዮጵያ መተው ቃጠሎ ወዳለበት ስፋር ያመሩት ባለሙያዎች በዘላቂ እርዳታ ዙሪያ እንደሚሰሩ ግምት አለ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *