እነ አቶ በረከት ላይ አንድ ሺህ ዘጠኝ ገጽ የያዘ የክስ ፋይል ቀረበባቸው፣ አንብበን ለመጨረስና የእምነት ክህደት ቃላችንን እስክንሰጥ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠን ማለታቸው ታወቀ። የክሱ ዝርዝር የተሰጣቸው ማታ መሆኑንንም አመልክተዋል። ፋና ይህንን ዘግቧል።

የአማራ ክልል ፀረ ሙስና አቃቤ ህግ በአቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ ላይ ክስ መሰረተ። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት በጥረት ኮርፖሬት ላይ ፍተኛ የሀብት ብክነት በማስከተል የተጠረጠሩትን አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳን ጉዳይ ተመልክቷል።

የሁለቱን ተጠርጣሪዎች ክስ በአንድ ላይ ለማዳመጥ የተሰየመው ችሎቱ ተከሳሾች የተከሰሱበት ዝርዝር ጉዳይ በትናንትናው ዕለት ለተከሳሾቹ በፅሑፍ መድረሱን ገልጿል።

ተከሳሾች በበኩላቸው የክስ መዝገቡ በትናንትናው ዕለት 12 ሰዓት ላይ እንደደረሳቸውና ገፁ 1 ሺህ 9 መሆኑን በመግለፅ በአግባቡ አንብበውና ተገንዝበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ተጨማሪ ጊዜ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ተከሳሾቹ ጠበቃ ማቅረብ ባለመቻላቸው በውጭ ጠበቃ አቁመው በፕላዝማ እንዲከታተሉ የሚደረግብት ሁኔታ እንዲፈጥርላቸው ጠይቀዋል።

ይህ ካልሆነ ደግሞ የህግ አማካሪ ባለሙያ እንዲፈቀድላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

የግራ ቀኙን ሃሳብ ያዳመጣው ፍርድ ቤቱም ተከሳሾች ጠበቃቸውን ማቆም ይችሉ ዘንድ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ትብብርና ጥበቃ እንዲያደርግላቸው ትዕዛዝ አስተላልፏል።

በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች ያቀረቡትን አቤቱታ ግምት ውስጥ በማስገባት በክሱ ላይ ያላቸውን ሃሳብ ለማዳመጥ ለሚያዚያ 14 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በናትናኤል ጥጋቡ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *