“Our true nationality is mankind.”H.G.

ጤና ጥበቃ በግል ህክምና ኮሌጆች የሚመረቁ ዶክተሮችን መቅጠር አቆመ፤ ባለሙያዎቹ ቅሬታ አቀረቡ

ቅሬታው ተገቢ ቢሆንም ከዚህ  ቀደም የግል የህክምና ኮሌጅ ተማሪዎችን ከተግባር ልምምድ እስከ መቅጠር ደረጃ ያደረስነው በወቅቱ የህክምና ባለሙያ እጥረት ስላጋጠመ ነው

ቅሬታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያቀረቡ ዶክተሮች ከአራት ወራት በላይ ሳይቀጠሩ መቆየታቸውንና ለመመረቅ የተግባር ስልጠና የሚቀራቸው የህክምና ባለሙያዎችም ወደ ተግባር ልምምድ መግባት አለመቻላቸውን ተናግረዋል። የአለም ጤና ድርጅት መስፈርት በአፍሪካ ደረጃ አንድ የህክምና ባለሙያ ለ 10 ሺ ሰው ማገልግል ይኖርበታል ይላል።

የድርጅቱ መስፈርት ይህ ቢሆነም ኢትዮጵያ ካለው የባለሙያ እጥረት አንፃር አንድ የህክምና ባለሙያ ለ25 ሺህ ሰው እያገለገለ እንደሚገኝ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት።

ይህን ባለሙያ ማፍራት የተቻለውም ከ 2009 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስልጠና የሚገቡ የህክምና ባለሙያዎችን ቁጥር በዓመት ወደ 3 ሺህ ከፍ ማድረገ በመቻሉ ነው።

እንደሚታወቀው የህክምና ባለሙያዎችና እና መሳሪያዎች በበቂ ሁኔታ ባመመኖራቸው ሳቢያ ከፍተኛ ወጭ አውጥተው ወደ ባህር ማዶ ሄደው የሚታከሙ ሰዎች ቁጥር ጥቂት አይደለም። እንዲሁም ህክምናም ሳያገኙ ሀይወታቸው የሚያልፉ በርካታ ሰዎች መኖራቸውማያታበይ ሀቅ ነው።

Related stories   የሲኤንኤን ዘጋቢ ኒማ- በተወነችው ተውኔት ውስጥ ዳግም ሞት የተፈረደባቸው ዜጎች

ነባራዊ ሁኔታው ይህ ሆኖ እያለ ሙያውን ይዘው ቀጣሪ አጣን የሚሉ በርካታ የህክምና ዶክተሮችም ማየት ደግሞ ግርምትን ይጭራል።

ዶክተር ሰኢድ አህመድ በአዲስ አበባ ሀያት ሜዲካል ኮሌጅ ከ 6 አመት በላይ የህክምና ትምህርቱን ተከታትሎ ከተመረቀ ከ አራት ወር በላይ ሆኖታል።

ትምህርት እንደጨረሰ ወዲያዉኑ በመንግስት ተመድቦ ስራ ላይ ሆኖ ህዝቡን ማገልገል እና እራሱም ለትምህርት ያወጣውን ወጭ መመለስ ቢያስብም ሊሆንለት አልቻለም።

እንደ ዶክተር ሰኢድ ሁሉ ከሀያት ሜዲካል ኮሌጅ ፣ ከአፍሪካ ሜዲካል ኮሌጅ እና ሌሎች የግል የህክምና ማሰልጠኛ ተቋማት የተመረቁ እና ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ላይ የሚገኙ ከ 800 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ቅሬታም ይህ ነው።

ተማሪዎቹ ምንም እንኳ የሙያ ፈቃዳችን ቢሰጠንም እንኳ ሌሎች ቦታዎች ላይ ለመወዳደር አልቻልንም፣ እድሉም እየተሰጠን አይደለም፣ በግላችን የህክምና ተቋም ለመክፈት ደግሞ የሙያ ፈቃዳችን የአገልግሎት ጊዜ ስለሚያስፈገው ከሁሉም ውጭ ሆነናል ይላሉ።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

ወደ ተግባር ልምምድ መግባት የነበረባቸው የመጨረሻ አመት ላይ የሚገኙ ተማሪዎችም የተግባር ልምምዱን መጀመር ከነበረብን ከ3 ወር በላይ አልፎናል፤ስለሆነም መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጠን ይገባል ነው ያሉት።

የጤና ሚኒስቴርም የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ደምሴ ቅሬታው ተገቢ ቢሆንም ከዚህ  ቀደም የግል የህክምና ኮሌጅ ተማሪዎችን ከተግባር ልምምድ እስከ መቅጠር ደረጃ ያደረስነው በወቅቱ የህክምና ባለሙያ እጥረት ስላጋጠመ ነው ብለዋል።

በዚህም ከኮሌጆቹ ጋር የውስጥ ስምምነት በማድረግ የባለሙያዎች እጥረት እስኪቃለል ድረስ በመንግስት ሆስፒታሎች ስንቀጥር ነበር ነው ያሉት አቶ ሀብታሙ።

አሁን ላይ የባለሙያ ችግሩ ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል ባይባልም ችግሩ በመቃለሉ የመንግስት ተመራቂዎችን ብቻ ወደ መቅጠሩ ተዛውረናል ያሉት ዳይሬክተሩ፥ከህዳር ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ ኮሌጆቹ እንዲያውቁት መደረጉንም አንስተዋል።

በግል እየተመረቁ ያሉ የህክምና ዶክተሮችን እንቅጠር ብንል እንኳ ያሉን የጤና ተቋማት የባለሙያ ፍላጎታቸው አሁን ያለውን ማስተናገድ የሚችሉ አይደሉም ነው ያሉት።

ለዚህም የጤና ተቋማት አለመስፋፋት እና የበጀት ጉዳይ ዶክተሮችን መቅጠር እንዲቆም ካደረጉ ምክንያቶች ውስጥ ተጠቃሾች ናቸው ብለዋል።

Related stories   ኦሮሞ ኦሮሞን አድፍጦ እየገደለ ነው፤ ኦነግ ሸኔ ለስራ የሚጓዙ አምስት ኦሮሞዎችን ገደለ

በጀት በክልሎች የሚያዝ በመሆኑ እና በጀቱም በአመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚያዝ መሆኑ የህክምና ተማሪዎች የሚመረቁበት ጊዜ ደግሞ በተለያየ ጊዜ አመቱን ሙሉ መሆኑ እንኳን ለግል ተመራቂዎች ይቅር እና የመንግስቶቹንም እንዳናስተናግድ እንቅፋት ሆኗል ብለዋል።

በዚህ ምክንያትም በመንግስት ከሚመረቁት የህክምና ባለሙያዎች ውስጥ በ8 ሙያዎች ብቻ እየተመደበ ሲሆን ከ5 በላይ በሚሆኑ ሙያዎች ምደባ እያከናወን አይደለም ነው ያሉት።

ይሀን ችግር ለመፍታት ከዚህ በኋላ ፍላጎትን ያመጣጠነ ስልጠና እንዲሰጥ ከተለያዩ ተቋማት ጋር እየተነጋገርን እንገኛለን ነው ያሉት ዳይሬክተሩ።

እነዚህ በግል የተመረቁ ዶክተሮች በተሰጣቸው የሙያ ፈቃድ በየትኛውም ቦታ የስራ አገልግሎት ሳይጠየቁ የግላቸውን ስራ እንዲሰሩ እንዲሁም በየክልሎቹ የሚወጡ የመንግስት ክፍት የስራ ቦታዎች ካሉ እንደ መንግስት ኮሌጅ ተመራቂዎች እኩል ቦታ እና ውድድር እንዲያገኙ ለሁሉም ክልሎች በደብዳቤ ማሳወቁን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0