በጀነራል ዋቆ ጉቱ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል የገቡ ተማሪዎች በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ዛሬ ከሰዓት በትምህርት ቤቱ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ 37 ተማሪዎች ራሳቸውን ስተው መውደቃቸውን እና አስፈለጊው የህክምና ድጋፍ ተደርጎላቸው አብዛኞቹ ተማሪዎች ወደ ቤታቸው መመለሳቸው ተገልጿል።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ እንደገለጹት ራሳቸውን ስተው የወደቁ ተማሪዎችን ወደ ቤቴል ሆስፒታ እንዲወሰዱ በማድረግ ህክምና ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

ህክምና ከተደረገላቸው በኋላም 34 የሚሆኑ ተማሪዎች ተሽሏቸው በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙና ሶስቱ ተማሪዎች ተጨማሪ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቤተል ሆስፒታል በተደረገው ምርመራ ይሄነው የሚባል ውጤት ባለመገኘቱ የታካሚዎቹ የደም ናሙና ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል መላኩን ከአዲስ ቲቪ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

FBC

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *