አምቦ በተካሄደ የኦሮሞና አማራ ሕብረት ስብሰባ ላይ ተስፋዬ ገብረአብ የፈጠራ ታሪክ በማሳተም ኦሮሞና አማራ አንዲጫረሱ ምክንያት አንደነበር፣ ይህንንም ሲያደርግ የነበረው በጀት ተፈቅዶለትና ዓላማና ግብ ተቀምጦለት አንደነበር መናገራቸውን ተከትሎ አነ ጃዋር መሐመድ በአቶ አዲሱ ላይ ዘመቻ አቀጣጠሉ።
ከጅምሩ ተስፋዬ መነካት አንደሌለበት ያስጠነቀቀው ጃዋር በቅርቡ የሚዲያና የፖለቲካ ስራውን ሳያምታታ አንደሚሰራ ኣስታውቆ ነበር። ይሁን አንጂ ቀደም ሲል ሲጠቀምበት የነበረውን ኔት ዎርክ ለዚሁ ተግባር ማዋሉ ታውቁኣል። ሚዲያውንም ለዚሁ ቅስቀሳ ተጠቅሟል።
በመዋቅሩ መሰረት በተለያዩ ቦታዎች አቶ አዲሱ ከሃላፊነታቸው አንዲነሱ፣ አንዲቀጡና በኦሮሞ ህዝብ ላይ ሃጢያት አንደሰሩ ተደርጎ ተቃውሞ እንዲነሳባቸው ተደርጉዋል። ተቃውሞው ተጠናክሮ አንደሚቀጥልም ተመልክቷል። መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ ያለው ነገር የለም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *