የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ሊወያዩ ነው።

ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመወያየት በያዝነው ሳምትን ወደ ሞስኮ የሚያቀኑ መሆኑን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንት ኪም ወደ ሞስኮ የሚያቀኑበት ትክክለኛ ቀን በዘገባው አልተጠቀሰም ።

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች የሚያደርጉት ይህ ውይይት ከአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2011 ወዲህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል ። ውይይቱ ፕዮንግያንግ ከዋሽንግተን ጋር በኒውክሌር ዙሪያ ያደረገችው ውይይት ያለ ስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ የሚደረግ መሆኑ ለሀገሪቱ ልዩ መልዕክት ያለው መሆኑ ተገልጿል።

እንዲሁም በሰሜን ኮሪያ ላይ የተጣሉ ዓለም አቀፍ ማዕቀቦች በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ ለመቀነስ ያለመ ነው ተብሏል። ኪም በሞስኮ ከፑቲን ጋር በሚኖራቸው ቆይታም በሀገራቱ መካከል ተቀዛቅዞ የቆየውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በጥልቀት ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

ከዚህ ባለፈም የተቋረጠው የፕሬዚዳንት ኪም እና ፕሬዚዳንት ትራምፕ የኒውክሌር የጦር መሳሪያ ስምምነት በድጋሜ ሊካሄድ በሚችልባቸው መንገዶች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል ። በተጨማሪም በሩሲያ ምስራቃዊ ግዛት በምትገኘው ቭላዲቮስቶከ የወደብ ከተማ ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥተው የሚወያዩ መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ – FBC

Related stories   መከላከያ ጸጥታ እንዲያስከበር ታዘዘ፤ አብዲ ተነስቶ አዲስ መሪ ተሰየመ፤ ቤተክርስቲያን አወገዘች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *