በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ፍተሻ መጀመሩን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ አስታወቀ። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንዱአለም አድማሴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ከኤጀንሲው እውቅና ውጭ ተሰማርተው የሚገኙ ተቋማት ላይ እስከ መዝጋት የሚደርስ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል።

 በኢትዮጵያ የሚገኙ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ሲነጻጸሩ ከ2 እጥፍ በላይ የሚሆኑት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ናቸው። እነዚህ ተቋማትም ላለፉት 20 ዓመታት የትምህርት ኢንዱስትሪውን በመደገፍ በኩል ትልቅ ድርሻን እየተወጡ ይገኛሉ። ነገር ግን ተቋማቱ ላይ የትምህርት ጥራት፣ የግብዓት እጥረቶች እና ሌሎች ችግሮች ጎልተው እንደሚታዩባቸው ተደጋግመው ሲነሱ ይስተዋላል። እነዚህ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ካላቸው ተልዕኮ አንፃር የሚጠበቅባቸውን ግብ እንዲያሳኩ መሟላት የሚገባቸውን ነጥቦች አስተያየት ሰጭዎቹ ያነሳሉ።

ተቋማቱ ያሉባቸውን ችግሮች እንዲቀርፉም መንግስት ያለው ትኩረትን ከማጠናከር ጀምሮ የራሱ የሆነ አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ እንደሆነም ያብራራሉ። የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ መረጃ እንደሚያመለክተው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ 174 በላይ የሚሆኑ እውቅና የተሰጣቸው የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አሉ። እነዚህ ተቋማትም በ 10 ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በየ አመቱ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስመርቃሉ።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

ኤጀንሲውም እነዚህን ተቋማት የስራ ፈቃዳቸውን በየ ሶስት አመቱ እንደሚያድስ እና ከህዝብ በሚደርሰው ጥቆማ ተቋማቱ ላይ ፍተሻ እና ቁጥጥር ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህ ዓመትም በአዲስ አበባ እና ዙሪያ በሚገኙ ተቋማት ላይ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ በርካታ ግድፈቶችን አግኝቷል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንዱአለም አድማሴ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ከ 1 መቶ በላይ በሚሆኑ ተቋማት ላይ በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 46 አይነት ግድፈቶች ተገኝተዋል። ከእነዚህም ወስጥ 27 ኮሌጆች እራሳቸውን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ብለው መሰየማቸው ታውቋል።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

በዚህም ለሁለት አመት ትምህርት እንዳይሰጡ ማደድረግና ከነጭራሹ እንዲዘጉ እስከማድረግ የሚዘልቅ ቅጣት ተጥሎባዋቸዋል ብለዋል ዶክተር አንዱአለም።እርምጃ እንዲወሰድባቸው ካደረጉት የፍተሻ መስፈርቶች ውስጥ ህጋዊ ሰነድ አለማሟላት፣ ስለሚሰጧቸው የትምህርት ዘርፎች እውቅና እንዲሁም የሚያስተምሩበት ካምፓስ እውቅና የሌለው መሆን ዋና ዋናዎቹ ናቸው ብለዋል።

ከእነዚህ ተቋማት ወስጥም 13ቱ የትምህርት ዘርፍ ባልሆነ በድለላ፣በጽህፈት መሳሪያና የማሽን ኪራይ ፍቃድ ሲሰሩ የተደረሰባቸው ናቸው። ከሁለት ዓመት እገዳ እስከ ካምፓስ መዝጋት እረምጃ ከተወሰደባቸው ተቋማት ውስጥም ኪያሜድ ኮሌጅ፣ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ እና ሀራምቤ ኮሌጆች ይገኙበታል።

ከኤጀንሲው እርምጃ በተጨማሪ በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ተማሪዎቻቸውንም በ15 ቀናት ውስጥ እንዲያሳውቁ ውሳኔ አሳልፈናለም ነው ያሉት። በአጠቃላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚገኙትን ተቋማትም የመፈተሽ ስራ መጀመሩን ነው ዶክተር አንዱአለም የነገሩን።

ፍተሻው አሁን የተፈተሹትንና እርምጃ የተወሰደባቸውነም የሚያካትት ሲሆን፥በመስፈርቱ መሰረት የተማሪ መቀበያ ነጥብ፣የትምህርት አይነቶች፣ የመምህራን ብቃት፣ የግብአት ሁኔታና አጠቃላይ ሬጅስተራቸው የሚፈተሽ ይሆናል።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

ከዚህ በኋላ ፍተሻው በተከታታይነት የሚካሄድ መሆኑን ያለሱት ዳይረሬክተሩ፥ቀጣይነቱም ተቋማቱን በማጥራት የትምህርት ጥራቱ እንዲጠበቅ ከማድረግ በተጨማሪ ተማሪዎች ላይም የሚደርሰውን ኪሳራ እና የስነ-ልቦና ጫና ለመቆጣጣር ያስችላል። ለዚህም ባለሙያዎች ሰልጥነው ስራ ጀምረዋል ነው ያሉት ዶክተር አንዱአለም።

ኤጀንሲወ በቀጣይ ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል የዳታ ቤዝ  ወይም የመረጃ ቋት ስርዓት እየዘረጋ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። የመረጃ ቋቱም ተቋማቱ የሚያስተምሯቸውን ተማሪዎች እና መስፈርቶቻቸውን መከታተል፣ስራ ቀጣሪ ተቋትም መስፈርቱን ያሟሉ ተማሪዎችን እና ተቋማትን ለማወቅ የሚቻበት ነው።

አዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት እና ክትትሎችን በማድረግም አሁን ባሉትና አዲስ በሚከፈቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከሚታዩ ስህተቶች ነጻ በማድረግ፥የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ታስቦ እየተሰራ መሆኑን ኤጀንሲው ገልጿል።

በዙፋን ካሳሁን

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *