አጫጭር ዜናዎች
“እንዲህ ወረኛ ሆነን መቅረታችን ያሳዝናል” ሙሉቀን መለሰ
” እንዲህ ወረኛ ሆነን መቅረታችን ያሳዝናል ” ሲል ባለ ብዙ ዝና ሙሉቀን መለሰ ሃዘኑን ገለጸ። የሸገር ሬዲዮ ” ታማኝ ምንጮቼ ነገሩኝ” ሲል ሙሉቀን መለሰ ህይወቱ ማለፉን በይፋ ድረገጹ አትሞ ነበር። ዜናውን ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያዎችና በተለያዩ መገናኛዎች እንደ ሰደድ እሳት የተራባውን የሙሉቀን መለሰ ህልፈት ከሰዓታት በሁዋላ ሽገር ሬዲዮ ማስተካከያ አቅርቧል። ሙሉቀንም በዚሁ ማስተካከያ ስርጭት ላይ ነው ማዘኑን የገለጸው።
ወሬው የፈጠራ መሆኑንን ያመለከተው ሙሉ ቀን ” በፈጠራ ወሬ እዚህ አገር ዶላር ይከፈላቸዋል” ብሏል። ከቀድሞው በተሻለ ሁኔታ በመልካም ሁኔታ እንደሚገኝም አስታውቋል። ሸገር የሚያምናቸው ምንጮቹ ከአሜሪካ የተሳሳተ መረጃ አቀብለውት የህልፈት ዜና መስራቱን በመጠቆም ሙሉቀንን በቀጥታ በስልክ ሲያነጋግር እንደተደመጠው፣ በንግግሩ የጸና ህመመተኛነት ምልክት እንኳን አይስተዋልም።
ሙሉቀን መናገር እየፈለገ በምስጋና በተቋጨውና ዓላማው የእሱን በህይወት መኖር ለመግለጽ በተሰራጨው አጭር ቃለ ምልልስ ” … እንዲህ ወሬኛ ሆነን መቅረታችን ያሳዝናል” ሲል የገለጸው በሃዘን ስለመሆኑ ግን ንግግሩ ያሳብቃል።
ዜናውን ፈጥረው ያራቡ ወገኖች ከዚህ መሰሉ ክፉ ተግባር ምን እንደሚጠቀሙ ግልጽ ባይሆንም ” እዚህ ሃገር ዶላር ይከፈላቸዋል” ሲል ሙሉቀን ያስተላለፈው መልዕት የሚሰመርበት ነው። በኢትዮጵያ አሁን የተያዘው የተገኘውን ሁሉ ዓየር ላይ ማዋልና ሳንቲም መልቀም መሆኑ ብዙዎችን እያሳሰበ ነው።
በመቶ የሚቆጠሩ የጉምዝ ተወላጆች ህይወት አለፈ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ የእንባ ጠባቂን ለኦ ኤም ኤን እንዳሉት በስም ያልገለጿቸው ታጣቂዎች በመቶ የሚቆጠሩ ጉምዞችን ገለዋል። ግድያው ህጻናትና ሴቶች ላይ ያነጣጠረ መሆኑም ታውቋል። አሁን ስፍራው ሙሉ በሙሉ በመከላከያ ቁትትር ስር ሲሆን አካባቢው ተረጋግቷል። ቀደም ሲል በተካሄደው ግድያ የተጠረጠሩ ፫፫ ሰዎች መያዛቸውን የክልሉ ፖሊስ ይፋ አድርጓል። አንድ የፖሊስ አባልም ይገኝበታል። አሁን ተፈጸመ ስለተባለው ግድያ በይፋ መንግስት ለጊዜው ያለው ነገር የለም።