” ህዝብ እንደ ጎርፍ የሚነዳበት ምክንያት አይገባኝም። ከለውጡ ማግስት ጀመሮ በክላችን ስራ የለም። ሞት፣ እሳት፣ ነውጥ፣ የሴራ ፖለቲካ፣ መከፋፈል፣ አለመግባባት፣ መጠራጠር፣ መፈናቀል… ባቻ ነው የሚታየው። ውሎ እያደረ እየሰመጥን ነው። ለምን ማስተዋል እንደተሳነን አይገባኝም። የአማራ ክልል ህዝብ በተለይም ወጣቱ ቢያስብ ይሻለዋል። ቢሰክን ይሻለዋል። የሚሰፈርለት አጀንዳና የሚጠመድለት ፈንጂ ላይ እየጋለበ አገር አልባ እንዳይሆን እሰጋለሁ”

የአማራን ክልል በተለያዩ አጀንዳዎች በመወጠር ከለውጥ ማግስት አመራሩ  ስትራቴጂክ የሆኑ ሥራዎችን ላይ አተኩሮ እንዳይሰራ መደረጉ ተገለጸ። ጥፋትን በጥፋት የመመለስ አካሄድ በትግል እንደሚሸነፍም ተመልክቷል። ይህን ያሉት የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ ናቸው።

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞንና ጃዊ አካባቢ ማንነታቸው ተረጋግጦ ባልተገለጸ ሃይሎች ተፈጸመ የተባለውን ግድያ አስመልክተው መግለጫ የሰጡት አቶ አሰማኸኝ፣ ድርጊቱን አውግዘዋል። ፍጹም ተቀባይነት የሌለውንና ከክልሉ ሰላማዊ ህዝብ ጋር በመሆን እንደሚታገሉትም ተናግረዋል። ከተለያዩ ጉዳዩ መከላከያን ጨምሮ ከሚመለከታቸው አካላትና ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ጋር  አጥፊዎችን የመለየትና በህግ ጥላ ስር የማዋል ስራው ሲጠናቀቅ ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን ተናግረዋል።

ግድያ መፈጸሙን ሳይሸሽጉ የተናገሩት ሃላፊው ዜናው የሚራገብበትን መንገድና፣ ይባስ ችግር ለመፍጠር በፈጠራ ምስልና መረጃ የሚታጀበበትን ሁኔታ ግን አጥብቀው ኮንነዋል። 

በግጭቱ ዙሪያ ሕዝቡን ከእውነታው የሚያርቅ ሀሰተኛ ዘገባ የሚያሠራጩ፣ የሚሠሩ ሰዎችና ተቋማት አሉ።  ከድርጊታቸው ሊታረሙ ይገባል፡፡ እነዚህ አካላት የአማራ መደራጀትና መጠንከር የማይዋጥላቸው ናቸው›› በማለት አቶ አሰማኸኝ ተናግረዋል። በስም የማይታወቁና በፈጠራ ስም የሚነቀሳቀሱ የማህበራዊ ሚዲያ አክተሮችን ዜናውን ” ነጩን ጥቁር” በሚል እያቀረቡ መሆኑንን የክልሉ ሚዲያ በድምጽ ያስተላለፈው ዘገባ ያስረዳል። 

amhara displaced.jpg

በስምም ሆነ በአካል የሚታወቁ ግለሰቦችና ተቋማት እንዳሉ አቶ አሰማኸኝ ገልጸዋል። ይሁን እንጂ የተቋማትን ስም አልዘረዘሩም። እሳቸው ይፋ ባያደርጉትም የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ በቅማንት ጉዳይ ላይ የእርቅ ስምምነቱን በሚካሄድበት ወቅት በተደጋጋሚ ” የቅማንት ወኪል ነን” የሚሉትን ወገኖች ልዩ የፕሮግራም ሽፋን ይሰጣቸው እንደነበር ይታወሳል። ይህ ሲደረግ ግን ከቅማንት ማግኘት የተፈለገው የፖለቲካ ትርፍም ሆነ ሌላ ጥቅም ግልጽ አልነበረም። 

በጉምዝ ነጹሃን ላይ ተፈጸመ የተባለው ግድያ ዩጋንዳ የተፈጸመን እልቂት ምስል በማስደገፍ በተለያዩ ታዋቂ የሚዲያ ተቋሞችና ግለሰቦች፣ እንዲሁም ይህንኑ በማራባት ላለፉት ሁለትና ሶስት ቀናት ስሜት የሚነኩ መረጃዎች ተሰራጭተዋል። አቶ አሰማኸኝ በግልጽ ባይናገሩም የፈጠራ መረጃ እንደሚረጭ ያስታወቁት ይኽንን ለማሳየት እንደሆነ ይገመታል። 

ማንም ምንም አለ ግድያው መፈጸሙ የማይካድና በምርመራ ላይ ያለ ጉዳይ እንደመሆኑ ዘገባዎች ፍጹም ሃላፊነት በተሞላው መልኩ ሊተላለፍ እንደሚገባ ስምምነት አለ። ክልሉ እንኳን ሊሸፋፍነው ቢሞክር ሃቁን ፈልጎ መዘገብ እንጂ ተጨማሪ ደም ሊያፋሥሥ በሚችል ጉዳይ ላይ በጎረቤት አገር የተፈጸመ ጭፍጨፋን ለራስ የፖለቲካ ጥቅማና ፍጆታ መጠቀም ኢሰብአዊነት ከመሆኑም በላይ ከመጠየቅም ማምለጥ አይቻልም።

” ህዝብ እንደ ጎርፍ የሚነዳበት ምክንያት አይገባኝም። ከለውጡ ማግስት ጀመሮ በክላችን ስራ የለም። ሞት፣ እሳት፣ ነውጥ፣ የሴራ ፖለቲካ፣ መከፋፈል፣ አለመግባባት፣ መጠራጠር፣ መፈናቀል… ባቻ ነው የሚታየው። ውሎ እያደረ እየሰመጥን ነው። ለምን ማስተዋል እንደተሳነን አይገባኝም። የአማራ ክልል ህዝብ በተለይም ወጣቱ ቢያስብ ይሻለዋል። ቢሰክን ይሻለዋል። የሚሰፈርለት አጀንዳና የሚጠመድለት ፈንጂ ላይ እየጋለበ አገር አልባ እንዳይሆን እሰጋለሁ” ሲል ሳሳሁልህ ጥላዬ የተሰኙ የገጻችን ደንበኛ አስተያየት ለግሰዋል።

የክልሉ ሚዲያ የሚከተለውን ዘግቧል።

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 25/2011ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ ዛሬ ለሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የመገናኛ ብዙኃን በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞንና በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወረዳ ከሚያዝያ 17 ቀን ጀምሮ የነበረው የፀጥታ መደፍረስና በአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በግለሰቦች የተነሳ ግጭ አድጎ ሰብዓዊ ቀውስ ማስከተሉንና የሁለቱ ክልሎች መንግሥታት በጋራ በመሥራታቸው አንጻራዊ ሠላም መስፈኑን ተናግረዋል፡፡

የግጭቱን ዝርዝር ሁኔታ ለማጣራት የሁለቱ ክልል መንግሥታት በጋራ እየሠሩ እንደሆኑና ጭካኔ በተሞላበት ድርጊት በሁለቱም ወገን የሰው ሕይወት መጥፋቱን፣ አካል መጉደሉን፣ ንብረት መውደሙን አስታውቀዋል፤ ድርጊቱ በክልሉ መንግሥት በጥብቅ የሚወገዝ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳድር ጃዊ ወረዳ ሚያዝያ 21 ቀን 2011ዓ.ም ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች የሰው ሕይወት ማጥፋታቸውን የገለጹት አቶ አሰማኸን ‹‹የክልሉ መንግሥት ጉዳዩን እያጣራ ነው፤ ጥፋትን በጥፋት የመመለስ አጀንዳ ሊታረም ይገባል›› ብለዋል፡፡

የአማራና ቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥታት በጋራ እየሠሩ መሆኑን ተከትሎ በአካባቢዎቹ አሁን ላይ አንጻራዊ መረጋጋት መፈጠሩንም ነው ለመገናኛ ብዙኃን ያስረዱት፡፡
ከኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከፌዴራል ፖሊስ እና ከኅብረተሰቡ ጋር የሁለቱ ክልሎች የፖለቲካ አመራሮች ቦታው ድረስ በመገኘት የማጣራትና የማረጋጋት ሥራዎችን እያከናወኑ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

በግጭቱ ዙሪያ ሕዝቡን ከእውነታው የሚያርቅ ሀሰተኛ ዘገባ የሚያሠራጩ የሚሠሩ ሰዎችና ተቋማት እንዳሉ ያመለከቱት ዳይሬክተሩ ‹‹ከድርጊታቸው ሊታረሙ ይገባል፡፡ እነዚህ አካላት የአማራ መደራጀትና መጠንከር የማይዋጥላቸው ናቸው›› ብለዋል፡፡

ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን በተመለከተም በአስተባባሪነት፣ በተባባሪነት፣በተሳተፊነትና አሳታፊነት በድርጊቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እጃቸው እንዳለበት የሚጠረጠሩ አካላትን በሕግ ቁጥጥር ሥር የማዋል ሥራ በጋራ እየተሠራ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ ተሳታፊ የሆኑ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
‹‹የአጣሪ ቡድኑ የሟቾችንና ተጎጂዎችን እንዲሁም ሌሎች የጉዳት መጠኖችን አጣርቶ እንደደረሰ ለሕዝብ እናሳውቀለን›› ያሉት አቶ አሰማኸን በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የሚገለጹ ቁጥሮች የተሳሳቱ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የአማራ ክልልን በተመለከተም ከደኅንነት አንጻር ስጋቶች እንዳሉ በሕዝብ እንደሚነሳ ተጠይቀው ‹‹አሁንላይ በክልሉ አንጻራዊ የሰላምና ደኅንነት መሻሻል አለ፡፡ ክልሉን በተለያዩ አጀንዳዎች ወጥሮ ስትራቴጂክ የሆኑ ሥራዎችን እንዳንሠራ የሚሠሩ ኃይሎች ግን ከድርጊታቸው ሊታረሙ ይገባል›› ብለዋል፡፡ በጎንደር፣ ከሚሴ፣ አጣዬና ማጀቴ አካባቢ አጋጥመው የነበሩ ችግሮች ከሕዝብ ጋር ሆኖ በተሠራው ሥራ ወደ ሠላምና መረጋጋት እየተመለሡ መሆናቸውንም አብራርተዋል፡፡

ትናንት በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎችን በተመለከተም ከጋዜጠኞች ተጠይቀው ምላሽ ሰትተዋል፡፡ ‹‹ሠላማዊ ሰልፎቹ በሰላም ተጠናቅቀዋል፤ ሕዝቡም ስሜቱን የገለጸባቸው ነበሩ፡፡ የክልሉ መንግሥትም በሰልፉ የተላለፉ መልዕክቶችን ይዞ ከሕዝቡ ጋር በመሆን በጋራ ይሠራል›› ነው ያሉት፡፡

ዘጋቢ፡- ጋሻው ፋንታሁን -ከአዲስ አበባ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *