)

የማህበራዊ ትስስር ገጹ በመተግበሪያው ሽብርተኝነትና ፅንፈኝነትን የሚያበረታቱ ይዘቶችን በሚያሰራጩ ገጾች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ኩባንያው ካለፈው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ ሽብርተኝነትን የሚያበረታቱና ተያያዥ ይዘቶችን የሚያሰራጩ ገጾችን ከመተግበሪያው ማገዱን ገልጿል።

ኩባንያው ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፥ እገዳውን ተከትሎ በመተግበሪያው ፅንፈኝነትን የሚያበረታቱ ይዘቶች ስርጭት መቀነሱን አስታውቋል።

ችግሩን ዘላቂነት ባለው መልኩ ለመፍታትም ከፌስቡክና ከጎግል ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አንስቷል።

Related stories   የመረጃ መንታፊዎች ዋትሳፕን እንደ ጥቃት ማድረሻ መሳሪያ እየተጠቀሙ መሆኑ ተገለጸ

ከዚህ ባለፈም በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ የመንግስት አካላት ጋር በማህበራዊ ትስስር ገጾች ፅንፈኝነትን የሚያበረታቱ ተጠቃሚዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው እየተሰራ ነው ተብሏል።

ከዚህ ጎን ለጎንም በመተግበሪያው መሰል ይዘቶችን የሚያሰራጩ ገጾችን ቅድሚያ ለመለየት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ይበልጥ ማሳደግ ይገባልም ነው የተባለው።

FBC – Meku Haile ምንጭ ፦ሲ ጂ ቲ ኤን

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *