“Our true nationality is mankind.”H.G.

በኤርትራ የ’በቃ’ ዘመቻ – የህወሃት ውጥንና የአማራ ክልል መተራመስና የፖለቲካ አኩኩሉ!!

ፎቶ – ፕሬዚዳንት ኢሳያስ እና ዶ/ር ደብረጽዮን ኦምሃጀር ድንበር ሲከፈት የተነሱት ከጠቅላይ ሚኒስትር ገጽ የተወሰደ

“የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ አክቲቪስት የሚባሉት፣ የለውጡ ደጋፊዎች በጥቅሉ አካሄድና ስትራቴጂ አያውቁም። የይደር ፖለቲካን አልተረዱም። በደመ ነፍስ ሲበሩ ለሌላ አገር የሚሰሩ ነው የሚመስሉት። ሆን ተብሎ የተነደፈው የጎሳ አመለካከት ወይም የተሸጡ ሰዎች ሁሉንም ጉዳይ አፈር አስግጠውታል። አሁን ተጠያቂዎች መሪዎች አይደሉም። ሕዝቡ ራሱ ነው። ለውጡ እንደተጀመረ በነበረው መንፈስ ህዝብ ተባብሮ ቢቀጥል ኖሮ ሁሉም ጉዳይ በተጠናቀቀ ነበር። የትግራይ ህዝብ ህወሃትን ቢጠላም ስትራቴጂካል አካሄዱ ስለገባው መሪዎቹን ከነሽታቸው አቅፎ ቁጭ ብሏል። አክቲቪስቶቻቸውም በተመሳሳይ ይህንኑ እያደረጉ ነው። ነገሩን ጠለቅ ብሎ መመርመር የሚችልና የሚረዳ እየሆነ ባለውና በተበላሸው ጉዳይ እድሜ ልኩን ያዝናል። አሁንም ግን ጊዜ አለ …” 

በቅርቡ ፕሮፌሰር አስመሮም ” የኤርትራ ሕዝብ በውያኔም ሆነ ቀደም ሲል የተሰራበትን በደል አይረሳም። ይህንን ረሳን ማለት በፍጹም የማይታሰብ ነው” ማለታቸውን ሰሞኑን የትግራይ ተወልጅ የሆኑ አክቲቪስቶችን በእጅጉ አስቆጥቶ ሰንብቷል። ፕሮፊሰሩ ይህንን ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን በተደጋጋሚ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ ላይ በጥልቀት እየተሰራና ውጤት እየተመዘገበ መሆኑንን ለሚመሩት ህዝብ መናገራቸውን ተከትሎ መሆኑ ፕሮፓጋንዳውን ወሃ ከልሶበታል። ከዚህ አንጻር ይመስላል በትግራይ የትግራይ ተወላጅ አክቲቪስቶች ተቃውሞ ጮክ ብሎ የተሰማው።

ዛሬ በየትኛውም ዓይነት ዋጋ ትግራይና ኤርትራን ማስተሳሰር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ሆኗል። ከመሃል አገር ጋር ያላቸው ግንኙነት የተበጠሰባቸው የህወሃት አንጋፋ መሪዎችና ባልደረቦቻቸው ወደ መቀሌ ካፈገፈጉ በሁዋላ ህዝቡን በፍርሃት አሸብበው ጥፋታቸውን እንዳይቆጥር አድርገዋል። ሕዝቡ ሰፊ የሚባል ተቃውሞ ቢኖርበትም ሌሎች እንደተነሱበት ተደርጎ የተራገበው በመራገብ ላይ ያለው ፕሮፓጋንዳና ከማዕከል የተስተዋሉ መጠነኛ ጥፋቶች ተዳምረው አሁን በትግራይ ህወሃት ጻድቅ ሆኖ የአማራጭ መንገድ እያፈላለገ ነው። እሱም ኤርትራን ከማንም በላይ መወዳጀት።

በአውሮፓ በስደት ከሃያ ዓመት በላይ እንደኖረ የሚናገረው ዮናስ እንደሚለው በኤርትራና በትግራይ መካከል ቀደም ሲል ሊረሳ የማይችል ክህደት ተፈጽሟል። ይህንን ክህደት ሁሉም የኤርትራ ተወላጆች ያውቁታል። የወያኔ አገዛዝ ይህንን የክህደት ታሪክ በመልካም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማስተካከል ቢፈልግ ኖሮ ጊዜው ዛሬ እንዳልሆነ ያክላል። እንኳን የቀደመውን ታሪክ ሊያድሱ ከኢሳያስ ጋር የነበራቸው አለመግባባት ተከትሎ በፖሊሲ ደረጃ ኤርትራዊያንን ዘርፈውና አፈናቅለው ባዶ በማስቀረት፣ በውክልና ዘመድ ኤርትራዊያን ለፍተው ያገኙትን ንብረት ዘርፈው ባዶ አስቀርተዋቸዋል። ይህንን ታሪክ ዛሬ ማጣፊያው ሲያጥር ለመቀየር መሞከር የዋህነት እንደሆነ ይናገራል። በዚሁ ሳቢያ በንዴት የታመሙ፣ የሞቱ፣ ቤተሰባቸው የተበተነ … ቤቱ ይቁጠረው ይላል።

እጅግ ግዙፍ ጋራዥ ባለቤት የነበሩ አባትዋ መርፌ ሳይዙ ተዋክበው ከነልጆቻቸው ከአገር እንዲባብረሩ መደረጉን የምታስታወሰው ሌላዋ የአምስተርዳም ነዋሪ ሰናይት ” ስለ እነሱ መስማትም ሆነ ማውራት አልፈልግም” ስትል እየተንገሸገሸች ብትናገርም አልፋ ማብራሪያ መስጠት አትወድም።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

ያለፈውን መርሳት አስፈላጊ እንደሆነ የሚናገሩና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ ከትግራይ ጋር መቀጠል እንዳለበት የሚናገሩም አሉ። ሰለሞን አንዱ ነው። እሱ እንደሚለው ብዙ ጥፋት ተሰርቷል እሱን እየቆጠሩ የወደፊቱ ትውልድ ላይ መፍረድ አግባብ አይደለም።

ከሁሉም ወገን የተለያዩ አመለካከቶች ቢኖሩም፣ ህወሃት በኤርትራ ለውጥ እንዲከሰት ቀደም ሲል በመንግስት ደረጃ፣ አሁን ደግሞ በራሱ በፓርቲ ደረጃ እየሰራ መሆኑን በርካታ ኤርትራዊያን ይናገራሉ። እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት ህወሃት በሚደጉማቸው አክቲቪስቶች አማካይነት በኤርትራ ውስጥ ያሉትን ሻዕቢያ የወለዳቸውን ችግሮች በማግዘፍ ህዝብ ወደ ተቃውሞ እንዲወጣ እየገፉት ነው። በተመሳሳይ በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል ሰላም እንዳይሰፍን እየተሰራ ለመሆኑ ጥርጥር የለም።

በቅርቡ አገሩን ጎብኝቶ የተመለሰ ወጣት እንደሚለው ጎንደር ውስጥ የሚካሄደውን ግጭትና የግጭቱን ባህሪ፣ እንዲሁም ግጭቱን የሚካሄድበት የመሳሪያ ቲክኖሎጂና የታጣቂዎቹ እንቅስቃሴ ከጀርባ ዳጎስ ያለ የብረትና የስልጠና እገዛ እንደሚደረግ ጥርጥር የለውም።

ይህንኑ የሚያጠናክረው ዮናስ ትኩል አሁን በጎንደርና አካባቢው የተነሳው ግጭት ለምን ህወሃት አገሪቱን በበላይነት በሚመራበት ወቅት  በዚህ መልኩ እንዳልተነሳ ይጠይቃል። መልሶም የአማራ ክልል መሪዎች በተደጋጋሚ ኤርትራ መሄዳቸው፣ ኢሳያስ አፉወርቂ ባህር ዳርቭ ተገኝተው መምከራቸው ህወሃትን እንቅልፍ ነስቷል። ስለሆነም ኢሳያስ አፉወርቂን የማስወገዱ የቆየ እቅድና ሙከራ እንዳለ ሆኖ፣ አማራ ክልል እንዳይረጋጋ ማድረግ ወቅቱ የሚጠይቀው አማራጭ ነው። እንዲሁም የማእከላዊ መንግስቱ በግጭትና በረብሻ ብዛት እንዲዳከም ማድረግና ከህዝብ መነጠል፣ ይህንኑ በሚዲያና በማህበራዊ ገጾች በማራገብ ኢላማን መምታት።

የሰላም ጉዞውና – የኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታ አመቺነት

ጠቅላይ ሚኒስት አብይ ኤርትራ፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ኢትዮጵያ ከመጡ በሁዋላ በሚያስገርም ፍጥነት የተቀጣጠለው የሰላም ጉዞ ከቆይታ በሁዋላ ኤርትራዊያንን ያልሳደሰተበት ምክንያቶች አሉ። ኢትዮጵያ እንደተደረገው ሁሉ እስረኞች አልተፈቱም። ሚዲያ ነጻ አልወጣም። ዜጎች የመቃወም ነጻነታቸውና የመሰለፍ መብታቸው በይፋ አልተከበረም። በውጭ ያሉ ትውልደ ኤርትራዊያን ወደ አገራቸው እንዲገቡ አልተደረገም። በጥቅሉ ለውጥ ቢጠበቅም ኢሳያስ በነብረው ባቡር መቀጠላቸው ደስታን አልፈጠረም። እንዲያውም ጉምጉምታ አለ። ወረቀት የመበተንና የ ” በቃ” ዘመቻ ስርሰሩን እየነደደ ነው። ዮናስ እንደሚለው በራሱ በኤርትራ መንግስት ድካምና ጥፋት ህወሃት እየተጠቀመበት ነው። ችግሮቹን በወኪሎቹ አማካይነት እያራገበ ለለውጥ ሰዎች እንዲነሱ እያስቀሰቀሰ ነው።

እየጋመ ያለው የጀነራሉ ጉዳይ

የኤርትራ የመከላከያ ሚኒስትር ጀኔራል ስብሀት ኤፍሬም ለኢሳያስ ቁልፍ፣ በመከላከያ ውስጥ ነባርና ልምድ ያላቸው ባለሙያ፣ በስልጣን ደረጃ ሁለተኛ የአገሪቱ ሰው መሆናቸው ይነገራል። የእኚህ መኮንን በጥይት መጎዳት መሰማቱን ተከትሎ በርካታ ዘገባዎች፣ መላምቶች፣ ጭፍን ትንታኔዎች እየቀረቡ ነው።

ጀነራሉ ላይ ደረሰ ስለተባለው የጥይት ጥቃት በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር ድርጊቱን አውግዘው፣ መልካም ጤንነት ከተመኙበት ቲውተር ሌላ ለመንግስት በገሃድ የተባለ ነገር የለም። ለህክምና ዱባይ ናቸው፣ ኢሳያስ ሊጠይቋቸው ዱባይ ሄዱ፣ ሞተዋል፣ ስማቸውን ቀይረው ኢትዮጵያ ግብተዋል። ኢትዮጵያ የገቡት በሰሜን በኩል የጦርነት ስትራቴጂ ለመንደፍ ነው… ብዙ ብዙ እየተባለ ቢሆንም፣ ኤርትራዊያን እውነቱን መስማት ግን ይፈልጋሉ።

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ

አፍቃሪ ህወሃት የሆኑ የኢሳያስ ታማኝ ሃይሎች መክዳታቸውንና መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ለማድረግ ጫፍ ደርሰው መክሸፉን፣ ይህንኑ መፈንቅለ መንግስት ጀነራሉ ይመሩት እንደነበር መጠቆሙን አስመልክቶ ዮናስ ” ጀነራል ስብሃት መፈንቅለ መንግስት ሞከረ ማለት ኢሳያስ አብቅቶለታል ማለት ነው። ምክንያቱም  ዋናው የኢሳያስ ቁልፍ ሰው ስብሃት ነው። እውነት ስብሃት እንኳን ከድቶ አዚህ ድርጊት ውስጥ ገብቶ እርምጃ ቢወሰድበት ጦሩ ውስጥ አደገኛ መሰንጠቅ ስለሚፈጥር  ነገሩ ዛሬ ድረስ አይቆይም ነበር” ሲል ይህንን ጉዳይ መታገስ አግባብ መሆኑንን ያናገራል።

ይሁን እንጂ ዮናስ ኢሳያስ አፉወርቂ በቅርቡ በሚከበረው የድል በዓል ላይ በርካታ ጉዳዮችን ይፋ የሚይደርጉ ይመስለኛል ይላል። ምክንያቱም ኤርትራዊያን መሰላቸታቸውንና ወደ ሌላ አማራጭ ሊሄዱ እንደሚገደዱ ምልክቶች አሉ። ምልክቶቹ ወደ ተቃውሞ ሊያመሩ ይችላሉ። ምንም እንኳን ህወሃት ሲሞክር እንደኖረው ውስጥ ውስጡን እነሱ በሚያደርጉት ሳይሆን ህዝቡ በራሱ ለለውጥ ሊጮህ ይችላል። ልክ ሱዳን ላይ እንደሆነው ወታደሩ ህዝቡን ከተቀላቀለ ሁሉም ነገር ያከትማልና።

ስትራቴጂን ያላገናዘቡ ወገኖች ያጨናገፉት ጉዞ

“የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ አክቲቪስት የሚባሉት፣ የለውጡ ደጋፊዎች በጥቅሉ አካሄድና ስትራቴጂ አያውቁም። የይደር ፖለቲካን አልተረዱም። በደመ ነፍስ ሲበሩ ለሌላ አገር የሚሰሩ ነው የሚመስሉት። ሆን ተብሎ የተነደፈው የጎሳ አመለካከት ወይም የተሸጡ ሰዎች ሁሉንም ጉዳይ አፈር አስግጠውታል። አሁን ተጠያቂዎች መሪዎች አይደሉም። ሕዝቡ ራሱ ነው። ለውጡ እንደተጀመረ በነበረው መንፈስ ህዝብ ተባብሮ ቢቀጥል ኖሮ ሁሉም ጉዳይ በተጠናቀቀ ነበር። የትግራይ ህዝብ ህወሃትን ቢጠላም ስትራቴጂካል አካሄዱ ስለገባው መሪዎቹን ከነሽታቸው አቅፎ ቁጭ ብሏል። አክቲቪስቶቻቸውም በተመሳሳይ ይህንኑ እያደረጉ ነው። ነገሩን ጠለቅ ብሎ መመርመር የሚችልና የሚረዳ እየሆነ ባለውና በተበላሸው ጉዳይ እድሜ ልኩን ያዝናል። ” 

ዮናስ ይህንን የሚለው በቁጣ መንፈስ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በተመረጡ ማግስት ኤርትራ ገብተው ያንን ሁሉ ተዓምር ሲሰሩ ለምንና እንዴት ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ ህዝብ በስካር ፖለቲካ ውስጥ ገብቶ አበደ። ሳይገባው አጨብጭቦ ሳይገባው ማውገዝ ጀመረ። በስሜት ደግፎ በስሜት ማውገዝ ጀምረ። ከሁሉም በላይ ግን በኤርትራ በኩል ሊሰራ የነበረውን የረቀቀ ፖለቲካ አጨናገፈ። ይህ አይነቱ መደናበር ብዙ ውጋ ያስከፍላል። የፖለቲካ መካንነት ያስከትላል። የኢትዮጵያ ህዝብ ለአንድ ዓመት መታገስ አቅቶት በሰማው ሁሉ እየተሳበ ወርቁን እድልና ስትራቴጂ አወየበው።

የህወሃት አማራጭ

“ህወሃት አማራ ክልል ሰላም ከሆነና ከተረጋጋ ምን እንደሚከተል ያውቃል። የፌደራል መንግስቱ በደንብ ከጸና ምን ጥያቄዎች እንደሚነሱ ይረዳል። ስለሆነም የኢርትራና የትግራይ ጉዳይ እልባት ሳያገኝ ማዕከላዊ መንግስት ሰላም አያገኝም” ይላል ዮናስ ” ይህንን እንደ ስትራቴጂ እኔም ብሆን አደርገዋለሁ” ሲል ያክላል። ጭንቀቱ ለትግራይ ህዝብ ሳይሆን ለራሳቸው ለህወሃት ጌቶች ነው። የሶማሌ ክልል አብዲ የሚባለው ‘ከብትና’ አበሮቹ ተለቅመው ሙስጣፋ የሚባል ሥትራቴጂስት ሰው መጣላቸው። አሁን ችግር የለባቸውን እየኖሩ ነው። አገሪቱ የምትፈርሰው በዚያ በኩል ነው ቢባልም ዛሬ የሆነው ሌላ ነው። በዚህ መለኪያ የህወሃት መሪዎች ቢወገዱ የትግራይ ህዝብ የተሻለ ዘመናዊ መሪዎች ያገኛል እንጂ የሚሆነው ነገር የለም። ራሳቸውንና ስራቸውን ሰለሚያውቁ ግን አማራጫቸው ከኢሳያስ ጋር ለመታረቅ ማንኛውንም አይነት ድንጋይ መፈንቀል፣ ኢሳያስን ለማስወገድ የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ አለያም ቀታዩ መሪና የኤርትራ ህዝብ ምን እንደሚል ባይታወቅም ኢሳያስ እንዲሞቱ መጸለይ!!

Related stories   “ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአንድነት በመከባበር፤ በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ሊያከብር ይገባል”

የህወሃት አመራሮች በትግራይ ህዝብ ስም በርካታ ወነጀሎችን ፈጽመዋል። ይህ የፈጸሙት ወንጀል እንደሚያስጠይቅ ሰለሚያውቁ ነው ንብረታቸውን ጥለው ወደ መቀሌ የሸሹት። እናም በየትኛውም መስፈርት የዶክተር አብይ አመራር እንዲረጋጋ አይፈቅዱም። ያላቸውን ንዋይ ያፈሳሉል። የነበራቸውን ኔት ዎርክ በመጠቀም አሁን እየሆነ ያለውን ዓይነት ተግባር ይፈጽማሉ። ይህ ህልውና ነውና ተባባሪ እስከተገኘና ሃብት እስካለቀ ድረስ የሚቀጥል እንደሚመስለው ዮናስ ይናገራል።

የሰላም ስምምነቱ መጠለፍ 

በአማራ ክልል ስለም መደፍረሱ፣ በመሃል አገር ያለው ሁኔታ ፕሬዚዳንት ኢሳያስን እረፍት እንደሚከለክላቸው ዮናስ ያምናል። የድንበር መከፈቱን ተከትሎ በርካታ ዜጎች ወደ ኤርትራ መመለስ ሲገባቸው ከሃያ ሺህ በላይ ኤርትራዊያን አገራቸውን ለቀው ወጥተዋል። ሁሉንም ጉዳይ በአግባቡ መቆጣጠር እንዳይቻል የፌደራል መንግስቱ ከትግራይ ክልል ጋር ያለው ግንኙነት ህግ የጠበቀ አይደለም። ስለሆነም ቴክኒካል ጉዳዮችን ሰበብ በማድረግ ስምምነቱን ያዝ መድረግ እንደ አንድ ስትራቴጂ የተያዘ እንደሚመስለው ይናገራል። ምን አልባት ፍልሰቱን ለመግታት የሚያስችልም እቅድና አሰራር ሊተገበር ታስቦ ሊሆን እንደሚችል ይገምታል።

ኢሳያስ አፉወርቂ ጥበቃውን አክርረው። ድንበሩን ጠርቅመው ዘግተው፣ አንደበታቸውን ዘግተው በውስጥ ስራ ላይ ናቸው። አብይ አህመድ ደግሞ አገር ውስጥ በሴራ ፖለቲካ ተወጥረዋል። እዛም እዚያም መልክ እየለዋወጡ የሚነሱ ችግሮችን ለመድፈን ሌት ተቀን እየባተቱ ባልበት ሁኔታ ውስጥ ህዝብ አልተረዳቸውም። አንዳንዴም በሚያስገርም ሁኔታ ይወቀሳሉ። የማይወዷቸውን የተገፉ ሃይላት ዓላማና ፍላጎት በማራመድ ላይ ያሉ ወገኖች እየበረከቱ ነው። አንዳንድ ሚዲያዎች ዘመቻና ቅስቀሳቸውን እሳቸው ላይ አነጣጥረው ቀጥለዋል። ነገሩን ለሚመለከት ግራ የሚያጋባ ነው። እንዲህ ባለ የተሳከረ ጉዳይ ውስጥ ኢሳያስ ገብተው እሳት መጨበጥ የሚፈልጉ እንደማይመስለው ዮናስ ያስረዳል። በዚህ መመዘኛ ለውጡ የተሰነካከለና ጊዜ የሚጠብቅ እንደሚመስለው ዮናስ ያክላል። የአማራ ክልል ቢረጋጋ ግን ተአምራዊ ለውጥ እንደሚታይ ቅንጣት እንደማይጠራጠር ዮናስ አስታውቋል። ይህን ማወቅ ፖለቲካ መማር እንደምይጠይቅ ያወሳው ዮናስ፣ “አሁን ጨውታው ተራ የፖለቲካ አኩኩሉ ነው። ሰዎች አገራቸውን ለማተራመስ በሌሎች ሲቀጠሩ ከማየት በላይ አሳዛኝ ነገር የለም። የኢትዮጵያ ህዝብ ሊነቃ ይገባል”

 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0