“Our true nationality is mankind.”H.G.

“ኢትዮጵያ የፈተና ዘመን ላይ ናት፤ አረሙም በአንድ ጊዜ አይጠራም ”  ዶክተር ወርቁ ነጋሽ

ዶክተር ወርቁ ነጋሽ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም መምህር እና አማካሪ ናቸው። በአሜሪካን ሀገር በነበራቸዉ ቆይታ በተለያዩ ከፍተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ስድስት ያክል ዲግሪዎችን አግኝተዋል። ስመጥር በሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች አስተምረዋል፤ ብዙ የሥራ ልምድም አላቸዉ። እናም በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ቆይታ አድርገናል፡፡ 

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥርዓት እና የሕዝብ እንቅስቃሴ ወቅታዊ ሁኔታዉን ዶክተር ወርቁ ነጋሽ ሲገልጹት ፖለቲካዉ የሕዝቡን ትኩረት እንደሳበ እና አብዛኛዉ ሰዉ ጊዜዉን የሚያጠፋበት ጉዳይ ሆኗል፡፡ ዘመኑ ‹‹የእኛ›› ሳይሆን ‹‹እኔ›› በሚል የዘረኝነት አመለካከት እንደተዋጀ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ጭንቀቱ ከቀን ቀን ከፍ እያለ እንደሄደ የገለፁት ዶክተር ወርቁ ሕዝቡ እፎይ ብሎ የሚተኛበት ዘመን ይናፍቀኛል ብለዋል። ችግሩን ያመጣው ብዙ ያልታሰበ የመንግሥት ፖሊሲ እንደሆነም ይገልጻሉ ምሁሩ። በኢትዮጵያ ሲካሄድ የቆየው የፖለቲካ ሥርዓት የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን ማንነት ጭምር ያፈነ ነበርም ብለዋል።
“ፖለቲከኞች ኃላፊ
ነታቸውን አልተረዱትም፤ ፖለቲካ ምን እንደሆነም አላወቁም፤ የፖለቲካ ሥራ የሚሠራ ሰው መነሻውም መድረሻውም ሕዝብን ማገልገል ነው” ብለዋል፡፡ አንድ ሰው ወደ ፖለቲካ ሲገባ ሕዝብን ሊያገለግል ሲያስብ መሆን እንዳለበት የሚገልጹት ምሁሩ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ግን “ሕዝብን እያገለገላችሁ ነው?” ተብለው ቢጠየቁ መልስ የላቸውም ብለዋል። እንደ ምሁሩ ማብራሪያ አሁን ያሉት ፖለቲከኞች በተፈጥሯቸው ክፉዎች ሆነው ሳይሆን ቀደም ሲል የተቃኙበት ቅኝት ግራ ቅኝት ስለሆነ ነው።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

ከዚህ ቀደም ፖለቲካው በቀኝ ተቃኝቶ ቢሆን ኖሮ ሕዝብን የሚጠቅም ይሆን ነበር። የግራው ቅኝት የዳበረው ሕዝቡ ያልተማረ በመሆኑ እና መብቱን ማጣጣም ስላልቻለ ነው። በኢትዮጵያ የነበረው አሁንም ያልፀዳው የፖለቲካ ሥርዓት በምዕራቡ ዓለም ቢሆን ኖሮ መንግሥት ከዙፋኑ አንድም ቀን ማደር አይቻለውም ነበር። መንግሥት በሕዝብ ካልተገታ ወደ ራሱ ፍላጎት መሄዱ አይቀሬ ነው፡፡ ሕዝቡ ሲበስል እና ሲማር የምንፈልገው ለውጥ እና የምናስባት ኢትዮጵያ ትመጣለች።
ወደ ኋላ መለስ ብለዉ ከኃይለሥላሴ እና ከደርግ ሥርዓት ጋር ያነጻጽራሉ፤ እናም ‹‹የአሁኑ የከፋ ዘመን እንደሆነ ይሰማኛል›› ባይ ናቸዉ። ምክንያታቸዉን ሲገልጹ ኢትዮጵያ የምትታወቀው የእኛ በሚል እንጂ የእኔ በሚል ትርክት አይደለም። አሁን የእኛ ጠፍቶ የእኔ ስለነገሠ ዘመኑን የከፋ እንዲሆን አድርጎታል። የእኛ የሚለው የኢትዮጵያ ታላቅ መገለጫ እና ታሪካችን እየጠፋ ነው፡፡ ያን መመለስ መቻል እንዳለብን ይገልጻሉ፡፡

Related stories   የኢትዮዽያ የቁርጥ ቀን ልጅ "ስለአባይ እውነቱን እንካችሁ" – መካ አደም አሊ

‹‹ቀደም ባለው ጊዜ ለሥራም ሆነ ለትምህርት ወደ ውጭ የሚሄዱ ኢትዮጵያውን ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበት ጊዜ እየረዘመባቸው በስስት ይጠብቁ ነበር፤ የአሁኑ ትውልድ ግን ወደ ውጭ ለመውጣት ያለውን አማራጭ የሚጠቀም ኢትዮጵያን ያልናፈቀ ነው›› ብለዋል። በቋንቋ፣ በሃይማኖት እና በብሔር መከፋፈል እና መቃኘት ለኢትዮጵያ ስጋት እንደሚሆንም ተናግረዋል። ይሁን እንጅ አደገኝነቱን አውቆ ወጣቱ ታግሎ ለውጥ አምጥቷል። አሁንም ግን የለውጡ ባለቤት ለሀገር አንድነት መሥራት እንዳለበት ዶክተሩ መክረዋል። “ጎርፍ ከጠብታ ይጀምራል” ያሉት ዶክተር ወርቁ “እኔ ጥቂት ጠብታዎች ለሀገሬ ልሰጥ ነው ወደሀገሬ የመጣሁት፤ ሌላውም የአቅሙን ጠብ በማድረግ ኢትዮጵያን ወደ ልዕልና መውሰድ መቻል አለበት” ብለዋል። የተሰጠ ሳይሆን የሰጠ እንደሚደሰት የገለጹጽ ዶክተር ወርቁ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያለውን መልካም ነገር መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል። አሁን ያለው መሪ በእኔ እምነት ጥሩ ነው። ነገር ግን ከታች ያሉት እያገዙት እና የሚገባውን ነገር አልሰጡትም ብለዋል። ወጣቶች ‹‹የእኔ ነው›› የሚለውን ትተው ‹‹የእኛ ነው›› በሚለው ታላቅ ታሪክ መጠመድ እንዳለባቸዉ እና ኢትዮጵያ የእኛ ናት ብቻ ሳይሆን አፍሪካ፣ ዓለምም የኛ ነዉ ወደሚል አስተሳስብ ማደግ እንዳለበት ይመክራሉ።

Related stories   እስራኤል አልጃዚራ ቴሊቪዥን፣ አሶሲየትድ ፕሬስና ሌሎች ሚዲያዎች የሚጠቀሙበትን ህንጻ አወደመች

በአለፉት ሦስት ዓመታት ወጣቱ ያደረገው ትግል ዓድዋ ላይ እንደተፈፀመው ገድል ነው ሲሉ የሚያወድሱት ዶክተር ወርቁ ለዓመታት የተበላው መርዝ ሲያም ቆይቶ እየለቀቀ ያለበት ዘመን እንደሆነም ይገልጻሉ። ‹‹ኢትዮጵያ የፈተና ዘመን ላይ ናት፤ መጥፎ ዘር በቅሎ እየታረመ ነው። አረሙም በአንድ ጊዜ አይጠራም›› ነው ያሉት። ሕዝቡ ማስተዋል እንደጀመረ የተናገሩት ምሁሩ መንግሥት አያያዙን ማሳመር እንደሚገባው መክረዋል።

‹‹ኢትዮጵያ የተጋረጠባትን ፈተና የምትሻገርበት ዘመን ላይ ናት፣መፃኢ ዕድሏ ብሩህ ነው›› ሲሉም ተስፋቸውን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ መፃኢ እድል ሲስተካከል የአፍሪካ ዕድልም አብሮ ይስተካከላል። ምክንያቱም ኢትዮጵያ ለአፍሪካውያን መሠረት እና ተስፋ ስለሆነች ነው። ወጣቱ ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ የአፍሪካን ተስፋ የማለምለም አደራ እንዳለበትም ዶክተር ወርቁ አሳስበዋል።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 05/2011ዓ.ም (አብመድ)

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0