ባህር ዳር ነዋሪዎች በስጋት ከሚኖሩባቸው ከተሞች አንዷ ናት። በዚህ መነሻ ከህዝብ በተገኘ ጥጥቆማ መነሻ የከተማው ፖሊስ፣ የክክሉ ፖሊስ ኮሚሽንና አስተዳደር በመተባበር በድንገት ፍተሻ አካሂደው ነበር። በተደረገው ያልታሰበ ፍተሻ የጦር መሳሪያና ከሰማንያ በላይ  ህገወጥ ተሽከርካሪዎች ተይዘዋል።

በፍተሻው ወቅት ሽጉጥ፣ ክላሽ፣ ጩቤዎች፣ ፌሮ ብረት የመሳሰሉ መሳሪያዎች መያዙን ፖሊስ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ተሽከርካሪዎች ህገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውር፣ ዝርፊያ፣ ነፍስ ግድያና የማስገደድ አስነዋሪ ተግባራት ሲከናወንባቸው እንደነበር ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

ቁጥጥሩና ስምሪቱ የላላና የተዳከመ መሆኑና ይህንን ተከትሎ የድንብ መተላለፍ ሊበራከት እንደቻለ ያስታወቀው ፖሊስ ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክቷል። ህዝብም በየዕለቱ ክትትሉን በማድረግ ጥቆማውን እንዲገፋበት ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል። ህዝብና የጸጥታ አካሉ እጅና ጓንት ሆነው ከሰሩ ህገወጦችን በመመንጠር የባህር ዳርን ሰላም ማስጠበቅ እንደማይከብድ ፖሊስ አክሎ ገልጿል።

የባህር ዳር ህዝብ ከርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው ጋር ዛሬ ባደረገው ውይይት ” አደራጁን ከተማችንን እንጠብቃለን ኮሽ የሚል ነገር አይሰማም” ማለቱና በማህበራዊ ሚዲያ የሃሰት ወሬ መሰላቸቱን  ተናግሯል።

 

Related stories   ሕወሃት በምዕራብ ኦሮሚያ ጥቃት መጀመሩ ተሰማ !! የክልሉ መንግስት ውሳኔ ይጠበቃል !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *