በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተፈጠረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ። የአማራ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገበው በቁጥጥር ስር የዋሉት የመተከል ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ፋንቻ አምሳያ እና የግልገል በለስ ከተማ ከንቲባ አቶ ጊሳ ዚፋህ ናቸው። ለጊዜው የተሰወሩ እንዳሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎቹ በሕግ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ከሰሞኑ በአካባቢው በነበረው የፀጥታ ችግር ተጠርጥረው መሆኑን የዓይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ በቦታው የሚገኘው ዘጋቢ ወንዳጥር መኮንን መዘገቡን ነው ሚዲያው ያስታወቀው።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው የክልሉ መንግስት ሙሉ ድጋፍ የጠየቀውና በክልሉ ጸጥታ እንዲያስከበር በአካባቢው የተሰማራው  የኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ናቸው።

የአካባቢው ነዋሪዎችን በስልክ ያነጋገረ ተወላጅ ለዛጎል እንዳለው ለጊዜው የተሸሸጉ ተፈላጊዎች አሉ።

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ካቢኔ በተደጋጋሚ ስብሰባ በማካሄድ በክልሉ ከቀን ወደ ቀን እየተስፋፋ የሄደውን ግጭትና መፈናቀል፣ እንዲሁም ግድያ አስመልክቶ ከወትሮው የተለየ አቋም እንደሚይዝ ሲያስታውቅ መቆይርቱ አይዘነጋም። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በትናትናው እለት አራት መሰራተዊ የተባሉ ውሳኔዎችን አሳልፎ ነበር።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ውሳኔ 1. 
ግጭት በተከሰተባቸውም ሆነ በየትኛውም የክልሉ አካባቢ ድምፅ አልባ መሣሪያዎችን ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

ውሳ 2.
በልዩ ሁኔታ ከተፈቀደላቸው አካላት ውጭ የክልሉ ሚሊሻ አባላትም ሆኑ የቀበሌ ታጣቂዎች ሕጋዊም ይሁን ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

ውሳኔ 3.
በተደራጀ መንገድም ሆነ በተናጠል ወደ አማራ ክልል አዋሳኞች ጥቃት ለመፈፀም የሚደረጉ ማናቸውም ዓይነት እንቅስቃሴዎች ፍፁም ሕገ-ወጥ፣ በየትኛውም አካል ተቀባይነት የሌለው እና የተወገዘ ከመሆኑም ባለፈ በልዩ ሁኔታ በሕግ የሚያስጠይቅ ተግባር ነው፡፡

ውሳኔ 4
ከመከላከያ ሠራዊትና ከፌዴራል ፖሊስ ውጭ በአስተዳደር ወሰን አካባቢዎች የክልሉ ልዩ ኃይል እና መደበኛ ፖሊስ በ5 ኪሎ ሜትር ራዲዬስ ውስጥ መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፍፁም የተከለከለ ነው፡፡

የፀጥታ ምክር ቤቱ እነዚህን ውሳኔዎች ለጋራ ሠላምና ፀጥታ እጅግ በጣም ወሳኝና መሠራታዊ መሆናቸውን በጥልቀት በመገንዘብ የመተከል ዞንና ከፍ ሲል በተጠቀሱት አራት ወረዳዎች የተዋቀሩ ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቶች በጥብቅ እንዲከታተ

 

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *