ለዜጎች ሞት እና መፈናቀል መፍትሔ መሰጠት እንዳለበት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር መኮንን ተናገሩ።
የአማራ ክልል እና የቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ለሰላም ውይይት በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ተገናኝተዋል፡፡

የሰላም ውይይቱ ዓላማ በሁለቱ ክልሎች አጎራባች ወረዳዎች ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር በመፍታት የህግ የበላይነትን ማስከበር፣ የዜጎችን ደኅንነትም ማረጋገጥ ነው፡፡ የሁለቱንም ክልሎች ነዋሪዎች ጉዳት ላይ የጣለውን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች አጠናክሮ የማስቀጠል ዓላማም አለው ምክክሩ፡፡

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

የጉሙዝ እና የአማራ ሕዝቦችን ወንድማዊ ዝምድና ለማፍረስ የተፈፀመውን ወንጀል እንደሚያወግዙ የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን ለዜጎች ሞት እና መፈናቀል መፍትሔ መሰጠት እንዳለበት አሳሰበዋል።

የተፈናቀሉ ወገኖች ስላምና ደኅንነታቸው ተጠብቆ ወደ ቀያችው እንዲመልሱ በማድረግ የክልሉ መንግስት ከጎናቸው እንደሚሆንም ነው ዶክተር አምባቸው የተናገሩት።

የቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሐሰንም ለሞት፣ ለአካልና ሥነ ልቦና ጉዳት እንዲሁም ለመፈናቀል ምክንያት የሆነውን ድርጊት አውግዘዋል።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

ቂም በቀልን በመተው ከልብ በመነጨ ይቅርታ ወደ ቀድሞ ሰላምና አብሮነት መመለስ እንደሚገባም አቶ አሻድሊ ተናግረዋል።

ተሳታፊዎች ደግሞ በርካታ አማራና አገዎች በግጭቱ ህይወታቸው እንደጠፋና እንደተፈናቀሉ አንስተዋል፡፡

ይህን ያደረጉ አጥፊዎች ካልተያዙ ስላሙ ዘላቂ እንደማይሆንም አሳስበዋል፡፡

በሁለቱም ክልሎች በፀጥታ ችግሩ ተሳታፊ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ አመራሮችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራው ቀጥሏል፡፡

ዘጋቢ፦ ወንዳጥር መኮንን

Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

አብመድg

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *