የህወሃት ባለስልጣናት ተሰብስበው ትግራይ መግባታቸውን ተከትሎ ብዙ ይባላል። መንግስት በኦፊሳል፣ ህዝብ በአደባባይ አዲስ አበባን ለቀው እንዲወጡ አልጠየቁምና የባለስልጣኑ መቀሌ መከተም ፍርሃት እንደሆነ የሚስማሙ ይበዛሉ። በይፋ ውጡ ባይባልም የሚደረገው ሁሉ አዝማሚያው ወደ እዛ በመሆኑ ቀድመው መሸሻቸው አግባብ ነው የሚሉና የሚከራከሩም ጥቂት አይደሉም። መሸሻቸውን ሳይሆን ሲመች የተዘነጋውን ምስኪን ህዝብ መመሸጊያ አድርገው የሚያራቡት ፕሮፕጋንዳ እንጂ መሸሻቸው ችግር የለውም። ራሳቸው ላይ በር ቆልፈው ቁልፉን እንደመጣል አድርገው የሚወስዱ አሉ። ልክ ኢሳያስ ላይ ቆልፈው ከጎዳና እንዳወጡት እነሱም ታሪክ ተደገመባቸው በሚል ፖለቲካዊ ይዘቱን የሚያዩ አሉ። ሁሉም ምንም ቢሉም ህዝብ አሁን ታግቶ በኑሮ ውድነት እየተጎዳ ነው። 

መለስ ዜናዊ ኤርትራ እንዲቆለፍባት አድርገው ነበር። በኢህአዴግ ሸንጎ ላይና የተለያዩ ቃለ ምልልሶች ላይ ይህንኑ በስኬት ሲያነሱ ነበር። ዛሬ ደግሞ በተመሳሳይ ትግራይ ኤርትራን እየሆነች ነው የሚሉ ድምጾች እየተሰሙ ነው። ኤርትራ ዛሬ ቁልፉ ተከፍቶላት ከተገለለችበት ጓዳ ወጥታለሽ። ኤርትራን የቆለፉባትና እንዲቆለፍባት ሲሰሩ የነበሩ በተራቸው ራሳቸው ላይ ቆልፈዋል።

መለስ ኢሳያስ አፉወርቂን ከአሸባሪነትና ከአተራማሽነት ጋር በማያያዝ ከኢጋድ፣ ከአፍሪቃ ህብረትና ከመላው ዓለም እንድትገለል ለቅሶ የደርሷቸው ሎቢስቶቻቸውን በመጠቀም የቀመሩት ቀመር ውጤታም ነበር። ከኤርትራ ተሰደው የወጡ እንደሚሉት ህዝቡና ኢሳያስ ቆዳቸው ጠንካራ በመሆኑ እንጂ የኑሮ ውድነቱና ድህነቱ ኤርትራን ገርፏታል።

በዚህ መልኩ ኢሳያስ አፉወርቂን በማንበርከክ የሚፈልጉትን ሲስተም ኤርትራ ላይ ለመትከል ሲታትሩ የነበሩት የህወሃት የስሌት ማሽን እንዳሰቡት ሳይሆንና የልባቸው ሳይደርስ አልፈዋል። ህወሃትም ቤተመንግስቱንና የፖለቲካውን ሃላፊነት ለማስረከብ ተገዷል። ህወሃቶች ተሰባስበው ራሳቸው ላይ በር ሲቆልፉ፣ ኢሳያስ ቁልፉ ተሰብሮላቸው አዲስ አበባ ተምነሽንሸዋል። ሁኔታውን የሚከታተሉ እንደሚሉት አሁን የህወሃት ባለስልጣናት ቀደም ሲል ኤርትራ ላይ የተገበሩት እቅድ ራሳቸው ላይ በራሳቸው እያደረጉት ነው።

ከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ለዓለም የተሰራጨው መረጃ፣ በከፍተኛ ዘርፊያና የአገር ሃብት ብክነት፣ ለህዝብ ይፋ ባልሆኑ በርካታ ጥፋቶች ፍርሃቻ የትግራይ ህዝብን እንደ ማሽግ የተጠቀሙበት የህወሃት ባለስልጣናት ትግራይ ላይ እንዲቆለፍብባት ማድረጋቸውን በርካቶች ይተቻሉ። በትግራይ ውስጥም ሆነው ይህንን በመቃወም የሚሰሩ አሉ።

ወደፊት የሚሆነውን መተንበይ ቢያስቸግርም ዛሬ ላይ ልክ ኤርትራ ደርሶባት እንደነበረው በትግራይ ገበያው ከቀን ወደ ቀን እየናረ ነው። የውስጥ መረጃዎች እንደሚያስረዱት ከሆነ በተለይ ከአማራ ክልል ጋር ያለው ጡዘት ወደ ቀና መንገድ ካልተቀየረ፣ በኦሮሚያ ክልልና በፌደራል መንግስት የሚቋቋሙ ተጨማሪ አዳዲስ ኬላዎች ሰንሰለታቸውን ካጠበቁ ገበያው ከዚህ በላይ እንደሚንር ይጠበቃል።

ከኤርትራ ጋር የሚያገኛኙ መንገዶች በፌደራል ደረጃ በሚታዘዙ ኬላዎች ጥብቅ መመሪያ ተዘጋጅቶላቸው የሚከፈቱ ቢሆንም የፖለቲካ መላላት እንጂ የኑሮ ውድነትን እንደማይቀንሰው ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ እየገለጹ ነው።

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ ግጭቶች ጋብ እያሉ፣ የተፈናቀሉ ዜጎች እያገገሙ፣ ጥፋት የሰሩ በቁጥጥር ስር እየዋሉ። የብሄር ልክፍቱ እየተቀዛቀዘ በመሆኑ የፌደራል መንግስት በሰላማዊ መንገድ ሀግ ወደ ማስከበሩ ከሄደ በትግራይ ከዚህ የባሰም የገበያ ንረት እንደሚፈጠር ይጠበቃል።

በተደጋጋሚ እንደሚነገረው የህወሃት ባለስልጣናት ” ተከበናል” በሚል ህዝቡን እያስፈራሩና እያሰለጠኑ በማስታጠቅ ላይ ያሉት ለምን እንደሆነ፣ የት ድረስ ለመምጣትና ለመዋጋት እንደሆነ እስካሁን በገሃድ የተገለጸ ነገር የለም። ቀደም ሲል ኤርትራ ላይ እንደተደረገው ሆን ተብሎ በር የማጠባበቁ ስራ ሰለመሰራቱም በመንግስት በኩል ፍንጭ የለም። 

ዋዜማ ይህንን ዘግቧል ኑሮ እየከበደ ነው

ከፖለቲካዊ መጋጋሉ ባሻገር በትግራይ አሁንም የኑሮ ውድነት እየተባባሰ መምጣቱን መረጃዎች ያሳያሉ። ሪፖርተራችን ተዘዋውሮ እንደተመለከተው ከሁለት ወር ወዲህ በምግብ እህሎችና በአንዳንድ ሸቀጣ ሸቀጦች ላይ ከሚጠበቀው በላይ ዋጋ ጭማሪ ታይቷል፡፡ ለምሳሌ 2,700 ብር ሲሸጥ የነበረ ጤፍ አሁን 3,300 ብር ደርሷል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ጤፍ ከአዲስ አበባ -ሞጆ- በአፋር በኩል ዞሮ ስለሚመጣ ነው ተብሏል፡፡ እንደ በርበሬ፣ በቆሎ፣ አተር የመሳሰሉት ደግሞ ከ40 በመቶ እስከ 50 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በትግራይ ክልል መቀሌ፣ አዲግራት፣ ሽረ፡እንደስላለሴ፣ አክሱም የሚገኙ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ቀደም ሲል በትግራይና በአማራ ክልል የነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ሁለቱን ክልሎች የሚያገናኟቸው መንገዶች ሰላም አለመሆን እንደ ምክንያትነት ይጠቅሳል፡፡ አንዳንድ ነጋዴዎችም አልፎ አልፎ መንገድ ላይ ዝርፊ ስለሚገጥማቸው ከጎንደርና ከጎጃም ሲመጡ የነበሩ የምግብ እህሎች አሁን የሉም፡፡

ነጋዴዎች እንደሚሉት 14 ሺሕ ብር የነበረው የመኪና ኪራይ አሁን 26 ሺሕ ይጠየቃሉ፡፡ በጨለማና በድብቅ የሚገቡት የምግብ እህሎችም ዋጋቸው ከፍተኛ ነው፡፡ 
በፖለቲከኞች አለመግባባት ሁለቱ ሕዝቦች መቸገር የለባቸውም የሚሉት ነጋዴዎች ችግሩ ያለው ከላይ ከፖለቲከኞች ነው ይላሉ፡፡ ነዋሪዎች በበኩላቸው መንገዱ ሰላም እንዲሆን የሁለቱ ክልል ፖለቲከኞች ቁጭ ብለው መነጋገር እንዳለባቸው ይጠይቃሉ።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *