የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርጫ ወረዳ ወደ መኖሪያ ቀያቸው የተመለሱ ተፈናቃዮችን ጎበኙ።

በዞኑ ቀርቻ ወረዳ ጉራቹ ጀልዱ ቀበሌ በተለያዩ ግጭቶች ተፈናቅለው የነበሩ ከ3 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ወደ መኖሪያቸው ተመልሰዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርቻ ወረዳ ጉራቹ ጀልዱ ቀበሌ ተፈናቅለው በጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ ተጠልለው የነበሩት እና አሁን ወደ ቀድሞ ቀያቸው የተመለሱትን እነዚህን ተፋናቃዮች በጉብኝቱ ወቅት አነጋግረዋል።

ዜጎቹ አሁን ላይ ከበፈቱ የተሻለ ሰላም መኖሩን በማንሳት፥ ይህንን ሰላም አስተማማኝ በማድረጉ ረገድ መንግስት እንዲሰራ ጠይቀዋል። መልሶ ለማቋቋም እየቀረበ ያለውም ድጋፍ በቂ አለመሆኑን ያነሱት ተመላሾቹ፥ ክረምት እየገባ በመሆኑ ወደ አርሻ ስራ መመለስ እንዲችሉ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም በጉብኝቱ ወቅት ጥያቄ አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በበኩላቸው መንግስት በቻለው መጠን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል የገቡ ሲሆን፥ የዘርና የምርጥ ዘር እንዲቀረብ ይደረጋልም ብለዋል።

ጉጂ እና ጌዲኦ ለዘመናት አብሮ የኖሩ ህዝቦች መሆናቸውን በማንሳትም ለሰላም ሁሉም ከመወቃቀስ ወጥቶ በጋራ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስትዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ እና የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ጎብኝተዋል። የልዑካን ቡድኑ ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የሚረዳ የግንባታ ዕቃዎችንም ለማኅበረሰቡ አባላት ለግሷል።

በሰላማዊት ካሳና አዳነች አበበ

 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *