የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ የቀድሞውን የክለቡን ተጫዋች ካሳዬ አራጌን ለቀጣዩ የውድድር አመት የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መምረጡን የአገር ቤት መገናኛዎች ክለቡን በመጥቀስ ይፋ አድርገዋል። በአዲስ ሃሳብ ቡናን ውበትና ማስተዋል የተላበስ ኳስ እንዲጫወት ያስቻለው ካሳዬ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሳይሆን በቂ ጊዜ እንደሚያስፈልገው፣ እሱም ካለፈው ልምዱ በመማር ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

የቡና የመሃል ሜዳ መሃንዲስ ካሳዬ ኳስ መያዝ በሚለው መርህ የሚታወቅ ሲሆን ቡናን ባሰለጠነበት አጭር ጊዜ ውስጥ ” አደገኛ – ቡና ” የሚለው ዜማ ያለማቋረጥ እንዲዘፈን አድርጎ ነበር። የአገራችንን ተጫዋቾች ሽሎታ ያገናዘበ፣ በረኛን እንደ አንድ ትርፍ ተጫዋች በማሰብ በጨዋትው ማሳተፍና፣ ኳስን በመያዝ ጥቃትን መቆጣጠር፣ በአጭር ቅብብል ተጋግዞ መንቀሳቀስ …. የሚለው ሃሳብ፣ በጥለዛ አሰልጣኞች ተቃውሞና ዘመቻ የተጀመረበት ከጅምሩ ነበር።

“ሳይንሳዊ ስልጠና” በሚል የሚደሰኩሩ አንዳንድ ራሳቸውን አዋቂ ያደረጉ ጸሃፊዎችና አውሪዎች፣ የካሳዬን ስልጠና ለመተቸት ቀዳሚ ነበሩ። ማንም ሳይገባው ካሳዬና ገነነ መኩሪያ እንዲሁም ማንም የማያውቀው ሚጥሚጣው የፎቶ ግራፍ ባለሙያው  አበበ ይህንን ሃሳብ ሲያመጡ የተቀበላቸው ክፍሎ እጅግ ጥቂት ነበር። ይሁን እንጂ ከጅምሩ ዛማሌክን በሜዳው ከውድድር ውጪ ማድርገ የተቻለበት አካሄድ ነበር። ለወትሮው ግብጽ ሄደው የሚጠቀጥቅባቸው አሰልጣኞች ይህንን ውጤት እንኳን ማክበር አልቻሉም።

ካሳዬ.jpg

የካሳዬ ሃሳብ የራሱ ተጫዋቾች፣ እንዲሁም ፈጥኖ ማሰብንና ጥሩ የኳስ ክህሎት እንዲሁም ብዙ አብሮ መጫወትን የሚጠይቅ እንቅስቃሴ ሲሆን እያደር የሚታረምና የሚዳብር ነው። ለዚሁ ይመስላል ካሳዬ አራጌ ከአሜሪካ  ከቦርዱ ጋር ከተነጋገረ እና ስምምነት ላይ ከተደረሰም፥ የውድድር አመቱ ሳይጠናቀቅ የተጫዋቾች ምርጫ እንዲያደርግ ውሳኔ ላይ መደረሱንም ክለቡ አስታውቋል።

የክለቡ የስራ አመራር ቦርድ አዲስ የአሰልጣኝ ቅጥርን የሚያከናውን የእግር ኳስ ኦፕሬሽንና ቴክኒክ አስተዳደር ኮሚቴ አዋቅሯል። ኮሚቴውም በቦርዱ በተሰጠው ውሳኔ መሰረት የክለቡን አሰልጣኝ ለመቅጠር የተለያዩ መመዘኛዎችን በማውጣት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። በመጨረሻም የክለቡን የጨዋታ ዘይቤ ይረዳል በሚል የቀድሞውን የክለቡን ኮከብ ካሳዬ አራጌን በአሰልጣኝነት እንዲመረጥ ወስኗል።

ውሳኔው ትክክለኛና ሲሆን የቡና ቦርድ ትዕግስት ተላብሶ ሙሉ ድጋፉን ለአሰልጣኙ ይሰታል ተብሎ ይጠበቃል።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *