የአማራ ክልል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር ፈጥረዋል የተባሉ 224 ሰዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አስታወቀ። የአማራ ክልል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ሃላፊ አቶ ምግባሩ ከበደ በዛሬው ዕለት በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ ምግባሩ በመግለጫቸው በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጥሩ ግጭቶች የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ለህግ የማቅረብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ መሰረትም በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር ፈጥረዋል የተባሉ 224 ሰዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ነው የገለጹት።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሰዎች ውስጥም 150 ከማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ፣ 42 ከኦሮሚያ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ፣ 24 ከአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን እንዲሁም 8 ከሰሜን ሽዋ ዞን መሆናቸውን ሃላፊው ተናግረዋል።

ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገው የምርመራ ሂደትም ከፌዴራልና ክልል እንዲሁም ግጭቶቹ ከተከሰቱባቸው አካባቢዎች ያሉ የዞን ፖሊሶችና ዓቃቤ ህጎች መሳተፋቸውን አቶ ምግባሩ ገልጸዋል።

ምርመራው በሶስቱ አካላት የተካሄደውም ተጠርጣሪዎች ያለ በቂ መረጃ እንዳይያዙ ለማድረግና በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ሰብዓዊ መብታቸው ተጠብቆ ለህግ እንዲቀርቡ ለማድረግ መሆኑን አብራርተዋል።

በናትናኤል ጥጋቡ

FBC

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *