በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ወደ ቀያቸው ለተመለሱ ዜጎች ለዘርና ማዳበሪያ ግዥ የሚውል ከ627 ሚሊየን ብር በላይ በድጋፍና በብድር መልክ እንዲሰጥ ተወሰነ

) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ካቢኔ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በቅርቡ ወደ ቀያቸው ለተመለሱ ዜጎች ለዘርና ማዳበሪያ ግዥ የሚውል ከ627 ሚሊየን ብር በላይ በድጋፍና በብድር መልክ እንዲሰጥ ውሳኔ አሳልፏል።

ካቢኔው በዛሬው ዕለት ባካሄደው 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በክልሉ ከሚገኙ ስምንት ዞኖች በተለያዩ ምክንያቶች ተፈናቅለው በቅርቡ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለተደረጉ ዜጎች ለዘርና ማዳበሪያ ግዥ የሚውል ከ627 ሚሊየን ብር በላይ በድጋፍና በብድር መልክ እንዲሰጥ ወስኗል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ካቢኔው ተፈናቃዮች በመደበኛ የግብርና ስራቸው ተሰማርተው ውጤታማ እንዲሆኑና ከዕለታዊ ድጋፍ ተላቀው እራሳቸውን እንዲችሉ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከተሰበሰበው ገንዘብ ነው ለዘርና ለማዳበሪያ ግዥ የሚውል ወጪ እንዲሆን ውሳኔ ያስተላለፈው።

የኦሮሚያ ክልል መንግስት የኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ውጪ እንዲሆን ከተወሰነው ገንዘብ 169 ሚሊየን 825 ሺህ 541ብር የሚሆነው ለዘር ግዥ በድጋፍ መልክ የሚሰጥ ነው ።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ቀሪው ብር ደግሞ በብድር መልክ ለማዳበሪያ ግዥ የሚውል መሆኑን ነው ሃላፊው የተናገሩት ።

በምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ባሌ፣ ቦረና ፣ ጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች የሚገኙና በቅርቡ ወደ ቀያቸው የተመለሱ አባወራ አርሶ አደሮች የዚህ ብድርና ድጋፍ ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል።

የክልሉ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽንና የግብርና ቢሮም አፈፃፀሙን እንዲከታተሉና ለአርሶ አደሮቹ በጊዜ ግብዓት እንዲያቀርቡ ካቢኔው አቅጣጫ አስቀምጧል ነው ያሉት ።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

አዲስ አበባ፣ሰኔ 6፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *