በትግራይ ክልል ከለላ ተሰጥቷቸው የሚገኙትና በክልሉ የእለት ተዕለት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ጉልህ ሚና እንዳላቸው የሚነገርላቸው የቀድሞው የድህንነት ሹም አቶ ጊታቸው አሰፋን ጭምሮ ሶስት ተከሳሾች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአዋጅ መጥሪያ እንዲደርሳቸው ፍርድ ቤት አዘዘ።

ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ ሌሎች ሶስት ተከሳሾች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዲጠሩ ያዘዘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ነው። ፍርድ ቤቱ በከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አመራር ለነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ አቶ አጽበሃ ግደይ፣ አቶ አሰፋ በላይና አቶ ሹሻይ ልዑል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ እንዲተላለፍላቸው ሲል ያዘዘው ተከሳሾቹ በፖሊስ ሃይል አስገድዶ ማቅረብ ባለመቻሉ ነው።

Related stories   ሱዳን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ላይ የሉዓላዊነት ጥያቄ እንደምታነሳ አስጠነቀቀች፤ "ብሄራዊ የጀግንነት ጥሪ ያፈልጋል"

ምንም እንኳን ተጠርጣሪዎች ያሉበት ቢታወቅም፣ ችሎቱ በእነ አቶ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ ዛሬ ተሰይሞ ከነበረበት ጉዳይ ውስጥ አንዱ ያልቀረቡ አራቱ ተከሳሾችን ጉዳይ መርምሮ ብይን ለመስጠት ሲሆን፤ ተከሳሾቹ በምርመራ ወቅት እና አሁንም ተጨባጭ አድራሻቸው ባለመታወቁ ምክንያት እንዲሁም ተከሳሾችም የቀረበባቸው ክስ ከተረጋገጠባቸው ከ12 ዓመት በላይ የሚያስቀጣቸው ነው በማለት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዲጠሩ ታዝዟል፡፡ የጋዜጣውን ጥሪ ለመከታተልም ለሐምሌ ዘጠኝ ቀጥሯል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *