ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠባቂ በደብረዘይት ባልታወቀ ምክንያት ተገድሎ ተገኘ ተባለ

ከስደት ከተመለሰ በኋላ ቻይና በመሄድ ተጨማሪ ስልጠና ወስዶ የጠቅላይ ሚንስትር ታማኝ ጠባቂ ሆኖ በማገልገል ላይ እንደነበረ ነው እስከ አሁን ባላወቅኩት ምክንያት ተገድሎ ተገኘ ነው የተባለው።

አዲሱ አለሙ ይባላል በትላንትናው እለት ባልታወቀ ምክንያት በደብረዘይት ተገድሎ መገኘቱን ስሰማ ልቤ እጅግ አዘነ።
ከአዲሱ ጋር የተገናኘነው የዛሬ 3 አመት ገደማ በናይሮቢ ኬንያ በስደት ላይ ሳለ ነው።

በወቅቱ በነበረው የህዋሃት አገዛዝ ተመርሮ የወጣው ይህ ወጣት የአጋዚ አባል የነበረ ሲሆን በንፁሃን ላይ የሚደርሰውን ግፍ በመቃወሙ ምክንያት ለህይወቱ የመጣውን ሞት ሸሽቶ ለሁለት አመት ከ 6ወር ያህል በኬንያ እራሱን ደብቆ ቆይቷል ። ይሁንና በሃገሪቱ ላይ በመጣው አንፃራዊ ሰላምና መንግስት ለስደተኞች ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ባቀረበው ጥሪ መሰረት ወደ ሃገሩ መግባቱን ሰምቼ ሳልቆይ ወራቶች ሳይቆጠሩ ደግሞ ሞቱን ሰማሁኝ።

እንደሰማሁት ከሆነ ከስደት ከተመለሰ በኋላ ቻይና በመሄድ ተጨማሪ ስልጠና ወስዶ የጠቅላይ ሚንስትር ታማኝ ጠባቂ ሆኖ በማገልገል ላይ እንደነበረ ነው እስከ አሁን ባላወቅኩት ምክንያት ተገድሎ ተገኘ ነው የተባለው።
አዲሱ የ28 አመት ወጣት ሲሆን ቆራጥ፣ ላመነበት ነገር ፍንክች የማይል እና በኢትዮጵያዊነት የማይደራደር ጀግና ልጅ ነበረ።
ለወዳጆቹና ለመላው ቤተሰቦቹ መፅናናትን እየተመኘው የንፁሃንን ደም በከንቱ ለሚያፈሱ ልቦና ይስጥልን የሟቹን ነፍስ ይማር። Medhanit Reda እንደጻፈችው

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   "በፕሮፓጋንዳ እስካሁን የተወናበድኩት ይበቃኛል ብሎ ቆም ብሎ ማሰብም ይገባል ... ወጣቱን ያለ እድሜው ህይወቱን ይቀጩታል"ሌ.ጀ ዮሐንስ
0Shares
0
Read previous post:
በክልሎች በልዩ ሃይል ስም የተቋቋመው ከፖሊስ በላይ ነው – የፌዴራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር

ከሰሞኑ የባለስልጣናት ግድያ ጋር ተያይዞ በየክልሉ ያሉ የ”ልዩ ኃይሎች” ጉዳይ እያጠያየቀ ነው።መንግስታዊው “አዲስ ዘመን” ጋዜጣ...

Close